ሀሰን ሼክ “የአስተዳደሬ ጠላቶች” ያሉዋቸውን ቡድኖችና ግለሰቦችላይ ሚደረገው የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ ሚዲያዎች በንቃት እንዲያሳተፉ ተማጽነዋል። በስብሰባው ላይ የተሳተፉትን ጠቅሰው መረጃውን በቲውተር ያሰራጩ እንዳሉት ይህ የፕሬዚዳንቱ አካሄደ ፕሬሱን በግጭቱ አውድ አሳቦ መጠቀሚያ የማድረግ ነው።
ሃሰን ሼክ ባለፈው ሐሙስ በዚላ ሶማሊያ ከተመረጡት የሚዲያ ዳይሬክተሮች ጋር የግል ስብሰባ አድርገዋል። ከየሚዲያዎቹ ዳይሬክተሮቹ የተመረጡት በጎሳቸው መሰረት መሆኑ ስጋት መፍጠሩ ተመልክቷል።እርምጃው የፕሬስ ነፃነት እና ግልጽነት ላይም ጥርጣሬ መፍጠሩን ስብሰባውን የተከታተሉት አመልክተዋል።
በውይይቱ ወቅት ፕሬዝደንት ሀሰን ለመገናኛ ብዙሃን ሃላፊዎች እንደተናገሩት መንግሥታቸውን “ጦርነት ገጥሞታል” ብለዋል።
“ጠላቶቻቸውን” ካሉ በሁዋላ አክለው “ጠላቶች እና ከኢትዮጵያ ጋር የተባበሩ” በማለት ያብራሩት ሀሰን ሼክ፣ “ጦርነት ውስጥ ነን” የሚለውን ሐረግ በመደጋገም የሁኔታውን ክብደት ለማሳየት ሞክረዋል።
ፕሬዝዳንቱ የመገናኛ ብዙሃን መንግስታቸው “የአስተዳደሩ ጠላቶች” ብሎ በፈረጃቸው ግለሰቦች እና ቡድኖች ላይ የሚያደርገውን የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ በንቃት እንዲደግፉ አሳስበዋል። ተሳታፊዎቹን የጠቀሱ በኤክስ ገጻቸው እንዳሉት ፕሬዚዳንቱ ግጭትን አንተርሰው ፕሬሱን ለፖለቲካ መጠቀሚያነት ለመቀየር ማሰባቸውን የሚያሳይ ምልክት እንደ አመልክተዋል።
አወዛጋቢ በሆነው የውይይቱ ክፍል ፕሬዝደንት ሀሰን ስለባኮ፣ ሂራዲ፣ ጌዲኦ እና ሶማሌላንድ ህዝቦች የሚያንኳስ አስተያየቶችን ሰጥተዋል ተብሏል፣ ይህም ቀድሞውንም በክልሎቹ መካከል በቋፍ ላይ የነበረው ውጥረት እንዲባባስ ማድረጉን እነዚሁ ወገኖች ጽፈዋል።
ስብሰባው የተካሄደው ፕሬዝዳንት አብዲአዚዝ ላፍታጋሬን በባይዶዋ አየር ማረፊያ ሞጋዲሹን በማውገዝ ንግግር ካደረጉ ከሁለት ቀናት በኋላ ነው። ይህ አካሄድ በፌዴራል ፓርላማ የታችኛው ምክር ቤት የሚዲያ ሽፋን ላይ ከተጣለው እገዳዎች ጋር የሚገጣጠም እንደሆነ ተገልጿል።
ባለፈው ሳምንት የፓርላማው የሚዲያ ዳይሬክተር በላከው መልእክት ጋዜጠኞች ከፕሬዚዳንት ሀሰን እና ከመስተዳድራቸው የተለየ አመለካከት ያላቸውን የፓርላማ አባላት ቃለ መጠይቅ እንዳያስተናግዱ፣ ወይም እንዳይቀርጹ እገዳ ተጥሎባቸው ነበር። ይህም በሶማሊያ ሀሳብን በነጻነት የመግለፅ አግባብን እያጠበበ በመሆኑ ሚዲያዎቹ ላይ ተጨማሪ ስጋት ፈጥሯል
ይህ በእንዲህ እንዳለ 10 ሺህ ሚሊሻ ወታደሮችን አሰልጥና በትግርኛ ሙዚቃ አጅባ ያስመረቀችው ኤርትራ ተገኝተው ሰልጣኞቹን ሲጎበኙና መፈክር ሲያሰሙ የሚያሳይ ምስል በኤርትራ መንግስት ደጋፊዎች ” እንኳን ደስ አላችሁ” ከሚል መልዕክት ጋር እየተሰራጨ ነው።
በቴሌግራም ይከተሉን እባክዎ https://t.me/+f_kxmaPjD-9jYTdk