ኤርትራ፣ ግብጽና ሶማሊያ በአንድነት ግንባር ፈጥረው ኢትዮጵያ ላይ እንዲረባረቡ ያደረጋቸው የባህር በር ቅድመ ስምምነት በቀጣዩ ሳምንት በአዲስ አበባ በውል ታስሮ እንደሚፈረም የኢትዮሪቪው ዲፕሎማቲክ ምንጮች አስታወቁ። የስማሊላንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከተመድ ስብሰባ ጎን በዚሁ ጉዳይ ከአሜሪካ ጋር እየመከሩ ነው። የስምምነቱ ህግ ዝግጅት ተጠናቀቀ።
እንደ መረጃው ከሆነ የመግባቢያ ሰነዱን ለመፈራረም የሶማሊላንድ ፕሬዚዳንት ሙሴቢሂ አብዲ በሚቀጥለው ሳምንት መጨረሻ አዲስ አበባ ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል። ፕሬዚዳንቱ አዲስ አበባ መግባታቸውን ተከትሎ የፊርማ ስነ ስርዓቱ በይፋ ለህዝብና ለዓለም እንደሚበሰር ለማወቅ ተችሏል።
ከዚሁ ጉዳይ ጋር በተያያዘ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ኢሳ ኪያዲ ይህ እስከተዘገበ ድረስ ላለፉት ሶስት ቀናት ከተመድ ስብሰባ ጎን ለጎን በአሜሪካ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እየመከሩ እንደሆነ የዜናው ሰዎች አረጋግጠዋል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በኢትዮጵያ አዲስ ዓመት ዋዜማ ስምምነቱ በማለሙያዎች ተዘጋጅቶ መጠናቀቁን አመልክተው በቅርብ፣ በሳምንታት ውስጥ እንደሚፈረም ማስታውቃቸው አይዘነጋም።
ኤርትራንና ግብጽን እንዳበሳጨው ሁሉ ዜናን እንደሰሙ ተቃውሞ ያሰሙ በዜግነት ኢትዮጵያዊ የሆኑ የሚዲያ አስተዳዳሪዎችና የማህበራዊ ሚዲያ ሰልፈኞች ፊርማው ሲፈረም ምን እንደሚሉ ለማየት መጓጓታቸውን ዜናውን ያካፈሉን ገልጸዋል።
ጅቡቲ በገሃድ ፈራ ተባ እያለች፣ አንዴ ወደብ አቅራቢ፣ ሌላ ጊዜ ደግሞ ደጋፊና ገድብ አስቀምጭ እየሆነች በምታንከስበት የሶማሊላንድና ኢትዮጵያ የባህር በር ስምምነት ኢትዮጵያ ውስጥ እርሻን ጨምሮ ሰፊ ሃብት ያላቸው ፕሬዚዳንቷ ከሶማሊላንድ ጋር በሚያዋስናቸው ግዛታቸው አልሰቤህ የገደቡሲንና መማስ ጎሳዎችን እያሰለጠነች እንደሆነ በተለያዩ መገናኛዎች መገለጹ ይታወሳል።
“የፈረሰች አገር” የምትባለው ሶማሊያ በኢትዮጵያ ወታደሮች እየተጠበቀች፣ ኢትዮጵያ ላይ የጦርነት ዛቻ ብትፈጽምም፣ ግብጽ አጋጣሚውን ተጠቅማ ወታደርና መሳሪያ ብታጓጉዝም ፊርማውን ሊያስቀር የሚችል ጉዳይ አለመኖሩን የዜናው ሰዎች ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ከሶማሊያም ሆነ ከግብጽ ይሰነዘራል ብላ የምትፈራው አንዳችም ነገር እንደሌለ አክለው አስታውቀዋል።
ከአምስቱ የሶማሊያ ስቴቶች ሶስቱ ማለትም ጁባ ላንድ፣ ሳውዝ ዌስትና ፑንት ላንድ ከኢትዮጵያ ወገን ሲሆኑ፣ ሁለቱ የሃዊዬ (ሃሰን ሼክ የተወለዱበት ጎሳ)ና የሄሪንና ሃርቲሼክ ጎሳዎች ከሞቃዲሾው መንግስት ወገን ናቸው።
“ላለፉት ሰለሳ ዓመትት በላይ ፈርሰን ግብስ የት ነበረች፣ ጦርነት አታምጡብን፣ የረዳችን ኢትዮጵያ ናት፣ ግብጽን አንፈልግም” በማለት የሳውዝ ዊውስት አገር ሽማግሌዎች ለሶማሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃምዛ አብዲ ባሬ በገሃድ መናገራቸውን የአካባቢው ሚዲያዎች ዘግበዋል። ሚኒስትሩ ባይደዋ የሳውዝ ዌስት ዋና ከተማ ለማግባባትና አቋም ለማስቀየር አምስት ሰዓታት የፈጀ ውይይት ቢያደርጉም እንዳልተሳካላቸው ውይይቱን ከተከታተሉና ከዘገቡ ሚዲያዎች ለመረዳት ትችሏል።