ሶማሊያ የኢትዮጵያን ተቃዋሚዎች እንደምታስታጥቅ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ በኩል በገሃድ ከተናገረች በሁውላ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነበዩ ተድላ የሶማሌያን ባለስልጣናት “የመንግስት ስልታን ጭንብል ያተለቁ የአልሸባብ ታጣቂዎች” በማለት ንግግራቸው አስቂኝ መሆኑን ጠቅሰው ማጣፊያ መልዕክት አስተላልፈዋል።
ኢትዮጵያ በቅርቡ ከሶማሊላንድ ጋር ያደረገችውን ስምምነት ወደ ተግባር የምትቀይር ከሆነ ምን እንደሚከተል ሲያስረዱ የሶማሊያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አህመድ ሞአሊም ፊቂስ አገራቸው ከኢትዮጵያን ተቃዋሚ ሃይሎች ጋር ግንኙነት እንደምትፈጥርና እንደምታስታጥቅ በይፋ በመግለጽ ነው ያስረዱት። ኢትዮጵያም “ያስቃል”ያለችው ይህንኑ ነው።
“Somalia may consider establishing contacts with and supporting rebels fighting the Ethiopian government if Ethiopia proceeds with its recently signed agreement with Somaliland” Fiqi’s comments were made during an interview with Universal TV.
ይህን ተከትሎ የተለያዩ አደረጃጀቶችና ሚዲያዎች “ሀሰን ሼክ ሶማሊያን ለመምራት ከሽፈዋል። ስልጣን እንዲለቁ ማድረግ የገባል” ሲሉ ተደምጠዋል።
በኢትዮጵያ እና በሶማሌ ላንድ መካከል የመግባቢያ ስምምነት ከተፈረመ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የዳሮድ ፖለቲከኞች፣ ተንታኞች እና ሚዲያዎች የሀሰን ሼክ እና የሃውዌ መንግስት ከሞቃዲሾ ስልጣን እንዲለቁ ጥሪ ማቅረባቸውን አስታውሰው። “ሀሰን ሶማሊያን ለመምራት ሙሉ በሙሉ ወድቋል” ከሚል ድምዳሜ ደርሰዋል።
For the first time since the MOU between Ethiopia and Somaliland was signed, Darod politicians, analysts, and media have begun calling for the resignation of Hassan Sheikh and the Hawiye regime in Muqdishu. According to them, Hassan has utterly failed in leading Somalia. Rather than building an inclusive, broad-based government that represents all Somali tribes, he has instead chosen to surround himself his Hawiye clan and build a regime dominated entirely by the Hawiye, that is confined to Hawiye inhabited towns and villages.
“የአልሸባብ ታጣቂዎች የመንግስት ባለስልጣናት ጭምብል ለብሰው፣ ከባይናዲ ውጪ መንቀሳቀስ የማይችሉ፣ በጠባብ ጎሳዊ ጥቅም ላይ የተመሰረተ ባዶ በብሄርተኝነት የታጀለ ጠባብ ስብከት ሲሰብኩ ማየት ያስቃል። እንዲህ ያለው ማላዘን ለዓመታት መሻሻል የታየበትን የሶማልያ ሁኔታ መልሶ መቅመቅ ከመክተትና ሶማሌን መልሶ ቀውስ ውስጥ ከመጨመር የዘለለ ፋይዳ የለውም” ሲሉ ምላሽ የሰጡት ቃለ አቀባዩ ባለስልጣኖቹን ጭንብል የለበሱ አልሸባቦች ያሉዋቸው ቀደም ሲል ከነበራቸው የጀርባ ታሪክ በመነሳት እንደሆነ በግል አስተያይታቸውን የሳፉ ጥቂት አይደሉም።፡
ሀሰን ሼክ የግብጽን አጀንዳ ለምግዛትና የኤርትራን ስጋት ለመጋራት ብለው የገቡበት ጣጣ ከመቅመቻቸው ሊፈነቅላቸው እንደሚችል ከወዲሁ የሶማሌ የሚዲያ ሰዎች እየተናገሩ ነው። እሳቸውም ከወዲሁ በፍርሃቻ በጎሳ ላይ ተመስርተው ሚዲያዎችን በመጥራት መንግታቸውን የሚጠሉ ያሉዋቸው ላይ በፕሮፓጋንዳ ዘመቻቸው እንዲያግዟቸው ተማጽነዋል። የሚዲያ ማዕቀብም አድረገዋል።
በቴሌግራም ይከተሉን እባክዎ https://t.me/+f_kxmaPjD-9jYTdk