የአሜሪካን መንግስት ልዩ መልዕክተኛ የሆኑት ማይክ ሀመር የትህነግ አመራሮች ልዩነቶቻቸውን በውይይት እንዲፈቱ አሳስበዋል። ሁሉም ወገኖች ለፕሪቶርያው ስምምነት ተፈጻሚነት ቁርጠኝነታቸውን እንዳረጋገጡላቸው አመልክተዋል።
የኢትዮጵያ መንግስት ባለስልታናትን የትግራይ ጊዜያዊ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጌታቸውን፣ ምክትላቸውን የቀድሞ ሌተናል ጄነራል ጻድቃንን እንዲሁም ዶ/ር ደብረጽዮንን ካነጋገሩ በሁዋላ ስምምነቱ ተጋራዊ እንዲሆን ሁሉም ወገኖች እንዳረጋገጡላቸው ማስታወቃቸው፣ የእነ ዶ/ር ድብረጽዮን ስምምነቱ አስመልክቶ ከፍላጎታቸው ውጪ መፈረሙን ጠቅሰው ሲሰጡ የነበረውን ዲስኩር መና አድርጎታል።
“ሁሉም የትግራይ ክልል ባለስልጣናት ለፕሪቶርያው የሰላም ስምምነት ተፈጻሚነት ቁርጠኛ መሆናቸውን ገልጸውልኛል” ሲሉ መስከረም 3 ቀን 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ይፋ እንዳደረጉት በሁለት ጎራ ተከፍለው የሚገኙት የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ አመራሮች ልዩነቶቻቸውን በውይይት እንዲፈቱም ልዩ መልዕክተኛው አሳስበዋል። “ልዩነቱ ምንም ይሁን ምን በውይይት እንዲፈቱ እናሳስባለን” ሲሉ ተድምጠዋል።
በያዝነው ሳምንት መጀመሪያ ቀናት ወደ መቀለ አምርተው የነበሩት ማይክ ሀመር በቆይታቸው ከክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳን አቶ ጌታቸው ረዳ እና ከህወሓቱ ሊቀመንበር ደብረጺዮን ገብረሚካኤል (ዶ/ር) ጋር መምከራቸውን ቀደም ሲል በኤምባሲው የኤክስ ገጽ፣ አሁን ደግሞ በአንድበታቸው ተናግረዋል። ሁለቱም መሪዎች ከማይክ ሀመር ጋር በነበራቸው ውይይት ለፕሪቶርያው የሰላም ስምምነት ተፈጻሚነት ያላቸውን ቁርጠኝነት እንደገለጹ ሐመር አመልክተዋል።
በጋዜጣዊ መግለጫቸው ሀገራቸው በአማራ እና ኦሮምያ ክልሎች ያለው ወቅታዊ ሁኔታ አሁንም እንደሚያሳስባት የገለጹት ማይክ ሀመር “ኢትዮጵያ ከማንም በላይ የአገዋ ተጠቃሚ እንድትሆን እንፈልጋለን፤ ነገር ግን ያስቀመጥነው ቅድመ ሁኔታ እና ህግ አለ” ሲሉ ጠቁመዋል፤ “የመንግስት ሃይሎች ምንም አይነት የሰብአዊ መብት ጥሰት በንጹሃን ላይ መፈጸም የለባቸውም” የሚል ቅድመ ሁኔታ መቀመጡን አስታውቀዋል።
አያይዘውም “በጣም የሚያሳዝነው ግን ብዙዎቻችሁ እንደዘገባችሁት አሁንም ግፍ እና በደል እየተፈፀመ ነው” ሲሉ አስታውቀው “እናም ይህ እስከቀጠለ ድረስ ኢትዮጵያ የአገዋ ተጠቃሚ መሆን አትችልም” ሲሉ ገልጸዋል። ግፍና በደል ያሉትን አላብራሩም። በተመሳሳይ ሌሎች ታጣቂዎች ስለሚፈጽሙት ግፍና በደል ያሉት ነገር የለም። ይልቁኑም ሀመር መንግስት ፈጸመ የሚሉት በደል መከላከያ እጁን አጣጥፎ ይቀመጥ ለማለት ይሁን ለሌላ መግለጫውን ተከታትለው የነበሩ በይፋ አልዘገቡም። ጥያቄው ስለመቀረቡም የተባለ ነገር የለም።
አሁን ላይ ህዝብ ከየአቅጣጫው እንደሚሰማው እጅግ ዘግናኝ ወንጀሎች እየተፈጸሙ ነው። በርካታ ግፋ በታጠቁ ሃይሎች መፈጸሙ ብቻ ሳይሆን በግልጽ ድልና ብስራት እየሆነ የሚቀርብበት ሁኔታ እያለ መንግስትን ብቻ በዚህ መፈረጁ ሰላም ለማምጣት ብዙም እንደማይሰራ በተደጋጋሚ የሚገለጽ ጉዳይ ነው።
በተመሳሳይ ዜና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ ከአሜሪካን የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ማይክ ሐመር ጋር በአፍሪካ ቀንድ ሰላም እና ፀጥታ ዙሪያ ተወያይተዋል።
አምባሳደር ታዬ፤ በ ሶማሊያ ከድህረ ከአፍሪካ ኅብረት የሽግግር ሰላም ማስከበር ተልዕኮ (አትሚስ) በሚኖረው የኃይል ስምሪት ዙሪያ ኢትዮጵያ ጥንቃቄ ይፈልጋሉ ያለቻቸውን ጉዳዮች ትኩረት ሰጥተው ማንሳታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ አመልክቷል። ኢትዮጵያ አሁን ላይ በቀጣናው ያለውን ውጥረት የማረገብ ሥራ እያከናወነች መሆኑንም አክለው ገልፀዋል።
አምባሳደሩ መንግሥት ለፕሪቶሪያው የሰላም ሥምምነት ሙሉ ተፈጻሚነት ያለውን ቁርጠኝነትም አስታውቀዋል ተብሏል። አምባሳደር ታዬ አሜሪካ የኢትዮጵያን የአጋዋ ጠቃሚነት እገዳ በማንሳት ወደ ቀድሞው ትግበራ እንድትመልስ ጥሪ አቅርበዋል።
የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ማይክ ሐመር መስከረም 3 ቀን 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ፣ “በኢትዮጵያ ግፍ እና በደል እየተፈፀመ ነው፤ ይህ እስከቀጠለ ድረስ ኢትዮጵያ የአገዋ ተጠቃሚ መሆን አትችልም” ሲሉ ገልጸዋል።
በሌላ ተመሳሳይ ዜና የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት ለሁለት ዓመት መቀጠሉን የሚደነቅ መሆኑን አመልክተው ለዘላቂነቱ ግን በተሟላ መልኩ ስምምነቱ መፈጸም አለበት ብለዋል።
የስምምነቱ ሁሉም ነጥቦች በተሟላ ሁኔታ መፈጸማቸውን ለማረጋገጥ ግን በጦርነት የተፈናቁ ሁሉ ደህንነት ተጠብቆ ወደ ቤታቸው እንዲመለሱ ትኩረት ማድረግ እንደሚገባ፣ የDDR የቀድሞ ተዋጊዎችን ትጥቅ ማስፈታት፣ መበተንና ወደ ማህበረሰቡ መልሶ ማዋሃድ መፈጸሙን ማረጋገጥና ዋና ዋና ጉዳዮችን በፖለቲካዊ ውይይት መፍታት አንገብጋቢ መሆኑን ገልሰዋል።
“አሜሪካ ለኢትዮጵያ ሉዓላዊነትና የግዛት አንድነት ድጋፍ ማድረጓን ትቀጥላለች። ከኢትዮጵያ ጋር ያለን ትብብር አስኳል ይሄ ነው” ሲሉ የተደመጡት ሐመር የትግራይ ተፈናቃዮችን የመመለስ ጅምር ስራ ቢኖርም አጥጋቢ እንዳልሆነ ጠቅሰው መጠናከር እንዳለበት አመልካተዋል።
አቶ ጌታቸው ሰሞኑን ለርዕዮት በሰጡት ቃለ ምልልስ የተፈናቀሉ ሰዎች እንዳይመለሱ አንዱና ዋናው እንቅፋት ተፈናቃዮች በሚመለሱበት ስፍራ “አስቀድመን አስተዳደር ከራሳችን መወከል አለብን” የሚሉ ከሕዝብ ስቃይ በላይ ስልታን የሚያሳስባቸው ሃይሎች ተፈናቃዮች በሚፈለገው ፍጥነት እንዳይመለሱ ማድረጉን ይፋ አድርገዋል። በመቶ ሺህ የሚቆተሩ ተፈናቃዮች ስቃይ ወደ ሁዋላ ተብሎ ስልጣን መጀመሪያ መጠየቁ እጅግ ያሳዘነና ያነጋገረ ጉዳይ ሆኖ መሰነበቱ ይታወሳል።
“የቀድሞ የትግራይ ታጣቂዎችን ትጥቅ ለማስፈታት፣ ለመበተንና ወደ ማህበረሰቡ ለመቀላቀል የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር አካላት ሙሉ ፍቃደኛ ናቸው። ተዋጊዎቹም ይሄን ይፈልጋሉ። ይህ ሂደት በፍጥነት መተግበር አለበት” ሲሉ ሃመር አስፈለጊውን ሁሉ ድጋፍ እንደሚያደርጉ ገልጸዋል።