በትብብር የአፍሪካ አምስት አገሮች እየጠበቁ ያጸኑት የሶማሊያ መንግስት ኢትዮጵያ ላይ ጫና ለማድረስ ደፋ ቀና በሚልበት ወቅት ከኢትዮጵያ ድንበርና በርበራ ወደብን የሚያገናኘው የአስፓልት መንገድ ተጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት መሆኑ ተሰማ።
ኢንሳይድ አፍሪካ እንዳለው 234 ኪሜ ርዝመት ያለው ይህ መንገድ የተገነባው በ400 ሚሊዮን ዶላር ከኤምሬትስ በተገኘ እርዳታ ነው። በሰበር ዜና ታጅቦ ተገለጸው ይህ የአስፓልት ኮንክሬት ግንባታ ጅቡቲን ማስደንገጡና ጭንቀት መፈጠሩ ተመልክቷል። የኢትዮጵያን የውጭ ንግድ 90 በመቶ ያሳድገዋል የተባለው የበርበራ ወደብ ጅቡቲ በየዓመቱ የምትዘርፈውን ሶስት ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ የኢትዮጵያን አንጡራ ሃብት የሚያመናምነው አዲሱ ወደብ ላይ ለኢትዮጵያ ትልቅ አማራጭ እንደሆነ በስፋት ሲነገር መቆየቱ ይታወሳል።
የበርበራ ወደብ መከፈት ዜና ከመሆኑ ቀናት በፊት፣ ጅቡቲ የታጁረን ወደብ ኢትዮጵያ ሙሉ በሙሉ እንድትጠቀምበት መፍቀዷን ማስታወቋ ትኩረት አፍሪካን ጠቅሰን መዘገባችን አይዘነጋም።
ከኢትዮጵያ ድንበር እስከ በርበራ ወደብ የተገነባው ይህ ደረጃውን የጠበቀ የየአስፋልት ኮንክሪት መንገድ ሙሉለሙሉ ተጠናቆ ወደስራ መግባቱ ሶማሊላንድ ከኢትዮጵያ ጋር የጀመረችው የባህር በር ስምምነት ካደረገች በሁዋላ በተነሳው አምባ ጓሮ ውስጥ መሆኑ ስምምነቱ እንደማይቀለበስ የሚያረጋግጥ እንደሆነ ማሳያ ነው ተብሏል።

የአስፓልት ግንባታው ብቻ ሳይሆን፣ ኢትዮጵያ ወደ ምትረከበው አዲሱ ወደብ ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ጭነት ማስተላለፊያ መስመር ዝርጋታ እየተጣደፈ መሆኑም ተመልክቷል። ኢትዮ-ቴሌኮም የአምስተኛው ትውልድ ቴክኖሎጂ በፍጥነት እየገነባ መሆኑ አብሮ ተመልክቷል።
በሌላ ዜና በኢትዮጵያ ታሪካው ጠላት ግብጽ የሚመራው የሞቃዲሾው መንግስት ኤርትራን አስከትሎ ኢትዮጵያን ለማተራመስ እንቅስቅሴ መጀመሩን ተከትሎ ከውስጥ ተቃውሞ እየተነሳበት መሆኑ ከተለያዩ ሚዲያዎች ተሰምቷል።
በሱማሊያ ካሉት ስድስት ስቴቶች በአምስቱ የግብፅ ሰራዊት የሶማሊያን ምድር መርገጡን በመቃወም የተቃውሞ ድምፅ እያሰሙ ነው።
ፕሬዚዳንቱ ሀሰን ሼክ መሐመድ የተነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ ከሀገሪቱ ከፍተኛ የፀጥታ ሃላፊዎች ጋር መምከራቸውን በምስል የተደገፉ ዘገባዎች አመልክተዋል።
ሃሰን ሼክ ኢትዮጵያ ላይ የጀመሩት የውክልና ዘመቻ ኢትዮጵያ በጥብቅ እየተከታተለችው እንደሆነ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ታዬ አቅጸስላሴ ማስታወቃቸው ጠቅሰን መዘገባችን ይታወሳል። እሳቸው እንዳሉት ኢትዮጵያ ለሶማሊያ ያጎደለችባት እንድም ነገር የለም። ዳሩ ባለስልጣኖቹ የኢትዮጵያን ታሪካዊ ጠላት አገራቸው በማስገባት ኢትዮጵያ እንድትተራመስ እያደረጉ ያለው ሙከራ አስፈላጊ ምላሽ እንደሚሰጠው የገለጸችው ኢትዮጵያ፣ ከዚያ በፊት ግን በሰላም በውይይት ሁሉንም ጉዳይ መነጋገር እንደሚበጅ፣ አሸባሪዎችን አብሮ መታገል የተሻለ አነደሚሆን አሳስባለች።
ኢትዮሪቪወን በቴሌግራም ይከተሉ https://t.me/+f_kxmaPjD-9jYTdk