ሦስተኛው የዓለም ጦርነት ከተጀመረ በአውሮፓ ብቻ እንደማይወሰን ሩሲያ አስጠነቀቀች።
ሦስተኛ ዓመቱ ላይ የሚገኘው የሩሲያ-ዩክሬን ጦርነት መልኩን እየቀያየረ እንደቀጠለ ይገኛል።
ከ20 ቀን በፊት ዩክሬን ምዕራብ ሩሲያ በኩል ባለችው ኩርስክ ግዛት በኩል ያልተጠበቀ ጥቃት በማድረስ በርካታ መንደሮችን መቆጣጠሯ ይታወሳል።
ሩሲያ ጥቃቱ ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ በውጭ ኃይሎች ላይ የተፈጸመባት ጥቃት መሆኑን አስታውቃለች።
ከዚህ በተጨማሪም ከጥቃቱ ጀርባ ምዕራባዊያን ሀገራት ሰራሽ የሆኑ ዘመናዊ የጦር መሳሪያዎች እንዳሉ
ይፋ አድርጋለች።
የሩሲያ ውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጊ ላቭሮቭ በሞስኮ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ እንዳሉት፤ የዩክሬን ኩርስክ ጥቃት የሦስተኛው የዓለም ጦርነትን የሚቀሰቅስ ነው ብለዋል።
ሚኒስትሩ አክለውም “ምዕራባዊያን ለዩክሬን በሰጡት መሳሪያ ሩሲያን እንድትመታ በማድረግ በእሳት እየተጫወቱ ነው” ሲሉ ተናግረዋል።
“ሦስተኛው የዓለም ጦርነት ከተጀመረ በአውሮፓ ብቻ የሚያበቃ አይደለም” ያሉት ሚኒስትሩ ምዕራባዊያን ዩክሬን በመጠቀም ወደ ከፋ ውድመት እየመሩ ነው ሲሉም አስጠንቅቀዋል።
ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ዩክሬን በኩርስክ ለፈጸመችው ጥቃት ተገቢው ምላሽ ይሰጣል ማለታቸው ይታወሳል።
የዩክሬን ፕሬዚዳንት ቮሎዶሚር ዘለንስኪ በበኩላቸው፤ ከኩርስክ ጥቃት በኋላ በሰጡት መግለጫ፤ የሩሲያ ያ ሁሉ ዛቻ ምንም ነው ሲሉ ተናግረው፤ ምዕራባዊን ሀገራት ተጨማሪ ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።
እንደ ሩሲያ ዕምነት ከሆነ ዩክሬን በሩሲያዋ ኩርስክ ግዛት ጥቃት የፈጸመችው በምዕራባዊን ሀገራት ጦር መሳሪያ፣ የሳተላይት መረጃዎች እና ሌሎች ድጋፎች ታግዛ ነው።
ሩሲያ ከ2022 ጀምሮ ሉዓላዊ ደህንነቷ አደጋ ውስጥ ከገባ የኑክሌር ጦር መሳሪያዋን እንድትጠቀም የሚፈቅድላት ሕግ እንዳላት ፕሬዚዳንት ፑቲን በተደጋጋሚ ማስጠንቀቃቸው ይታወሳል።
አዲስ ዘመን
TIPS
The Wars We Still Can Stop
Ethiopia: Israel Foreign Minister Says His Country Wants to Be Part of Ethiopia’s Success
A Nation Silenced: How the 1993 Referendum Stripped All Ethiopians of Their Sea
The 1976 TPLF Manifesto: TPLF’s “Republic of Greater Tigray”
Away from the global spotlight, Eritreans are trapped in a garrison state
Testimonials of a Sudanese Intelligence Officer on the Proxy war between Sudan and Ethiopia from 1970s to early 1990s
Ethiopia-Eritrea Tension: A Volatile History that Never Truly Ended – Could Assab Become Africa’s Crimea?
“As an outlier among the five tplf leaders, I wasn’t part of the armed struggle tradition”
Former Tigray fighters say no to war
Don’t Risk Your Future: The United States Cracks Down on Illegal Immigration
Counter-Video by EBC Challenges EBS Broadcast, Sparks Public Outcry Over Alleged Misinformation
Ethiopia and Eritrea Slide Closer to War amid Tigray Upheaval
Sea Outlet Serious and Unabated Agenda for Ethiopia: Retired Lieutenant General Yohannes
Israel’s Peace With Egypt Is Starting to Crack
Egyptian, Eritrean FMs reject involvement of non-bordering countries[Ethiopia] in Red Sea security
Ethiopia, Creditors Agree on $8.4 Billion Debt Restructuring