መንግስት ሻዕቢያና ወያኔ በዱባይ በር ዘግተው ሲመክሩ ሙሉ መረጃ እንደነበረው ስማቸውን ለጊዜው መግለጽ ያልፈለጉና ለጉዳይ እጅግ ቅርብ የሆኑ ለኢትዮሪቪው ገለጹ። እንደ ገለጻው ከፕሪቶሪያው ስምምነት በሁዋላ መንግስት ከትህነግ ሰዎች ጋር በነበረው ስብሰባ ይህንኑ ጉዳይ አንስቶ የተሰወረ ጉዳይ እንደሌለ አስታውቋቸዋል።
ይህ የተሰማው የትህነግን መሰንተቅ ተከትሎ ሰሞኑን አንደኛው ወገን ሌላኛውን ለመክሰስና ለማስጠቆር ከሻዕቢያ ጋር በዱባይ ሲደረግ የነበረው ግንኙነት አጀንዳ መሆኑን ተከትሎ ነው። የዜናው ሰዎች እንደሚሉት የዱባዩ ግንኙነት አጀንዳ መሆኑ ቁብ የለውም። ምንም ዓይነት ፖለቲካዊ ፋይዳም ሆነ ስጋት የሚፈጥር አይደለም። ይልቁኑም ሌሎች ከሻእቢያ ጋር የሚሸረቡ ሽረባዎች አሉ። መንግስት በቅርብ የሚከታተላቸው በተጨባጭ መረጃ የተደገፉና አስፈላጊ ሲሆን ለህዝብ ይፋ የሚሆኑ መረጃዎች ስላሉ ነው አስቀድሞ ጩኸቱ የተመረጠው።
“አየር ላይ ያለ መንግስት” በሚል ትህነግ ሲዛበትበት የነበረው የለውጡ መንግስት በስለላ ተቋሙ ከፍተኛ በሚባል ደረጃ ማደጉን ለማይቀበሉት የትህነግ ሰዎች መንግስት መረጃው እንዳለው ሲያውቁ አስደንግጧቸው ነበር። ይህ ብቻ ሳይሆን ከተለያዩ አካላት ጋር የነበራቸው ግንኙነት ቦታ፣ ስምና አጀንዳው እየተጠቀሰ ሲነገራቸው ማመን ተስኗቸው ነበር። በተለይም ኤርትራ ድንበር ላይ የተደረገ አንድ ንግግር በተንቀሳቃሽ ምስል ተደግፎ ቀርቦላቸው አይናቸውን ማመን እንደተሳናቸው ዜናውን ያካፈሉን ገልጸዋል።
የሻዕቢያ አዛውንት ባለስልጣናት ኢንሳን በጎበኙበት ወቅት “ ይህ ኢትዮጵያ ነው” እስኪሉ ድረስ መገረማቸውን ጠቅሰን ዘግበን ነበር። ይህ በኤርትራ የጦር መኮንኖች የተደረገው የመሰነባበቻ የሚመስል ጉብኝት የኢትዮጵያን የመረጃ ተቋማት እድገት ቁልጭ አድርጎ ያሳየና ሙሉ በሙሉ ቴክኖሎጂ ጠገብ መሆኑ ጎብኚዎቹ አዛውንቶች ከሚረዱት በላይ እንደሆነባቸው ማብራሪያ ሲሰጡ ከነበሩ ቅርብ ሰዎች የተገኘውን መረጃ ጠቅሰን ማካፈላችንም አይዘነጋም።
ይህ በማስታወስ መረጃ ያቀበሉን እንዳሉት ዛሬ የትግራይ ህዝብ ነጻ አውጪ ግንባር ትህነግ ለሁለት ተሰንጥቆ ለመጠቋቆሪያ የሚጠቀምበት ጉዳይ መንግስት ለየትኛውም ዓይነት ግብዓት የማይጠቀምበት ዜና ነው። ከሻዕቢያ ጋር የጀመሩትን የውስጥ ለውስጥ ግንኙነት እንዲያቆሙ በወቅቱ መንግስት አሳስቦ ነበር። የመንግስት ማሳሰቢያ ወደሁዋላ በመግፋት ” ወንጀለኛ” ከሚሉት ሻዕቢያ ጋር ዳንኪራውን የቀጠሉበት እንዳሉ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ከትግራይ ህዝብ ወኪሎች ጋር ቀርበው ሲወያዩ ፍንጭ መስጠታቸውም አይዘነጋም። በዛው ንግግራቸው ዳግም ግጭት እንዳይነሳ በዲፕሎማሲ ጉዳዩን እንደሚይዙትም አመልክተው ነበር።
“ትህነግ እና የኤርትራ ባለስልጣናት ዱባይ ላይ ተገናኝተው መክረዋል” ተብለው የአሜሪካ የአፍሪቃ ቀንድ አምባሳደር ሐመር ሰሞኑን ተጠይቀው ሲመልሱ” እኛ የምንፈልገው ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ወደ ጦርነት አለመመለሳቸውን ነው” የሚል ምላሽ መስጠታቸው ነገሩን ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ምላሽ ጋር አስማምቶታል።
“የምንፈልገው አንዳቸው የሌላኛቸውን ግዛት ጥሰው አለመግባታቸውን ነው። ከተቻለ የአልጀርስ ስምምነት በተሟላ መልኩ ተግባራዊ እንዲሆን መርዳት እንፈልጋለን” ሲል ለቪኦኤ ያስታወቁት ሐመር፣ አቋማቸው መንግስት አቶ መለስ በህይወት እያሉ አስመራን ሊይዝ አፋፍ ላይ የነበረውን ጦር “ተመለስ” ብለው የፈረሙት የአልጀርስ ስምምነት እንዲተገበር ካለው የጸና ዕምነት ጋር የሚዛመድ ሆኗል።
ከላይ በዲፕሎአሲያዊ ቋንቋ ተንደርድረው፣ ወደ ዋናው ጥያቄ ምላሽ ” ስለዚህም በሁለቱ አካላት መካከል ውይይት ከተደረገ በማንኛውም አካል እየተፈጸመ ያለ የሰብዓዊ መብት ጥሰት በማስቆም በሁለቱም ሀገሮች መካከል ያለውን ግንኙነት በማሻሻል ላይ ያተኮረ መሆን አለበት” ሲሉ የትህነግ ስዎች በአገራት መካከል ሊደረግ የሚገባ ንግግር ውስጥ ገብቶ እያላቆጠ መሆኑን በሳሳ ቋንቋ ገልሰዋል። ይህ መረጃቸው ጉዳዩን ጠንቅቀው እንደሚያውቁት አመላካችም ሆኗል።
ሐመር ይህን ብቻ አላሉም። ለቪኦኤ ስለ ሰሞኑ የኢትዮጲያ ክንውናቸው ሲያስታውቁ፣ “አሜሪካ ለኢትዮጵያ ሉዓላዊነት እና የግዛት አንድነት ድጋፍ ማድረጓን ትቀጥላለች። ከኢትዮጵያ ጋር ያለን ትብብር አስኳል ይሄ ነው” ብለዋል። ይህ ንግግራቸው ኢትዮጵያና አሜሪካ በቀይባህር ላይ ጀምረውታል የተባለው አዲስ ህብረት እየደረጀ መሆኑን የሚያሳይ ሆኗል። ዜናው የአውሮፓ ህብረት “ኢትዮጵዮጵያ በአፍሪቃ ቀንድና በቀይ ባህር የአውሮፓ ቁልፍ ስትራቴጂክ አጋር ናት” ሲል ካስታወቀ ጋር ሲዳመር፣ ኢትዮጵያ በሶማሊላንድ የጦር ሰፈር ከመገንባቷ ጋር ሲያያዝ የሐመር ንግግር ትርጉሙ እንደሚገዝፍ አስተያየት እየተሰጠ ነው።
አሜሪካ የፋኖ ሃይሎች ወደ ሰላም እንዲመጡና ውይይት እንዲደረግ ጥረት እያደረገች መሆኑን፣ ጠረቱ ከሚዲያ ጀርባ እየተከናወነ እንደሚገኝ መግለጻቸውና የትህነግ ታጣቂዎች በአስቸኳይ ትጥቅ እንዲፈቱ እንዲደረግ እየተሰራ መሆኑን ማስታወቃቸው ሰላም ለሚናፍቁ ወገኖች መልካም የአዲስ ዓመት ዜና ሆኗል። ከኦነግ ታታቂዎችም ጋር ተጀምሮ የከሸፈው ንግግር እንደሚቀጥል ሐመር እግረ መነገዳቸውን ጠቁመዋል።
ለውጡ ይፋ ሲሆን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ” ከፍተኛና ዘመኑንን የሚዋጅ የመከላከያና የጸጥታ ኃይል ስንገነባ እንከበራለን። ተጸእኖ ፈጣሪም እንሆናለን” በሚል መናገራቸው የሚታወስ ነው።