ከሰማዩ መጥራት ጋር በተያያዘ ስያሜውን እንዳገኘ የሚነገረው የቡሄ በዓል መላጣ ወይም ገላጣ የሚል ትርጉም የተሰጠው ከክረምቱ መውጣት እና አዲስ ዘመን መምጣት ጋር በተያያዘ እንደሆነ በቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ የሥነ-መለኮት መምህር የሆኑት ቀሲስ አንድነት አሸናፊ ከኢቢሲ ጋር በነበራቸው ቆይታ ገልጸዋል።
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ ቅድሚያ የሚሰጠው ስያሜ ግን ደብረታቦር የሚለው እንደሆነ ጠቅሰው፣ ይህም ከኢየሱስ ክርስቶስ 9ኙ ዐበይት በዓላት አንደኛው ነው ብለዋል።
“ኢየሱስ ክርስቶስ በደብረታቦር ተራራ የገለጠው ምስጢር ከዕለቱ ስድስት ቀናት በፊት ሰዎች ማን እንደሚሉት ደቀ መዛሙርቱን በመጠየቅ “እናንተስ ማን ትሉኛላችሁ?” ብሎ ከጠየቀበት እና ካስተማረበት ምስጢር ጋርም የሚገናኝ” ነው ብለዋል። ለዚያ ጥያቄ መለስ ለማሰጠትም ወደ ደብረታቦር ተራራ እንደወሰዳቸውም መምህሩ ተናግረዋል።
“በቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ ከፍታ ሲወጣ ያደክማል፤ ከወጡ በኋላ ግን የራቀውን አቅርቦ፣ የረቀቀውን አጉልቶ ስለሚያሳይ ደስ የሚያሰኝ ነው” ያሉት መምህሩ፤ “ክርስቶስም መሞት የለብህም፤ ማን ይሾመናል፤ ከአንተ ጋር አብረን እንሆናለን” የሚለውን ሃሳባቸውን ወደ ተራራው ወስዶ፣ ከፍ ወዳለው እሳቤ እንዲመጡ ያደረገበት ምስጢር መሆኑንም ጠቁመዋል።
በሃይማኖት ውስጥ የሚኖር ሰውም ሁሌም ከፍ ያለውን አስተሳሰብ ይዞ ወደ ከፍታ፣ ወደ መልካም፣ ወደ በጎ አስተሳሰብ ሊወጣ ይገባል ብለዋል መምህር አንድነት አሸናፊ።
ደብረታቦር ላይ ነብሳቸው ከሥጋቸው የተለየች እና በሕይወት ያሉ ሙሴና ኤሊያስ የተገለጹበት በመሆኑ፤ ሰዎች ክርስቶስን ኤልያስ ነው፣ ሙሴ ነው ይሉት እንደነበር እና ይህም ምስክርነት በተራራው የተገለጠበት ሕያው ኢየሱስ ክርስቶስ መሆኑን ያስረዳበት እንደሆነም አንስተዋል።
ከዚህ ሐይማኖታዊ መሰረት የመነጩ የተለያዩ ባህላዊ ጨዋታዎች እንደሚከወኑ የገለጹት መምህሩ፤ ቤተክርስቲያን ደብረታቦርን የምታከብረው ከዋዜማው ጀምሮ መሆኑን ጠቁመዋል።
በሜሮን ንብረት etv
TIPS
The Wars We Still Can Stop
Ethiopia: Israel Foreign Minister Says His Country Wants to Be Part of Ethiopia’s Success
A Nation Silenced: How the 1993 Referendum Stripped All Ethiopians of Their Sea
The 1976 TPLF Manifesto: TPLF’s “Republic of Greater Tigray”
Away from the global spotlight, Eritreans are trapped in a garrison state
Testimonials of a Sudanese Intelligence Officer on the Proxy war between Sudan and Ethiopia from 1970s to early 1990s
Ethiopia-Eritrea Tension: A Volatile History that Never Truly Ended – Could Assab Become Africa’s Crimea?
“As an outlier among the five tplf leaders, I wasn’t part of the armed struggle tradition”
Former Tigray fighters say no to war
Don’t Risk Your Future: The United States Cracks Down on Illegal Immigration
Counter-Video by EBC Challenges EBS Broadcast, Sparks Public Outcry Over Alleged Misinformation
Ethiopia and Eritrea Slide Closer to War amid Tigray Upheaval
Sea Outlet Serious and Unabated Agenda for Ethiopia: Retired Lieutenant General Yohannes
Israel’s Peace With Egypt Is Starting to Crack
Egyptian, Eritrean FMs reject involvement of non-bordering countries[Ethiopia] in Red Sea security
Ethiopia, Creditors Agree on $8.4 Billion Debt Restructuring