የመረጃ እጥረት ካልሆነ በስተቀር ኢትዮጵያን መክበብ የሚችልም ሆነ የከበበ ኃይል እንደሌለ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ አስታወቁ። እንግሊዝ አገር የሚኖር የግብጽ ታዋቂ ጋዜጠኛ አልሲሲ በሶማሊያ ወታደር ማሰማራቱን በመግለጽ የሚጫወቱት ጨዋታ ጨበታ መሆኑን አመለከተ።
የኢትዮጵያ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ከሉዓላዊ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንደተናገሩት በአሁኑ ሰዓት ኢትዮጵያን መክበብ የሚችል ኃይል የለም። እሳቸው እንዳሉት እዛም እዚህም የሚናፈውሰው የከበባ ወሬ የመረጃ እጥረት ነው።
ቀደም ባሉት ጊዜያት ኢትዮጵያ ጠንካራ የመከላከያ ኃይል መገንባቷን፣ አመራሩ በተማሩ ኃይሎች የተዋቀረ መሆኑ፣ አደረጃጀቱ ቴክኖሎጂ ተኮር መሆኑ፣ ይፋ ባይገለጽም ዘመናዊ ትጥቅ የተላበሰ መደረጉ፣ ሁሉንም ዓይነት ሙያ የሚተገብሩ ባለሙያዎች ማፍራቱን በመጥቀስ ከፍተኛ የሰራዊቱ አመራሮች በተደጋጋሚ፣ በተለያዩ አጋጣሚዎች መናገራቸው ይታወሳል።
ከበባ ያደረጉት ግብጽና ኤርትራ ስለመሆናቸው፣ ኤርትራ ከሶማሌ ጋር እንደምትገናኝ ተጠቅሶ ለተጠየቁት፣ “ኤርትራ ከሶማሌያ ጋር መገናኘት መብቷ ነው” ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል። ከቃለ መልልሱ ተቀንጭቦ የተሰማው በዚህ የጄነራሉ ምላሽ ተከትሎ መንግስት ለኤርትራ ወታደራዊ አቋም ያለውን ምልከታ ያሰየ እንደሆነ አድርገው በርካቶች አስተያየት ሰጥተዋል።
የኤርትራ መንግስት ወታደር ወደ ሶማሊያ እንዲልክ ከግብጽ ጥያቄ ቀርቦለት ለጊዜው ዝግጁ እንዳልሆነ፣ ነገር ግን የሶማሊያን ወጣቶችን ማሰልጠኑን እንደሚገፋበት ማስታወቁን የሰሙ፣ የጄኔራሉ ግምገማ ያስኬዳል ባይ ናቸው።
በትግራይ ጦርነት ወቅት በተለይ በአዲግራትና አክሱም የተገደሉ የኤርትራ ወታደሮች ቁጥር ከፍተኛ መሆኑን ተከትሎ እስካሁን ቤተሰቦች መርዶ እንዳልተነገራቸው የአውሮፓ ነዋሪዎችን ጠቅሰን መዘገባችን ይታወሳል። በዘገባው የኤርትራ መንግስት የወታደር እጥረት እንዳለበትና ሽማግሌዎች ሳይቀሩ በተጥንቀቅ እንዲቆዩ ማዘዙ ተመልክቶ ነበር።
የኢትዮጵያ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ” መብቷ ነው” ሲሉ እንዳሻት በስምራቅ አፍሪቃ ብትንሸራሸር ኢትዮጵያን ቁብ እንደማይሰጣት መግለጻቸው ከላይ በተገለጸው ምክንያት ይሁን በሌላ ተጨማሪ መረጃዎች ስለመደገፉ ለጊዜው ይፋ የሆነው ቃለ ምልልስ አላስታወቀም። ሙሉ ቃለ ምልልሱ ዛሬ ማምሻውን በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 3 ሰዓት በሉዓላዊ ሚዲያ ይለቀቃል።
ተቀማጭነቱ እንግሊዝ የሆነው የግብጽ ጋዜጠኛ Kings of Abbay (KoA) ተተርጉሞ በቀረበው ቪዲዮ የግብጽ ፕሬዚዳንት አልሲሲ አጋጣሚን ለሚዲያ ግርግር የሚጠቀሙ ውሸታም መሆናቸውን ንግግራቸውን እያሰማ ሲተች ተሰምቷል። በአገራችን ሿሿ እንደሚባለው ዓይነት የሃሰት ወሬ ከግብጽ ሚዲያዎች እንደሚተላለፍ ሚዲያዎቹን እያሳየ የጠቆመው ይህ ጋዜጠኛ “ሶማሊያ ገቡ የተባሉ ወታደሮች የት አሉ? አሸንፈው ወደ ግብጽ ተመለሱ?” ሲል ያላግጣል።
በሶማሊያ አለ የተባለው የግብጽ ወታደሮች ውሸት መሆኑን ሲያስታውቅ “ፎቶ ተነስ፣ ፎቶውን አሰራጭ፣ ፕሮፓጋንዳ ስራ” የሚል ጨዋታ እየተጫወቱ እንደሆነ አመልክቷል። በሶማሊያ የሚገኙ የግብጽ ወታደሮች እንደሆኑ ተደርጎ የሚሰራጨውን ፎቶ አመልክቶ “ጎግል አድርጉና እዩ” ይልና ” ኮፍታው ግብጽ፣ ሱሪው ቦስኒያ፣ ኮቱ ሩሲያ …” ሆኖ ታገኙታላችሁ ሲል አልሲሲ ደረጃው የወረደ ውሸታም መሪ እንደሆነ አመልክቷል።
ሶማሊያ የአረብ ሊግ አባል አገር እንደሆነች ጠቅሰው አልሲሲ የተነናገሩትን ” ይህን ውሸታም አድምጡ” ብሎ ካሰማ በሁዋላ ” ሶማሊያ ቀይ መስመራችን ናት። ሶማሊያን የነካ ወዮለት ስትል የነበረው የት ገባ?” በማለት ጨዋታው ሁሉ ጨበታ መሆኑን ያክላል።
በሶማሊያ ወታደር ማስገባታቸው ሃሰት እንደሆነ ያመለከተው ይህ ጋዜጠኛ፣ አሁን ላይ ኢትዮጵያ አንድ ደረጃ ከፍ ማለቷን ተቅሶ ግብጽ ጉርሻዋን እንደተነጠቀች ገልጿል። ተራ ሲሉ አልሲሲ የገለጿይና አንድም አገር ዕውቅና እንዳልሰጣት አድርገው ያቀረቧት አገር ሶማሊላንድ የግብጽና የካልቸር ማዕከል ዘግታ ሰራተኞች ማባረሯን አንስቶ ” አንተ ያለህበትና የደረስክበት ደረጃ በናቅካቸው መበለጥ ነው” ብሏል።
“ፊልድ ማርሻል ብረሃኑ ጁላ ከበባ ማድረግ የሚችል ኃይል የለም። ከበባ የሚባል ነር የለም” ማለታቸው ውሃ የሚያነሳ ጉዳይ ሆኖ ተገኝቷል። በሶማሊያ ከሚገኙት አምስት ክልሎች ሶስቱ ከኢትዮጵያ ወገን መቆማቸው በተደጋጋሚ መገለጹ ይታወሳል።