በፎቶው የምናያቸው ጄኔቫ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ሰራተኞች ናቸው። ይህን ፎቶ የተነሱት በዘመነ ደረግ በጄኔቫ የኢትዮጵያ አምባሳደር የነበሩት ከሳ ከበደ ለኢትዮጵያ አምባሳደሮች መኖሪያ እንዲሆን በጄኔቫ ከተባበሩት መንግሥታት ቢሮ በቅርብ ርቀት ላይ በዘመነ ደርግ የገዙት ትልቅ ቪላ ያለው ሰፊ ግቢ ውስጥ ነው።
አምባሳደር ካሳ ከበደ ይሄንን ቤት ሲገዙ ከኢትዮጵያ ሕዝብ በተዘረፈ ገንዘብ መንግሥቱ ኃይለማርያም ሥልጣኑን ሲያጣ በስደት የሚጠለልበት ቪላ በሥሙ ገዙለት ተብለው በወቅቱ የተቃዋሚ ሬድዮ ጣቢያዎች በቪኦኤና መሰል ትላልቅ ተቋማት ጭምር የሥም ማጥፋት ዘመቻ ተከፍቶባቸው ነበር።
በወቅቱ ቪኦኤ ላይ ጭምር ቀርበው ቤቱ የተገዛው ኢትዮጵያ ለአምባሳደሮች መኖሪያ ቤት ኪራይ የምታወጣውን ወጪ ለማስቀረት እና ዶላር ለመቆጠብ መሆኑን እና ንብረትነቱም የኢትዮጵያ መንግሥት እንጂ በመንግሥቱም ሆነ በሌላ ግለሰብ ሥም የተገዛ አለመሆኑን ለማስረዳት ብዙ ቢጣጣሩም በተቃዋሚ ፕሮፓጋንዳ ተደፍቀው ሰሚ አላገኙም ነበር።
እነሆ ዛሬ ታሪክ የሳቸውን ዕውነት እና የተቃዋሚ ፕሮፓጋንዲስቶችን ቅጥፈት መስክራለች ። ዛሬ ላይ ይህ ቤት በወቅቱ የተገዛበትን ዋጋ ብዙ ዕጥፍ የሚያወጣ ዋጋ ሲኖረው ላለፉት 35 ዓመታት ኢትዮጵያ ለአምባሳደሮች መኖሪያ ታወጣ የነበረውን በሚሊዮኖች የሚቆጠር ዶላርም ማዳን ችሏል።
እነዚህ የኤምባሲ ሰራተኞች ይህን ፎቶ የተነሱት ዛሬ በአንድ ጀምበር 600 ሚሊዮን ችግኝ የመትከልን ሀገራዊ ዘመቻ በመደገፍ በዚህ የአምባሳደሩ ግቢ የችግኝ ተከላ አካሂደው ከጨረሱ በሁዋላ ነው።
የምትሰራው ነገር ለሀገር እንደሚጠቅም እርግጠኛ ከሆንክ ወቅታዊ የመንጋ ጩኸት ሳይበግርህ አድርገው።
ዳኛው ጊዜ፣ ዳኛው ታሪክ፣ ዳኛው የነገ ትውልድ !!
via, አብነት
TIPS
The Wars We Still Can Stop
Ethiopia: Israel Foreign Minister Says His Country Wants to Be Part of Ethiopia’s Success
A Nation Silenced: How the 1993 Referendum Stripped All Ethiopians of Their Sea
The 1976 TPLF Manifesto: TPLF’s “Republic of Greater Tigray”
Away from the global spotlight, Eritreans are trapped in a garrison state
Testimonials of a Sudanese Intelligence Officer on the Proxy war between Sudan and Ethiopia from 1970s to early 1990s
Ethiopia-Eritrea Tension: A Volatile History that Never Truly Ended – Could Assab Become Africa’s Crimea?
“As an outlier among the five tplf leaders, I wasn’t part of the armed struggle tradition”
Former Tigray fighters say no to war
Don’t Risk Your Future: The United States Cracks Down on Illegal Immigration
Counter-Video by EBC Challenges EBS Broadcast, Sparks Public Outcry Over Alleged Misinformation
Ethiopia and Eritrea Slide Closer to War amid Tigray Upheaval
Sea Outlet Serious and Unabated Agenda for Ethiopia: Retired Lieutenant General Yohannes
Israel’s Peace With Egypt Is Starting to Crack
Egyptian, Eritrean FMs reject involvement of non-bordering countries[Ethiopia] in Red Sea security
Ethiopia, Creditors Agree on $8.4 Billion Debt Restructuring