በኮሪደር ልማት ኘላን የማይካተት ከመመሪያና አሠራር ዉጪ ስድስት መኖሪያና አንድ የንግድ ቤት ከሆቴል ባለቤት ጋር በመመሳተር በማስፈረስና ብድርድር የካሳ ግምት በማናር የመንግስትን ሃብት አሳልፎ በመስጠት ለግል ጥቃማቸው በማዋላቸው ሳቢያ ሲፈለጉ የነበሩት የመሬት ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ ሆቴል ውስጥ ተመሽገው መገኘታቸው ተሰማ። ሆን ብለው ከአገር እንደወጡ መረጃ አስነግረው ነበር ተብሏል። ስድስት ገቢዎች ቢሮ ሰራተኞች ታሰሩ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ልደታ ክፍለ ከተማ የመሬት ልማት ጽ/ቤት ተወካይ ኃላፊ የነበሩት አቶ ቴዎድሮስ ፀጋዬ በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው ሲፈለጉ እንደነበር አስቀድሞ መገለጹ ይታወሳል። የአዲስ አበባ የፀረ ሙስና ግብረ ሃይል ዛሬ ይፋ እንዳደረገው ተጠርጣሪውን በቁጥጥር ውለዋል።
ተጠርጣሪው በኮሪደር ልማት ሽፍን በማድረግ ከመንግስት አሰራር እና ውሳኔ ውጪ በመደራደር ባልተገባ መንገድ ለግል ጥቅም ለማግኘት ሲል የካሳ ግምት በማናር ውስን የሆነዉን የህዝብና የመንግስትን መሬት ከአሰራር ውጪ በማሰተላለፍ ለግለሰቦች አላስፈላጊ ጥቅም በማዋላቸው ሳቢያ ሲፈለጉ ነበር። መረጃው እንዳልመለከተው ተጠርጣሪው በዛሬው ዕለት ከተሸሸጉበት ሆቴል በቁጥጥር ሰር ውለዋል።
በቁጥጥር ስር የዋሉት ተጠርጣሪ አቶ ቴዎድሮስ ሆን ብለው “ከሀገር ውጪ ወጥዋል” በማስባል ክትትሉ እንዲላላ፣ የህግ ማስከበሩን እንዲስተጓልና የመርመራውን አቅጣጫ ለማሳት ሞክረዋል።
ተጠርጣሪው ከመጀመሪያው የህግ መተላለፍ በተጨማሪም በክ/ከተማው ወረዳ 4 ዉስጥ በኮሪደር ልማት ኘላን ውስጥ የማይካተት ከመመሪያና አሠራር ዉጪ 6 መኖሪያና አንድ የንግድ ቤት የሆነውን ከዋይልድ አፓርትመንት የተባለ ህንፃ ባለቤት ጋር ተመሳጥረው ቤቶቹን እንዲፈርሱ በማድረግ ለህንፃው ማስፋፊያ እንዲሆን የሰጡና የመንግስት ቤት ውስጥ ይኖሩ የነበሩ ግለሰቦች የእቃ የማጓጓዥያ ሳይከፈል እንዲነሱ በማድረጉ እንዲሁም ምትክ ቦታ እስጣቿለው በማለት አንደኛ ቦታ አስቀይርላቿለውና የተለያዩ የማጭበርበር ወንጀሎችን በማድረግ ህብረተሰቡ ሲያደናግርና ያልተገቡ ጥቅሞችን ሲያደርግ እንደነበረ የከንቲባ ጽሕፈት ቤት መረጃ ያመለክታል።
በተመሳሳይ የሌብነት ዜና በአዲስ አበበ ከተማ የታክስ ኦዲት ቡድን አስተባባሪ፣ ባለሙያዎች እና ደላሎች በሙስና ወንጀል እጅ ከፍንጅ ተይዘው በቁጥጥር ሥር ዋሉ የአዲስ አበበ ከተማ አስተዳዳር ገቢዎች ቢሮ ከፍተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት የታክስ ኦዲት ቡድን አስተባባሪ የሆኑት፦
1ኛ. አቶ ሃብታሙ ግዲሳ ጆቴ፣ 2ኛ. ስምረት ገ/እግዚአብሔር አሰፋ የከፍተኛ ግብር ከፋዮች የታክስ ኦዲት ከፍተኛ ኦፊሰር 3ኛ. አቶ ዮሴፍ ባቡ ሆራ የከፍተኛ ግብር ከፋዮች የታክስ ኦዲት ከፍተኛ ኦፊሰር፣ 4ኛ. አቶ አቤኔዘር ቶሎሳ ሙሉ የከፍተኛ ግብር ከፋዮች ታክስ ኦዲት ከፍተኛ ኦፊሰር፣ 5ኛ. አቶ ለሚ ሲሌ ከፍተኛ ግብር ከፋይ የታክስ ኦዲት ከፍተኛ ኦፊሰር እና፣ 6ኛ. ወ/ሮ መቅደስ አረጋዊ ገንዘብ ተቀባይ የሆኑት በቀን 06/01/2017 ዓ.ም በሙስና ወንጀል ተጠርጥረዉ በቁጥጥር ስር ውለዉ ምርመራ እየተጣራ እንደሚገኝ የከተማ አስተዳደሩ አስታውቋል።