የሽግግር ፍትሕ ትግበራ ፍኖተ-ካርታ ዝግጅት መጠናቀቅና የሕግ ማዕቀፎች ዝግጅት ሂደትን አስመልክቶ ከፍትሕ ሚኒስቴር የተሰጠ መግለጫ
የኢፈዱሪ የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ ሚያዝያ 9 ቀን 2016 ዓ.ም በሚኒስትሮች ምክር ቤት መፅደቁን ተከትሎ ፖሊሲውን ወደ ትግበራ ምዕራፍ ለማሸጋገር የሚረዱ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ሲከናወኑ ቆይተዋል፡፡ ከነዚህ ስራዎች መካከል አንዱ የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲውን አፈፃፀም፡ ክትትልና ድጋፍ ሥርዓት የሚመራ ፍኖተ ካርታ ማዘጋጀት ሲሆን – አሁን ላይ የፍኖተ ካርታው ዝግጅት ተጠናቆ ወደ ስራ እንዲገባ ተደርጓል።
በሌላ በኩል የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲው ካስቀመጣቸው ጉዳዮች እንዱ የሽግግር ፍትሕ ስልቶችን የሚተገብሩ ነጻና ገለልተኛ ተቋማት ለማቋቋምና ለማደራጀት የሚያስፈልጉ የተለያዩ የሕግ ማዕቀፎች ዝግጅትን የሚመለከት ነው።
በዚህ መሰረት የዓለም አቀፍ ወንጀሎችን የሚደነግግ አዋጅ፣ የእውነት፣ ምህረት እና ማካካሻ ኮሚሽን ማቋቋሚያ አዋጅ እና የሌሎች የሽግግር ፍትሕ አላባዎች ፈፃሚ ተቋማት ማቋቋሚያ አዋጆችን የማርቀቅ ስራ እየተሳለጠ ነው፡፡ በተጨማሪም በሽግግር ፍትሕ ማዕቀፍ የወንጀል ጉዳዮችን የሚያየው ልዩ ችሎት ስልጣንና አሰራርን የሚመሰርተው የሽግግር ፍትሕ ልዩ ችሎት አዋጅ ዝግጅት በፈዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አስተባባሪነት የሚከናወን ይሆናል።
የሕግ ማዕቀፎቹ ዝግጅት በጉዳዩ ላይ በቂ እውቀትና ልምድ ባላቸው ባለሙያዎች የሚካሄድ ሲሆን፤ አጠቃላይ ሂደቱ በሁለት ወር ጊዜ ውስጥ የሚጠናቀቅ ይሆናል። የሕግ ማርቀቅ ስራው እንደተገባደደ ህዝቡና ባለድርሻ አካላት ዝርዝር አስተያየት የሚሰጡባቸው አገር አቀፍ እና ዓለም አቀፍ መድረኮች የሚዘጋጁ ይሆናል።
የነዚህ ሕጎች በፍጥነት መውጣት በፖሊሲው ላይ የተመላከቱትን ዓላማዎች ለማሳካት በተለይም የተለያዩ የሽግግር ፍትሕ ስልቶችን በመጠቀም እውነት ለማውጣት፣ እርቅ የሚወርድበትን አሰራር ለመመስረት፣ የወንጀል ተጠያቂነትን ለማሰፈን፣ በቅድመ ሁኔታ ላይ የተመሰረተ ምህረትን ተግባራዊ ለማድረግ፣ የማካካሻና ተቋማዊ ማሻሻያ ስራዎችን ለማከናወን እና በአጠቃላይ የተሟላ ፍትሕ ለማስፈን ቁልፍ ሚና ይጫወታል።
የሽግግር ፍትሕ የተቋማት ቅንጅታዊ አመራር መድረክ ሴክሬታሪያት
አዲስ አበባ
ነሐሴ 13 ቀን 2016 ዓም
TIPS
Growing relations between Israel and Ethiopia: between military deals, intelligence influence, and an eye on Egypt
The Wars We Still Can Stop
Ethiopia: Israel Foreign Minister Says His Country Wants to Be Part of Ethiopia’s Success
A Nation Silenced: How the 1993 Referendum Stripped All Ethiopians of Their Sea
The 1976 TPLF Manifesto: TPLF’s “Republic of Greater Tigray”
Away from the global spotlight, Eritreans are trapped in a garrison state
Testimonials of a Sudanese Intelligence Officer on the Proxy war between Sudan and Ethiopia from 1970s to early 1990s
Ethiopia-Eritrea Tension: A Volatile History that Never Truly Ended – Could Assab Become Africa’s Crimea?
“As an outlier among the five tplf leaders, I wasn’t part of the armed struggle tradition”
Former Tigray fighters say no to war
Don’t Risk Your Future: The United States Cracks Down on Illegal Immigration
Counter-Video by EBC Challenges EBS Broadcast, Sparks Public Outcry Over Alleged Misinformation
Ethiopia and Eritrea Slide Closer to War amid Tigray Upheaval
Sea Outlet Serious and Unabated Agenda for Ethiopia: Retired Lieutenant General Yohannes
Israel’s Peace With Egypt Is Starting to Crack
Egyptian, Eritrean FMs reject involvement of non-bordering countries[Ethiopia] in Red Sea security