በኒውዮርክ እየተካሄደ ባለው 79ኛው የ.ተ.መ.ድ. ጠቅላላ ጉባዔ የዋና ፀሐፊው አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ኢኒሼቲቭ የሆነውና ከ140 በላይ የአገር መሪዎች የሚሳተፉበት የመጪው ጊዜ ጉባዔ (Summit of the Future) ተከፍቷል።
በዚሁ ጉባዔ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሤ የተመራ የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን እየተሣተፈ ይገኛል።
በጉባዔው ላይ ሚኒስትሩ ባሰሙት ንግግር የተመድ የፀጥታው ምክር ቤት ማሻሻያ የአፍሪካን እውነተኛ ውክልና ባረጋገጠ መልኩ እንዲከናወን ጠይቀዋል።
አምባሳደር ታዬ ምክር ቤቱን ለማሻሻል የሚደረገው እንቅስቃሴ የአፍሪካን የውክልና አድማስ ከሁሉም መመዘኛዎች አንጻር ታሳቢ ሊያደርግ እንደሚገባው ጠይቀዋል።
ስምምነቱ ሁሉንም አገራት በእኩል አይን የሚመለከተው ጊዜ አይሽሬ የሆነው የተመድ መመሥረቻ ቻርተር ሳይሸራረፍ እንዲተገበር ለማድረግ የበኩሉን ሚና እንደሚጫወት ያላቸውን ተስፋ ገልጸዋል።
በመጪው ጊዜ ጉባዔ ላይ የባለብዙ ወገን የዲፕሎማሲ ሥርዓትን ሪፎርም ለማድረግ በትውልድ የአንድ ጊዜ ዕድል ይሆናል ተብሎ የሚጠበቅ ጉባዔ ሠነድ ከ143 አገራት በላይ ድጋፍ በማግኘት ፀድቋል።
አምባሳደር ታዬ ስምምነቱ የዘላቂ ልማት ግቦችን ለማሳካት በሚደረገው ጥረት የሚታዩ ክፍተቶችን ለማስተካከል ከፍተኛ ሚና እንደሚኖረው አንስተዋል።
ሚኒስትሩ አገራት ድህነትን ለማጥፋት የሚያደርጉት ጥረት በራሳቸው የፖሊሲ ማዕቀፍ ምርጫ አግባብ የተጠናከረ ድጋፍ እንዲደረግላቸው እና ለጉዳዩ ቀዳሚ ትኩረት እና የፖለቲካ ቁርጠኝነት እንዲኖር ጠይቀዋል።
ኢትዮጵያ በጉባዔው የፀደቁት ሠነዶች Pact for the Future, Declaration on Future Generations, Global Digital Compact የድርድር ሂደት ላይ ተሳትፎ ስታደርግ ቆይታለች።
የሠነዱ መፅደቅ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ድህነት፣ ረሃብ፣ የአየር ንብረት ቀውስ፣ አደገኛ ግጭቶች፣ ወረርሽኞች እና ከአዳዲስ ቴክኖሎጂዎች ጋር ተያይዘው የሚመጡ አደጋዎች እያደጉ በሚገኙበት ወቅት፣ የጋራ ምላሽ እና መፍትሄ ለመስጠት ዕድል እንደሚፈጥር ታምኖበታል።
(EBC)
TIPS
The Wars We Still Can Stop
Ethiopia: Israel Foreign Minister Says His Country Wants to Be Part of Ethiopia’s Success
A Nation Silenced: How the 1993 Referendum Stripped All Ethiopians of Their Sea
The 1976 TPLF Manifesto: TPLF’s “Republic of Greater Tigray”
Away from the global spotlight, Eritreans are trapped in a garrison state
Testimonials of a Sudanese Intelligence Officer on the Proxy war between Sudan and Ethiopia from 1970s to early 1990s
Ethiopia-Eritrea Tension: A Volatile History that Never Truly Ended – Could Assab Become Africa’s Crimea?
“As an outlier among the five tplf leaders, I wasn’t part of the armed struggle tradition”
Former Tigray fighters say no to war
Don’t Risk Your Future: The United States Cracks Down on Illegal Immigration
Counter-Video by EBC Challenges EBS Broadcast, Sparks Public Outcry Over Alleged Misinformation
Ethiopia and Eritrea Slide Closer to War amid Tigray Upheaval
Sea Outlet Serious and Unabated Agenda for Ethiopia: Retired Lieutenant General Yohannes
Israel’s Peace With Egypt Is Starting to Crack
Egyptian, Eritrean FMs reject involvement of non-bordering countries[Ethiopia] in Red Sea security
Ethiopia, Creditors Agree on $8.4 Billion Debt Restructuring