በ2024 ፓሪስ ኦሊምፒክ በ800 ሜትር የሴቶች ውድድር ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ለፍጻሜ ደረሱ። በ800 ሜትር የሴቶች ግማሽ ፍፃሜ አትሌት ወርቅነሽ መሰለ እና ፅጌ ድጉማ ፍጻሜውን ተቀላቅለዋል።
በፓሪስ ኦሎምፒክ 800ሜ ሴቶች የግማሽ ፍፃሜ ማጣሪያ ውድድሯን በሁለተኛው ምድብ ያደረገችው ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ፅጌ ዱጉማ ለፍፃሜ ደርሳለች። አትሌት ፅጌ ዱጉማ የግማሽ ፍፃሜ ውድድሯን 1:57:47 በሆነ ሰዓት በመግባት በአንደኛነት ማጠናቀቅ ችላለች። በመጀመሪያው ምድብ የተወዳደረችው አትሌት ወርቅነሽ መሰለ ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ ለፍፃሜ መድረሷ ይታወቃል።
የ800ሜ ሴቶች ፍፃሜ ውድድር ሰኞ ሐምሌ 29/2016 ዓ.ም ምሽት 4:45 የሚደረግ ይሆናል። በወኖች 1500 ሜትር ማጣሪ የተሰለፉት አትሌቶች አልተሳካላቸውም።