የተለያዩ የኤርትራ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ጥምረት በመመስረት በጋራ ለመታገል መወሰናቸውን አስታወቁ
የተለያዩ የኤርትራ ተቃዋሚ ፓርቲዎች አምባገነን ያሉትን አሁን በሥልጣን ላይ ያለውን መንግሥት ለመታገል የጋራ ጥምረት መመስረታቸውን አስታወቁ።
ፓርቲዎቹ በደቡብ ምዕራብ ጀርመን በምትገኘው ቪዝባደን በተባለችው ከተማ ሲያካሂዱት የነበረውን ጉባኤ ማጠናቀቃቸውን ገልጸዋል።
«የኤርትራ ፖለቲካዊ ሃይሎች ጥምረት» የተሰኘ የጋራ ግንባር መመስረታቸውን የአደራጅ ኮሚቴው ምክትል ፕሬዚደንትና የቀይ ባሕር ዓፋር ዴሞክራሲያዊ ድርጅት ከፍተኛ አመራር አባል አቶ ያሲን መሐመድ ዓብደላ እንደገለጹለት የጀርመን ድምጽ ሬድዮ ዘግቧል።
የኤርትራ ፖለቲካዊ ሃይሎች ጥምረት የተባለው የጋራ ግንባር የመሰረቱት ፓርቲዎች የቀይ ባሕር ዓፋር ዴሞክራሲያዊ ድርጅት፣ የኤርትራ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ እና በሥሩ አራት ፓርቲዎችን ያካተተው የኤርትራ አንድነት የጋራ ግንባር የተባሉ እንደሆኑ አቶ ያሲን መግለጻቸውን ዘገባው አስታውቋል።
ኤርትራ ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች የሚከበሩባት ሀገር እንድትሆን፣ የራስን ዕድል በራስ የመወሰን መብት እንዲከበር፣ በሕገ መንግሥት የሚመራና ተገማች መንግሥት ለማቋቋም፣ በኤርትራ የመድብለ ፓርቲ ሥርዓት እንዲቋቋም በጋራ ለመሥራት መስማማታቸውን ዘገባው አካቷል። ለአፍሪቃ ቀንድ መተራመስ አስተዋጽኦ እያደረገ ነው ላሉት በኤርትራ ያለው መንግሥት ለመታገል በምናደርገው ጥረት የአካባቢው ሃገራትና የኤርትራ ሕዝብ እንዲሁም ዓለም አቀፍ ድርጅቶችና መንግሥታት ከጎናቸው እንዲቆሙ አቶ ያሲን ጥሪ ማቅረባቸውን ዘገባው አስታውቋል
TIPS
The Wars We Still Can Stop
Ethiopia: Israel Foreign Minister Says His Country Wants to Be Part of Ethiopia’s Success
A Nation Silenced: How the 1993 Referendum Stripped All Ethiopians of Their Sea
The 1976 TPLF Manifesto: TPLF’s “Republic of Greater Tigray”
Away from the global spotlight, Eritreans are trapped in a garrison state
Testimonials of a Sudanese Intelligence Officer on the Proxy war between Sudan and Ethiopia from 1970s to early 1990s
Ethiopia-Eritrea Tension: A Volatile History that Never Truly Ended – Could Assab Become Africa’s Crimea?
“As an outlier among the five tplf leaders, I wasn’t part of the armed struggle tradition”
Former Tigray fighters say no to war
Don’t Risk Your Future: The United States Cracks Down on Illegal Immigration
Counter-Video by EBC Challenges EBS Broadcast, Sparks Public Outcry Over Alleged Misinformation
Ethiopia and Eritrea Slide Closer to War amid Tigray Upheaval
Sea Outlet Serious and Unabated Agenda for Ethiopia: Retired Lieutenant General Yohannes
Israel’s Peace With Egypt Is Starting to Crack
Egyptian, Eritrean FMs reject involvement of non-bordering countries[Ethiopia] in Red Sea security
Ethiopia, Creditors Agree on $8.4 Billion Debt Restructuring