የአሜሪካ መንግስት በይፋ ሻዕቢያን የሚቃወሙ ድርጅቶችን በገንዘብ መረዳት የግድ አስፈላጊ መሆኑ፣ “The U.S. must support the fight for a free Eritrea” ኤርትራዊ አሜርካውያን ወደ ኤርትራ የሚልኩት ገንዘብ የሚቆምበት መንገድ እነዲፈለግ የካሊፎርኒያ ግዛት የሕዝብ ተወካይ እንደራሴ ብራድ ሸርማን ጠየቁ፣ ጥያቀው የቀረበው በአሜሪካ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ጉዳይ ኮሚቴ የስቴት ዲፓርትመንት (የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር) መሥሪያ ቤት ኃላፊን ቃል በተቀበለበት ወቅት ነው። ጥያቄውን በማስረጃ አስደግፈው ያቀረቡት ሸርማን የኮሚቴው ከፍተኛ አባል ናቸው።
በአሜሪካ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ጉዳይ ኮሚቴ የስቴት ዲፓርትመንት (የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር) ኃላፊ ቃል በሰማበት ወቅት ተናጋሪ የነበሩት የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ወኪልና በፖለቲካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር ጆን ባስ ነበሩ፡፡
ጆን ባስ በንግግራቸው አሸባሪነትን አስቀድመዋል። በተለይም በአፍሪካ የሚካሄደውን የሽብር ተባር አስመልክቶ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርን አረዳድና ማስረጃ ተንተርሰው ማብራሪያና ሰጥተዋል። በምላሻቸው አገራቸው በአሸባሪዎች ላይ ያላትን የሰና አቋም ገልጸዋል።
ጥያቄ ያቀረቡትን አስተያየታቸውን የሰጡት የኮሚቴው ከፍተኛ አባልና የካሊፎርኒያ የሕዝብ ተወካይ ሸርማን በአፍሪካ የሚንቀሳቀሱ የሽብር ድርጅቶችን ዘርዝረው፣ አሸባሪነትን ለሚዋጉ የአፍሪካ አገራት ስቴት ዲፓርትመንት ልዩ ዕገዛ ማድረግ እንዳለበት አስታውቀዋል። በዚህ ረገድም የጆን ባስን መሥሪያ፣ ውጭ ጉዳይ ማለታቸው ነው፣ ምን እያደረገ ነው ሲሉ ጠይቀዋል።
ስለአፍሪካ የአሸባሪዎች እንቅስቃሴ ካነሱ በሁዋላ በቀጥታ ኤርትራን የጠቀሱት ብራድ ሸርማን ኤርትራን ከሰሜን ኮርያ ጋር አመሳስለው። ስለምስራቅ አፍሪቃ የአሸባሪዎች እንቅስቃሴ ሲያስታውቁ ኤርትራን የጠቆሙት እንደራሴ ብራድ ሸርማን፣ ኤርትራ በኢሳያስ አፈወርቂ አምባገነናዊ ጭቆና ውስጥ የወደቀች አገር መሆኗን አምልክተዋል።
ኢሳያስን በመኮነን አገሪቱን “የአፍሪካ ሰሜን ኮሪያ” ነች ያሉት እንደራሴው፣ ከኢሳያስ ተቃዋሚዎች ጋር መገናኘት አስፈላጊ እንደሆነ አስምረዋበታል። “ተቃዋሚዎችን ማግኘትና በገንዘብ መርዳት አስፈላጊ እንደሆነ አምናለሁ” ሲሉ ድምጻቸውን ከፍ አድርገው አሰምተዋል፡፡ ሲያስረዱም “በኤርትራ ዴሞክራሲያዊ መንግሥት እስካልተመሠረተ ድረስ የኤርትራ ሕዝብ ነጻት አይኖረውም፤ አጎራባች አገራትም ሰላም አይኖራቸውም” ብለዋል። ይህም ንግግራቸው ኢትዮጵያና ኬንያ እንዲሁም ሶማሊያ ስለማ ሊያገኙ አለመቻላቸውን አመላካች ሆኗል። ኢትዮጵያም ውስጥ ውስጡን እየሰራች ላለው ስራ ፖለቲካዊ ድጋፍ የሚሰጥ ሆኖ ተገኝቷል።
የሕዝብ ተወካዩ ብራድ ሸርማን በመጨረሻም ቁልፍ ጉዳይ አንስተዋል። በአሜሪካ የሚኖሩ የአሜሪካ ዜግነት ያላቸው ትውልደ ኤርትራውያን ታክስ እንዳይከፍሉ መገድ ስለሚቻልበት ሁኔታ አንስተዋል። የኤርትራ መንግሥት ከዲያስፖራ የሚሰበስበውን “የዳያስፖራ ታክስ” ዋና የአገሪቱ የገቢ ምንጭ እንደሆነ ይታወሳል። ይህንኑ ገንዘብ ነው “ወደ ኤርትራ እንዳይሄድ እንዴት መከልከል እንችላለን” ሲሉ እንደራሴው የጠየቁት።
ውጭ ያሉ ኤርትራዊያን በውጭ አገራ ባሉ ኤምባሲዎች ማንኛውንም ዓይነት አገልግሎት ለማግኘት ከፍለጉ፣ ከሚኖሩበት አገር አግባብ ያለው ተቋም ገቢያቸውን የሚያሳይ ሪፖርት ማቅረብ ይገደዳሉ። ይህም የሚሆነው የሚጣልባቸውን የዲያስፓራ ቀረጥ ለመገምገም ሲሆን፣ አስፈላጊውን ክፍያ ካላገኙ አገልግሎቱን አያገኙም።
ከኤርትራ በኩል ይህን ዜና ተከትሎ ከፍተኛ ተቃውሞ የተሰነዘረ ሲሆን እንደራሴውን በምርቻ ወቅት ከወያኔዎች ገንዘብ የተቀበሉ ናቸው በሚል የማስታወቂያ ሚኒስትርሩ አቶ የማነ ምላሽ ሰጥተዋል።
በአሜሪካ ለያውም በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ደረጃ እንዲህ ያለ ጉዳይ ለንግግር ያህል የሚነገር እንዳልሆነ የሚገልጹ፣ ዜናው ለኢትዮጵያ መንግስት መልካም አጋታሚ እየተመቻቸ መሆኑንን እንደሚያመልክት አስታውቀዋል።
በቴሌግራም ይከተሉን እባክዎ https://t.me/+f_kxmaPjD-9jYTdk