ሁሉም የፓለቲካ ፓርቲዎች በእኩል የሚያሳትፍ በምክር ቤት የሚመራ ሲቪል ጊዚያዊ አስተዳደር እንዲቋቋም አራት የትግራይ ተፎካካሪ የፓለቲካ ፓርቲዎች ጠየቁ።
የጋራ መግለጫውን ያወጡት ፦
– ሳልሳይ ወያነ ትግራይ (ሳወት) ፣
– ባይቶና ዓባይ ትግራይ (ባይቶና) ፣
– ውድብ ናፅነት ትግራይ (ውናት)
– ዓረና ንሉኣላውነትን ዴሞክራስን (ዓረና) ናቸው።
ፓርቲዎቹ ባወጡት የጋራ መግለጫ ፤ ” በትግራይ ያጋጠመው ችግር መነሻው ፓለቲካዊ ውድቀት ስለሆነ ከውድቀቱ ለመውጣት አካታች ፓለቲካዊ መፍትሄ ያስፈልጋል ” ብለዋል።
” ችግሩ የሚፈታው አንድ የፓለቲካ ፓርቲ በሚያራምደው የበላይነት አመራር ሳይሆን ሁሉም አቀፍ በሆነ አካሄድ ነው ” ሲሉ ገልጸዋል።
ለዚህም ሁሉም የፓለቲካ ሃይሎች በእኩል የሚሳተፉበት በምክር ቤት የሚመራ ስቪል ጊዚያዊ አስተዳደር ማቋቋም እንደ አንድ የችግር መፍቻ አስቀምጠዋል።
ፓርቲዎቹ በአሁኑ ወቅት በሁለት የህወሓት ሃይሎች የተፈጠረው ፓለቲካዊ መሳሳብ ወደ ጎን በመተው ወጣቶች ፣ ሴቶች ፣ የዳያስፓራ ማህበረሰብ መላው የትግራይ ህዝብ ዓላማቸው ደግፎ ከጎናቸው ሆኖ እንዲታገል ጥሪ አቅርበዋል።
” የትግራይ የፀጥታ ሃይሎች ከማንኛውም የፓለቲካ ሃይል ውግንና ነፃ በመሆን የሲቪል መንግስትና ህግ በመመራት ለህዝብና አገር ጥቅም መቆም አለባቸው ” ሲሉ አሳስበዋል።
በቅርቡ የሚፈፀሙት ተጨማሪ ተፈናቃዮች ወደ ቄያቸው የመመለስ ፣ ግዛታዊ አንድነት የማስመለስ ፣ ታጣቃዎች ትጥቅ የማስፈታትና ወደ ህብረተሰቡ የመቀላቀልና ሌሎች በትግራይ በኩል የሚፈፀሙ ስምምነቶችና ውሎች ለህዝብና ጉዳዩ ለሚመለከታቸው አካላት ግልፅና ይፋ እንዲደረግም ጠይቀዋል።
TIPS
The Wars We Still Can Stop
Ethiopia: Israel Foreign Minister Says His Country Wants to Be Part of Ethiopia’s Success
A Nation Silenced: How the 1993 Referendum Stripped All Ethiopians of Their Sea
The 1976 TPLF Manifesto: TPLF’s “Republic of Greater Tigray”
Away from the global spotlight, Eritreans are trapped in a garrison state
Testimonials of a Sudanese Intelligence Officer on the Proxy war between Sudan and Ethiopia from 1970s to early 1990s
Ethiopia-Eritrea Tension: A Volatile History that Never Truly Ended – Could Assab Become Africa’s Crimea?
“As an outlier among the five tplf leaders, I wasn’t part of the armed struggle tradition”
Former Tigray fighters say no to war
Don’t Risk Your Future: The United States Cracks Down on Illegal Immigration
Counter-Video by EBC Challenges EBS Broadcast, Sparks Public Outcry Over Alleged Misinformation
Ethiopia and Eritrea Slide Closer to War amid Tigray Upheaval
Sea Outlet Serious and Unabated Agenda for Ethiopia: Retired Lieutenant General Yohannes
Israel’s Peace With Egypt Is Starting to Crack
Egyptian, Eritrean FMs reject involvement of non-bordering countries[Ethiopia] in Red Sea security
Ethiopia, Creditors Agree on $8.4 Billion Debt Restructuring