እስራኤል አርብ እለት በቤሩት ባደረገችው መጠነ ሰፊ የአየር ጥቃት የሄዝቦላህ መሪ ሀሰን ናስራላህን መግደሏን አስታወቃለች፡፡ ሄዝቦላህ መሪው ሀሰን ናስራላህ በአየር ጥቃቱ መገዳለቸውን አረጋግጧል፡፡
ግድያው የተፈፀመው የሂዝቦላህ አመራሮች በዳሂየህ በሚገኘው ዋና ፅህፈት ቤታቸው ሰብሳባ ላይ በነበሩበት ወቅት በተሰነዘረ የአየር ጥቃት መሆኑ ተገልፆል።
ባለፉት ቀናት እሰራኤል በሊባኖስ በፈፀመቻቸው ጥቃቶች ከ720 በላይ ሰዎች የተገለዱሉ ሲሆን ከ200 መቶ ሺ በላይ የሚሆኑት ደግሞ ከቀያቸው ተፈናቅለዋል።
የሄዝቦላህ መሪ በተገደሉበት የአርቡ ጥቃት ብቻ 6 ሰዎች ሲገደሉ 91 ቆስለዋል ፡፡ በጥቃቱ የሄዝቦላህን የሚሳኤል ክፍል ሃላፊ ሙሀመድ አሊ ኢስማኤል እና ምክትሉ ሆሴን አህመድ ኢስማኤል መገደላቸውም ተገልጿል።
በሌላ በኩል እስራኤል በሊባኖስ ላይ የምታደርገው ዘመቻ በእስራኤል ላይ ትልቅ ሽንፈት እንደሚያደርስ ኢራን አስጠንቅቃለች፡

እስራኤል የምድር ጦርነት ከጀመረች ለሂዝቦላህ ትልቅ ደስታ ነው ያሉት አንድ የኢራን ከፍተኛ የጦር አዛዥ እስራኤል ትሰቃያለች ሲሉ ተናግረዋል፡፡
የጦር አዛዡ ይህን ያሉት በቴህራን ከጁምአ ሶላት በኋላ ምእመናን በተገኙበት በተካሄደው ሰልፍ ላይ ነው።
የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ አርብ ዕለት በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላጉባኤ ንግግር አድርገዋል። በንግግራቸውም ኢራን ጥቃት ከፈፀመች እስራኤል አፀፋውን ትመልሳልች ብለዋል፡፡
እስራኤል በቤሩት የምትፈጸምውን የአየር ጥቃት በዛሬው እለትም አጠናክራ ቀጥላለች።