እንደ ሮያል የማህፀንና የጽንስና ሀኪሞች ኮሌጅ (RC0G) እና የአሜሪካ የጽንስና የማህፀን ሐኪሞች ኮሌጅ (ACOG) ካሉ ድርጅቶች የተሰጡ መደበኛ የሕክምና መመሪያዎች እንደዋና የህክምና መመርያ መከተል እና ለሚሰጡ ህክምናዎች ከነዚህ መመርያዎች አለመራቅ በመላው አለም የሚመከር ሲሆን ሁለቱም የህክምና መመርያዎች በእርግዝና ወቅት ፓፓያ አለመብላትን አይመክሩም።
በተቃራኒው በእነዚህ መመሪያዎች መሰረት በአጠቃላይ በእርግዝና ወቅት ሁለቱንም መመገብ ደህንነቱ የተጠበቀ መሆኑን በግልፅ ያሳያሉ።
✅ የበሰለ ፓፓያ ጥቅሞች
በቫይታሚን ኤ፣ ቢ እና ሲ እንዲሁም ቤታ ካሮቲን፣ ቾሊን፣ ፋይበር የበለፀገ ነው። የበሰለ ፓፓያ በእርግዝና ወቅት ብቻ ሳይሆን በተለይም እንደ የሆድ ድርቀት ያሉ የምግብ መፈጨት ችግሮችን ለመፍታት ጠቃሚ መሆኑን የተመሠከረለት ነው።
✅ ያልበሰለ ፓፓያ በእርግዝና መጠቀም የሚያስከትለውን ጉዳት።
ያልበሰለ ፓፓያ የላቴክስ እና ፔፒን በውስጡ የያዘ ሲሆን ይህም የማኅፀን መኮማተር፣ ደም መፍሰስ እና የፅንስ ከረጢት ከማህፀን እንዲለይ ያደርጋል። የእነዚህ ንጥረ ነገሮች ተጽእኖ ከሰው ወደ ሰው ሊለያይ ይችላል ነገርግን በአጠቃላይ በእርግዝና ወቅት ያልበሰሉ ፓፓያዎችን ከመጠቀም መቆጠብ ሊያስከትሉ የሚችሉ ችግሮችን ለማስወገድ ይመከራል።
✅ አናናስ በእርግዝና ወቅት ጎጂ ነው የሚለውን የተሳሳተ ግንዛቤ ማብራሪያ
ይህም ህመምን፣ ደም መፍሰስን ወይም ያለጊዜ ምጥ ሊፈጥር ይችላል የሚለው የተዛባ ነው። አናናስ የፕሮቲን ትስስርን የሚሰብር ብሮሜሊን የተባለ ኢንዛይም በውስጡ ቢይዝም በቫይታሚን ሲ፣ ፋይበር እና አንቲኦክሲዳንትስ ምክንያት ደህንነቱ የተጠበቀ እና ጠቃሚ ነው። ከመጠን በላይ መመገብ ወደ አሲድነት ወይም ወደ ቃር ሊያመራ ይችላል። አናናስን በአመጋገብ ውስጥ ማካተት እና በእርግዝና ወቅት ለተመጣጣኝ አመጋገብ አስተዋፅኦ ያደርጋል ፣ ይመከራል።
ዶ/ር ትዕዛዙ ዓለሙ (የማህፀን እና ፅንስ ስፔሻሊስት)
ለመረጃ- 0939011402
Hakim