ክረምቱን ተከትሎ በተለያዩ ክልሎች በተከሰተ የመሬት መንሸራተት፣ ናዳ እንዲሁም የጎርፍ አደጋ የበርካታ ሰዎች ሕይወት ያለፈ ሲሆን አሁንም እያጋጠመ ያለ አደጋ ነው፡፡ የመሬት መንሸራተት በተዳፋታማ አካባቢዎች ከፍተኛ ዝናብ በሚዘንብበት ወቅት፣ በበረዶ መቅለጥ፣ በመሬት መሰንጠቅና መንቀጥቀጥ፣ የእሳተ ገሞራ፣ በከርሰ መሬት ውስጥ ባለ የውሃ መጠን ለውጥና በሌሎች ሰው ሠራሽ ምክንያቶች የሚከሰት ነው፡፡
ከሌሎች ተፈጥሯዊ ክስተቶች በበለጠ የመሬት መንሸራተት በስፋት እንዲሁም በየትኛውም የምድራችን ክፍል ላይ ሊከሰት እንደሚችል የተለያዩ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ በኢትዮጵያም በቅርቡ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጎፋ ዞን ፤ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ቤንች ሸኮ፤ ካፋና ዳውሮ ዞኖች፤ በሲዳማ ክልል ማዕከላዊ ሲዳማ ዞን፤ በድሬዳዋ ከተማ፤ በትግራይ ክልል፣ በአማራ ክልል ደቡብ ወሎና ሰሜን ጎንደር ዞን፤ በኦሮሚያ ክልል ጅማ፤ ቄለም ወለጋ፤ ሐረርጌና አርሲ ዞኖች አጋጥሟል፡፡
በዚህም በአደጋው ሕይወታቸው ካለፈ ዜጎች በተጨማሪ ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉትና የወደመው ንብረት እንዲሁ በቀላሉ የሚገመት አይደለም፡፡ በክልሎቹም ለአደጋ ተጋላጭ የሆኑ ቦታዎች ተለይተው ነዋሪዎች በሌሎች ቦታዎች የማስፈር ሥራዎች ተሠርቷል፡፡
ይህንንም ተከትሎ የሠብዓዊ ድጋፎች፣ ምግብና ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሳቁሶች ፣ የተለያዩ የህክምና ቁሳቁሶች፣ የግንባታ ግብዓቶች በጎፋ ወረዳ በመሬት መንሸራተት ምክንያት ለተጎዱ ወገኖች ድጋፍ መደረጉ ተመላክቷል፡፡
በሚቀጥሉት የክረምቱ ጊዜያትም ቅጽበታዊ ጎርፍ፣ የመሬት መንሸራተትና የወንዞች ሙላት ሊያጋጥም ስለሚችል ማህበረሰቡ፣ የሚመለከታቸው አካላት አስፈላጊውን ዝግጅት እንዲሁም ጥንቃቄ ሊያደርጉ እንደሚገባ ኢትዮጵያ የሚቴዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት ባወጣው መግለጫ አሳስቧል፡፡ በተለይ ተዳፋታማ በሆኑ አካባቢዎች የመሬት መንሸራተትና መሰንጠቅ፣ እንዲሁም የሰብል በጎርፍ የመጠረግ ሁኔታዎች እንዳይኖር መጠንቀቅ እንደሚያስፈልግም አስጠንቅቋል፡፡
ዓለምን እያጋጠማት ባለው የአየር ንብረት ለውጥ ሳቢያ የመሬት መንሸራተት እየተደጋጋመና እየከፋ መምጣቱን እና ይህም ቀጣይነት ሊኖረው እንደሚችል ባለሙያዎች ይጠቁማሉ፡፡ በቅርቡም በሀገራችን በተለያዩ ክልሎች የተከሰተው የመሬት መንሸራተትና ናዳ ከዚሁ ጋር ተያያዥነት ያላቸው መሆኑን ያስረዳሉ፡፡
የአፈር ሳይንስ ባለሙያው መሀመድ ሃሰን (ፕ/ር) ለኢፕድ በሰጡት ቃል፣ በኢትዮጵያ ውስጥ የመሬት ችግር ያለ በመሆኑ ከመሬት አጠቃቀም ጉድለትና የሀብት ጥበት የተነሳ አዲስ እንዳይከሰት ማድረግና አደጋው የተከሰተባቸው አካባቢዎች ላይ የመልሶ ማልማት ሥራም መከናወን አለበት ይላሉ፡፡
አደጋው የደረሰባቸው አካባቢዎች ወደ ልማት ለመመለስም የችግሩ መጠን ማወቅ፣ እንዴትስ መመለስ ይቻላል፣ ምን አይነት መቆጣጠሪያ ዘዴ መጠቀም ያስፈልጋል የሚሉ ጥያቄዎችን በመመለስ የመልሶ ማልማት ሥራ ካልተሠራ የሚደረጉ አዲስ ሠፈራዎች ጊዜያዊ እንጂ ዘላቂ መፍትሔ የሚያመጡ አለመሆናቸውን ይጠቁማሉ፡፡ ለዚህም ማሳያው አሁን የታዩ ችግሮች ከመቶ እና ከ50 ዓመታት በፊት የሰው ሰራሽ ችግሮች ውጤት መሆናቸው ነው፡፡
አብዛኛው የኢትዮጵያ ክፍል ተራራማና በሰው ሰራሽ አደጋ የተጠቃ በመሆኑ ተጋላጭነቱን ለመቀነስ ዘላቂ የተፈጥሮ ሀብት መከላከያ ዜዴዎች መጠቀም ያስፈልጋል ባይም ናቸው፡፡ በቅርቡ በኢትዮጵያ የተከሰተው የመሬት መንሸራተት በከፍተኛ ደረጃ ብዙ የሀገሪቱ አካባቢዎች ያጥለቀለቀና ተጽዕኖውም ከባድ ጉዳት ያመጣ ከመሆኑም በላይ ሰው ሰራሽ ችግሮቹ የተፈጥሮን ችግር እያባባሱት እየሄዱ እንደሆነ የሚያመላክት ነውም ይላሉ፡፡
የተፈጥሮ ዛፎች አፈርን አጣብቆ መያዝና የሚዘንበው ዝናብ መጥኖ ወደ አፈር እንዲሰርግ የማድረግ አቅም በማጎልበት የተፈጥሮን ሚዛናዊነት ይበልጥ መጠበቅ ይችላሉ የሚሉት ፕሮፌሰር መሀመድ፤ አሁን በተለያዩ አካባቢዎች እየተከሰተ የሚገኘው የአፈር መሸርሸርና የመሬት መንሸራተት አንዱ መንስኤ የተፈጥሮ ደኖች መመናመን መሆኑን ይገልጻሉ፡፡
መፍትሔውም አስቀድሞ የመመከላከል ሥራ በትኩረት መሥራት፣ተፈጥሮን ያገናዘበ የሕዝብ ሠፈራ ማከናወን፣ ለልማት የሚውሉ መሬቶች በየዘርፋቸው በመክፈል ዘመናዊ የመሬት አጠቃቀም ሥርዓት ማበጀት፣ መሬትን በተለያ ዘዴዎች ማከም እንዲሁም የተፈጥሮ ደኖች በብዛት እንዲተከሉ ማድረግ ተገቢ ነው፡፡
በኢትዮጵያ እንደ አውሮፓያውያኑ የዘመን ቀመር ከ1960ዎቹ ጀምሮ በመሬትና መሬት ነክ ጉዳዮች የተለያዩ ጥናቶችና ሪፖርቶች ቢደረጉም የፖሊሲ አውጪዎች ግብዓቱን ወስደው በትክክል ስላልተረጎሙት፣ ፖሊሲውም ተግባራዊ ማድረግ ባለመቻሉ እንዲሁም በቅንጅት ባለመሠራቱ ችግሮቹ ይበልጥ እየጨመሩ መምጣታቸውን ያክላሉ፡፡
ማሌዢያ ከኢትዮጵያ የበለጠ በተፈጥሮ ለመሰል አደጋዎች ተጋላጭ ብትሆንም የተቀናጀ ሥራ በመስራቷ አደጋውን መቆጣጠርና አልፎ አልፎ የሚከሰተውንም እንዳይስፋፋ ማድረግ እንደቻለች ይናገራሉ፡፡
ወደፊትም በኢትዮጵያ ችግሩን አስቀድሞ የመከላከል፣ አደጋ የደረሰባቸው ቦታዎች መልሶ ማልማት፣ ተፈጥሮን የመንከባከብ እንዲሁም ፖሊሲ አውጪውና ባለሙያው በቅንጅት መሥራት ካልቻሉ እየሰፋ ሄዶ የሚያደርሰው ተጽዕኖ ከፍተኛ ይሆናል የሚሉት የአፈር ሳይንስ ባለሙያው፤ እንክብካቤውም ለተወሰነ አካል የሚተው ባለመሆኑ ከህብረተሰቡ ጀምሮ ሁሉም በትብብር መሥራት እንዳለበትም ያብራራሉ፡፡
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የአካባቢ ጥበቃ ባለሙያ ዲሪባ ዳዲ(ረ/ፕ) በበኩላቸው ችግሩ በዘላቂነት ለመፍታት የኢትዮጵያን ሥነ-ምህዳር ያገናዘበ እንክብካቤ ማድረግና አሁን ለአደጋ ተጋላጭ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች ወደ ሌሎች ቦታዎች ማስፈር ይገባል፡፡
ከተለያዩ ኢንዱስትሪዎች የሚወጡና ከማህበረሰቡ የሚመነጩ ተረፈ ምርቶች በአግባቡ ባለመወገዳቸው የዓለም አየር ንብረት ለውጥ እንዲጨምርና ወቅቱ ያልጠበቀ የጊዜያት መለዋወጥ ድንገተኛ አደጋዎች እንዲከሰቱ እያስቻሉ መሆኑ ያስረዳሉ፡፡
እንደ ረዳት ፕሮፌሰር ዲሪባ ገለጻ፤ መጠኑ አነስተኛ እስከ ከፍተኛ የሆነ የመሬት መንሸራረተት መፈጠሩ ከከፍተኛ የሕዝብ ሰፈራና ለልማት የሚውሉ በታዎች በጥናት የተደረገፉ አለመሆናቸው ነው።
አደጋው ሊቀጥል የሚችልበት ብዙ አመላካች ሁኔታዎች በመኖራቸው ጥናቶች ተካሂደው የመሬት አገልግሎት አጠቃቀም ማዘመንና የአረንጓዴ ዐሻራ፣ እርከን ሥራ እንዲሁም ሌሎች የመሬት አጠባበቅ እንክብካቤዎች የበለጠ ማጠናከር አስፈላጊ ነው ይላሉ።
የአካባቢ ጥበቃ የሚሠሩ የልማት ሥራዎች የተረጋጋና ሰላማዊ አካባቢ ለመፍጠር ያላቸው ሚና ከፍተኛ ነው የሚሉት ረዳት ፕሮፌሰሩ፤ የግንዛቤ መፍጠር ሥራው በማጎልበት የተራቆጡ፣ ለብክለት ምክንያት የሆኑ ፋብሪካዎችና ሌሎች ተቋማት አስፈላጊውን የአካባቢ ጥበቃ ሥራ መሥራት እንዲችሉ ማድረግ እንዳለበት ያመላክታሉ፡፡
በተለይ ቆሻሻን በአግባቡ አለመያዝ የአካባቢውን የአየር ንብረት ለውጥ ከማባባስ ውጪ ኢኮኖሚዊ ተጠቃሚነት የሚያስቀር ነው ባይ ናቸው፡፡
ልጅዓለም ፍቅሬ
አዲስ ዘመን ነሐሴ 14 /2016 ዓ.ም
TIPS
Growing relations between Israel and Ethiopia: between military deals, intelligence influence, and an eye on Egypt
The Wars We Still Can Stop
Ethiopia: Israel Foreign Minister Says His Country Wants to Be Part of Ethiopia’s Success
A Nation Silenced: How the 1993 Referendum Stripped All Ethiopians of Their Sea
The 1976 TPLF Manifesto: TPLF’s “Republic of Greater Tigray”
Away from the global spotlight, Eritreans are trapped in a garrison state
Testimonials of a Sudanese Intelligence Officer on the Proxy war between Sudan and Ethiopia from 1970s to early 1990s
Ethiopia-Eritrea Tension: A Volatile History that Never Truly Ended – Could Assab Become Africa’s Crimea?
“As an outlier among the five tplf leaders, I wasn’t part of the armed struggle tradition”
Former Tigray fighters say no to war
Don’t Risk Your Future: The United States Cracks Down on Illegal Immigration
Counter-Video by EBC Challenges EBS Broadcast, Sparks Public Outcry Over Alleged Misinformation
Ethiopia and Eritrea Slide Closer to War amid Tigray Upheaval
Sea Outlet Serious and Unabated Agenda for Ethiopia: Retired Lieutenant General Yohannes
Israel’s Peace With Egypt Is Starting to Crack
Egyptian, Eritrean FMs reject involvement of non-bordering countries[Ethiopia] in Red Sea security