” በዚህ ጦርነት ውስጥ ማን እየተጠቀመ እንዳለ ማወቅ አልቻልኩም ” ሲል የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ም/ቤት ተናገረ
” በአማራ እና በኦሮሚያ ክልሎች በመንግስት እና በታጣቂዎች መካከል እየተደረገ ያለው ግጭት ዓላማው ሊገባኝ አልቻለም ” አለ።
ም/ቤቱ ይህን ያለው ለሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬድዮ በሰጠው ቃል ነው።
የም/ቤቱ ዋና ሰብሳቢ ደስታ ዲንቃ ፥ ” በሁለቱ ክልሎች ያለ መፍትሄ የቀጠለው ግጭት የጋራ ምክር ቤቱን በእጅጉ አሳስቦታል ” ብለዋል።
” ንጹሃንን እየገደለ፣ እያሰቃየ እና የሀገርን ሀብት እያወደመ ያለውን ግጭት ሁለቱም አካላት ቆም ብለው አስበው ምን እንዳመጣ እራሳቸውን ሊጠይቁ ” ይገባል ሲሉ ተናግረዋል።
” ንጹሃን፣ ባለስልጣናት እና የባለስልጣናት ልጆች እየተገደሉ እየታፈኑ ነው ” ያሉት ዋና ሰብሳቢው ” በዚህ ጦርነት ውስጥ ማን እየተጠቀመ እንዳለ ማወቅ አልቻልኩም ” ሲሉ አስረድተዋል፡፡
” በጦርነቱ እንደ ሀገር ሀገር እየተጎዳ ነው፣ እንደ ህዝብ ህዝብ እየተጎዳ ነው ፣እንደ ዜጋ ዜጎች እየተጎዱ ነው ፣እንደ ታሪክ ታሪክን እያበላሽን ነው ምን ዓይነት ስሌት አስልተን እንደምንረጋጋ አላውቅም ” ብለዋል፡፡
በሀገሪቱ በመንግስት እና በታጣቂዎች መካከል እየተደረገ ያለው ግጭት ውድመት እያስከተለ ቀጥሏል ያሉት አቶ ደስታ ችግሩን በንግግር ለመፍታት በሁለቱም ወገን ፍላጎት አይታይም ሲሉ ወቅሰዋል፡፡
” አንዱ በአንዱ ላይ የበላይ ለመሆን ከሚደረግ ሩጫ የዘለለ ግጭቱን በንግግር የመፍታት ፍላጎት እየተመለከትን አይደለም ” ሲሉ ገልጸዋል።
” ታጣቂዎች ሆኑ መንግስት ችግሩን በንግግር ከመፍታ ይልቅ ግጭቱን ስም ለማጠልሸት አንዱ ሌላውን ለመወንጀል እና የህዝብ ድጋፍ ለማግኝት እየተጠቀሙበት ነው ” ብለዋል።
ምክር ቤቱ በመንግስት እና በታጣዊዎች መካከል እየተካሄደ ያለው ግጭት ሁለቱም አካላት እቆምለታለሁ ፣ እቆረቆርለታለሁ የሚሉትን ህዝብ እና ሀገርን እያወደመ መሆኑን አውቀው በንግግር ችግራቸውን እንዲፈቱ ለሬድዮ ጣቢያው በሰጠው ቃል ጠይቋል፡፡
TIPS
Growing relations between Israel and Ethiopia: between military deals, intelligence influence, and an eye on Egypt
The Wars We Still Can Stop
Ethiopia: Israel Foreign Minister Says His Country Wants to Be Part of Ethiopia’s Success
A Nation Silenced: How the 1993 Referendum Stripped All Ethiopians of Their Sea
The 1976 TPLF Manifesto: TPLF’s “Republic of Greater Tigray”
Away from the global spotlight, Eritreans are trapped in a garrison state
Testimonials of a Sudanese Intelligence Officer on the Proxy war between Sudan and Ethiopia from 1970s to early 1990s
Ethiopia-Eritrea Tension: A Volatile History that Never Truly Ended – Could Assab Become Africa’s Crimea?
“As an outlier among the five tplf leaders, I wasn’t part of the armed struggle tradition”
Former Tigray fighters say no to war
Don’t Risk Your Future: The United States Cracks Down on Illegal Immigration
Counter-Video by EBC Challenges EBS Broadcast, Sparks Public Outcry Over Alleged Misinformation
Ethiopia and Eritrea Slide Closer to War amid Tigray Upheaval
Sea Outlet Serious and Unabated Agenda for Ethiopia: Retired Lieutenant General Yohannes
Israel’s Peace With Egypt Is Starting to Crack
Egyptian, Eritrean FMs reject involvement of non-bordering countries[Ethiopia] in Red Sea security