በሶማሌና በአፋር ክልሎች መካከል ተከስቶ የነበረው ግጭት እንዲቆም መደረጉን ችግሩን ለመፍታት የተቋቋመው ብሔራዊ ኮሚቴ አስታወቀ።
ብሔራዊ ኮሚቴው ባደረገው ግምገማ የመጀመሪያው ምዕራፍ አፈጻፀም ውጤታማ ሆኖ በመገኘቱ ወደ ሁለተኛው የትግበራ ምዕራፍ ለመሸጋገር የሚያስችለውን ውሳኔ አሳልፏል።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ፣ የሰላም ሚኒስትር አቶ ብናልፍ አንዱዓለም እና የሁለቱ ክልሎች ፕሬዚዳንቶች እንዲሁም የፌደራልና የክልል የፀጥታና ደኅንነት አካላት በተገኙበት የኮሚቴው የመጀምሪያ ምዕራፍ አፈጻጸም ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።
በድንበር ይገባኛል ጥያቄ ምክንያት በሶማሌና በአፋር ክልሎች መካከል ተከስቶ የነበረው አለመግባባት ወደ ግጭት አምርቶ ለብዙ ዜጎች የህይወት ህልፈትና ስደት እንዲሁም ለበርካታ ሀብትና ንብረት ውድመት ምክንያት መሆኑ የሚታወስ ነው።
ብሔራዊ ኮሚቴው ለኢፕድ በላከው መረጃ፣ ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት እንዲቻል ከሁለቱ ክልሎችና ከፌደራል መንግሥት የፀጥታና ደኅንነት አካላት የተውጣጣ ብሔራዊ ኮሚቴ ተቋቁሞ ሲሰራ መቆየቱን በሪፖርት ጠቅሷል።
ብሔራዊ ኮሚቴው በመጀመሪያው ምዕራፍ የአፈፃፀም ሂደት ውስጥ በቀጣናው የነበረውን ግጭት የማስቆም፣ የሰዎችን ሞት የመከላከል፣ በግጭት አካባቢዎች ነፃ ቀጣና እንዲኖር የማስቻል እና ነፃ ቀጣናው በመከላከያና በፌደራል ፖሊስ ቁጥጥር ሥር ሆኖ እንዲቆይ የማድረግ ቁልፍ ዓላማዎችን ይዞ ተንቀሳቅሷል።
በመድረኩ ላይ የተገኙት የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጦፌ መሐመድ እንዳሉት፥ በብሔራዊ ኮሚቴው እና በሁለቱ የክልል መንግሥታት በኩል የተጀመረው የሰላም ጥረት በአካባቢው ተቀስቅሶ የነበረው ግጭት እንዲቆም አድርጓል።
ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት ይቻል ዘንድ በሁለቱ ክልሎች አመራሮች መካከል በመተማመንና በወንድማማችነት ስሜት ችግሮችን ለመፍታት እየተደረገ ያለው ጥረት ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባውም ጠቁመዋል።
የአፋር ብሔራዊ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ፥ ኮሚቴውን የሚመሩ የፌደራል ከፍተኛ አመራሮች፣ የዐቢይ እና የቴክኒክ ኮሚቴው አባላት እና በሁለቱ ክልሎች ውስጥ የሚገኙ አመራሮች እንዲሁም ሰላም ወዳዱ የአፋርና የሶማሌ ህዝብ በአካባቢው የነበረው ግጭት ወደ ሰላማዊ ሁኔታ እንዲመለስ ላበረከቱት የጎላ አስተዋፅኦ ያላቸውን አክብሮት ገልፀዋል።
በሁለቱም ክልሎች በኩል የሚስተዋሉ አፍራሽ አመለካከቶችን እየታገሉና እያረሙ መሄድ የየክልሎቹ ከፍተኛ አመራሮች ድርሻ መሆኑን ያወሱት ርዕሰ መስተዳድሩ፤ በመጀመሪያው ምዕራፍ የአፈፃፀም ሂደት ውስጥ የታየው ውጤት አበረታች ነው ብለዋል።
በሁለቱም ክልሎች በኩል የሚስተዋሉ ክፍተቶችን በቅንነት እያረሙ መሄድና የተጀመረው በመተማመን ላይ የተመሰረተ የመፍትሔ አቅጣጫ ዳር እንዲደርስ መረባረብ እንደሚያስፈልግም ጠቁመዋል።
የሰላም ሚንስትሩ ብናልፍ አንዱዓለም፥ ብሔራዊ ኮሚቴው ሲቋቋም ያነገባቸው ግጭትን የማስቆም፣ የሰዎችን ሞት የመከላከል፣ ነፃ ቀጣናን የመፍጠርና በነፃ አካባቢዎች የፌደራል የፀጥታ ኃይሎች እንዲሰፍሩ የማድረግ ቁልፍ ተልዕኮዎች ሙሉ በሙሉ ሊባል በሚችል ደረጃ ተፈፃሚ ሆነዋል ብለዋል።
ይህም የአካባቢው ህዝብ የሰላም አየር እንዲተነፍስና እፎይታ እንዲያገኝ ያስቻለ መሆኑን ተናግረዋል።
በሁለቱ ክልሎች አመራሮችና የፀጥታ ኃይሎች በኩል የሚስተዋሉ ጥቃቅን ክፍተቶች እንዳሉ የጠቆሙት አቶ ብናልፍ፤ ነፃ ቀጣናውን ለቀው ያልወጡ ታጣቂ ኃይሎች በአስቸኳይ አካባቢውን ለቀው እንዲወጡ ማድረግና ችግሩ ዘላቂ መፍትሔ እስኪያገኝ ድረስ በአወዛጋቢ ቀጣናዎች ውስጥ ሰፈራዎችን ከማድረግ መቆጠብ እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል።
የመጀመሪያው ምዕራፍ አፈፃጸም ስኬት ወደ ሁለተኛው ምዕራፍ ለመሸጋገር የሚያስችል ምቹ ሁኔታን የፈጠረ መሆኑንም አስረድተዋል።
የኢፌዲሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በበኩላቸው፥ በአካባቢው የተገኘው አንጻራዊ ሰላም በሁለቱ ክልሎች አመራሮች ጥረትና የሰላም ፍላጎት የተገኘ በመሆኑ ጅምሩ ተጠናክሮ እንዲቀጥልና ችግሩ ዘላቂ መፍትሔ እንዲያገኝ ክፍተቶችን እየደፈኑ፣ ሥጋቶችን እያረሙና በህዝቦች መካከል ያለውን የወንድማማችነት ስሜት እያጠናከሩ መሄድ ያስፈልጋል ብለዋል።
ለዚህ ደግሞ በሁለቱም ክልሎች እጅ የሚገኙ ምርኮኞችን መለዋወጥ፣ ሂደቱን በሚያደናቅፉ አካላት ላይ እርምጃ መውሰድ፣ በውይይትና መግባባት ችግሮችን እየፈቱ መሄድ፣ የሰላም ስምምነቱን ሊያደናቅፉ ከሚችሉ አስተሳሰቦችና ድርጊቶች መቆጠብና ችግሮችን በፍጥነት እየፈቱ ለመሄድ መረባረብ እንደሚገባ አሳስበዋል።
በመጨረሻም ዐቢይ ኮሚቴው በመጀመሪያው ምዕራፍ የተንጠባጠቡ ተግባራት በቶሎ እንዲፈፀሙ፤ የሁለተኛው ምዕራፍ ትግበራም እንዲጀመር በሙሉ ድምጽ ወስኗል።
ሰብዓዊ ድጋፎችን አጠናክሮ መቀጠል፤ ተፈናቃዮችን ወደ ቦታቸው መመለስ፣ የፖለቲካ ውይይቶችንና የህዝብ ለህዝብ መድረኮችን መፍጠር እንዲሁም በእርቅ ችግሩን እየቋጩ መሄድ ኮሚቴው በሁለተኛው ምዕራፍ ትኩረት ከሚሰጣቸው ቁልፍ ተግባራት መካከል ተጠቃሽ መሆናቸውን ለኢፕድ የላከው መረጃው አመልክቷል።
መሰከረም 3 ቀን 2017 ዓም ENA
TIPS
The Wars We Still Can Stop
Ethiopia: Israel Foreign Minister Says His Country Wants to Be Part of Ethiopia’s Success
A Nation Silenced: How the 1993 Referendum Stripped All Ethiopians of Their Sea
The 1976 TPLF Manifesto: TPLF’s “Republic of Greater Tigray”
Away from the global spotlight, Eritreans are trapped in a garrison state
Testimonials of a Sudanese Intelligence Officer on the Proxy war between Sudan and Ethiopia from 1970s to early 1990s
Ethiopia-Eritrea Tension: A Volatile History that Never Truly Ended – Could Assab Become Africa’s Crimea?
“As an outlier among the five tplf leaders, I wasn’t part of the armed struggle tradition”
Former Tigray fighters say no to war
Don’t Risk Your Future: The United States Cracks Down on Illegal Immigration
Counter-Video by EBC Challenges EBS Broadcast, Sparks Public Outcry Over Alleged Misinformation
Ethiopia and Eritrea Slide Closer to War amid Tigray Upheaval
Sea Outlet Serious and Unabated Agenda for Ethiopia: Retired Lieutenant General Yohannes
Israel’s Peace With Egypt Is Starting to Crack
Egyptian, Eritrean FMs reject involvement of non-bordering countries[Ethiopia] in Red Sea security
Ethiopia, Creditors Agree on $8.4 Billion Debt Restructuring