ሞዛምቢክ በሰሜናዊ የሀገሪቱ ክፍል የሚገኘውን የናካላ ወደብ የተወሰነ ክፍል የባህር በር የሌላት ማላዊ አልምታ እንድትጠቀምበት ስምምነት ላይ ደረሰች።
ስምምነቱ ሞዛምቢክ በሰሜናዊው የሃገሪቱ ክፍል የሚገኘውን የናካላ ወደብ የባህር በር ለሌላት ጎረቤቷ ማላዊ በከፊል ለማከራየት የሚያስችል ነው።
የሞዛምቢክ ፕሬዝዳንት ፊሊፔ ኒዩሲ እና የማላዊው አቻቸው ላዛሩስ ቻክዌራ ባለፈው ሳምንት የመግባቢያ ሰነድ መፈራረማቸው ተጠቅሷል።
ሁለቱ ሀገራት ያከናወኑት ስምምነት የንግድ ግንኙነታቸውን፣ በኤሌክትሪክ አቅርቦትና በሌሎች የኢኮኖሚ ዘርፎች ያላቸውን ትስስር ለማሳደግ ያለመ መሆኑም ተገልጿል ።
በስምምነቱ መሰረትም በሞዛምቢክ ሰሜናዊ ክፍል የሚገኘውን ናካላ ወደብን የተወሰነ ክፍል ማላዊ በሊዝ አልምታ ለወጪና ገቢ ንግዷ ትጠቀማለች።
የሞዛምቢክ ፕሬዝዳንት ፊሊፔ ኒዩሲ ስምምነቱ በተፈረመበት ወቅት፤ ስምምነቱ ሁለቱንም አገሮች እንደሚጠቅም አንስተው፤ እንደ ሞዛምቢክ-ማላዊ የጋራ የኤሌክትሪክ ሃይል ማመንጫ ፕሮጀክት አይነት ጅምር ፕሮጀክቶችን ለማጎልበት እንደሚረዳ ተናግረዋል።
ስምምነቱ ቀደም ሲል በኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት የተሳሰሩትን ሁለቱን ሀገራት ትብብር የሚያጠናክር መሆኑንም ፕሬዝዳንት ኒዩሲ ተናግረዋል።
የማላዊ ፕሬዚዳንት ላዛሩስ ቻክዌራ በበኩላቸው፤ የናካላ ወደብ ሀገሪቱ እቃ ለማጓጓዝ የምታወጣውን ከፍተኛ ወጪ ለመቀነስ እንደሚያግዛት ገልጸዋል፡፡
የናካላ ወደብ በማላዊ፣ ዛምቢያ እና ሞዛምቢክ በጋራ እየተገነባ ያለ የናካላ ልማት ኮሪደር አካል ሲሆን፤ የፕሮጀክቱ ዓላማ ወደብ ለሌላቸው ማላዊ እና ዛምቢያ የባህር መዳረሻን ለማመቻቸት እና የቀጠናውን የልማት ትስስር ለማሳደግ ነው ተብሏል።
የናካላ ወደብ ኮሪደር ልማት ሞዛምቢክን ጨምሮ የባህር በር የሌላቸውን ማላዊ እና ዛምቢያ ተጠቃሚ በሚያደርግ አግባብ በጋራ እየለማ እንደሚገኝም የማሪታይም ኤክስኪዩቲቭ ዘገባ ያሳያል።
TIPS
The Wars We Still Can Stop
Ethiopia: Israel Foreign Minister Says His Country Wants to Be Part of Ethiopia’s Success
A Nation Silenced: How the 1993 Referendum Stripped All Ethiopians of Their Sea
The 1976 TPLF Manifesto: TPLF’s “Republic of Greater Tigray”
Away from the global spotlight, Eritreans are trapped in a garrison state
Testimonials of a Sudanese Intelligence Officer on the Proxy war between Sudan and Ethiopia from 1970s to early 1990s
Ethiopia-Eritrea Tension: A Volatile History that Never Truly Ended – Could Assab Become Africa’s Crimea?
“As an outlier among the five tplf leaders, I wasn’t part of the armed struggle tradition”
Former Tigray fighters say no to war
Don’t Risk Your Future: The United States Cracks Down on Illegal Immigration
Counter-Video by EBC Challenges EBS Broadcast, Sparks Public Outcry Over Alleged Misinformation
Ethiopia and Eritrea Slide Closer to War amid Tigray Upheaval
Sea Outlet Serious and Unabated Agenda for Ethiopia: Retired Lieutenant General Yohannes
Israel’s Peace With Egypt Is Starting to Crack
Egyptian, Eritrean FMs reject involvement of non-bordering countries[Ethiopia] in Red Sea security
Ethiopia, Creditors Agree on $8.4 Billion Debt Restructuring