ኅብረተሰቡ ምን ይላል?
ገዳይ እጆች ይሰብሰቡ! መሞት በቃን! መራብ በቃን!”
ይህ በተለያየ ችግር ውስጥ ያሉ የኅብረተሰብ ክፍሎች ለአሚኮ የሰጡት ድምጽ ነው።
“በቃን! መሞት በቃን፣ መራብ በቃን፣ በሥጋት መኖር በቃን፣ አባቶቻችን እና እናቶቻችን ያወረሱንን እሴት መነጠቅ በቃን፡፡
ከየትኛውም አቅጣጫ በሰላማዊ ዜጎች ላይ የሚተኮሱ ጠብ መንጃዎች ይቁሙልን፡፡ ገዳይ እጆች ይሰብሰቡልን፡፡
በሰላም እና በነጻነት የመኖር መብታችን ይጠበቅልን፡፡ በየትኛውም የሀገሪቱ ክፍል ተንቀሳቅሰን የመሥራት እና ሃብት የማፍራት መብታችን ይጠበቅልን፡፡
በልጆቻችን ላይ የትምህርት ቤቶች በሮች መዘጋታቸው ይቁም፡፡ ለልጆቻችን የድንቁርናን መንገድ አናሳያቸው፡፡ ለልጆቻችን ጠብ አጫሪነትን አናውርሳቸው፡፡ ያልተማሩ ልጆቻችን በነገዋ የሰለጠነች ዓለም ውስጥ ቦታ እንዲያጡ አናድርጋቸው፡፡
ነፍስ ያላወቁ ሕጻናትን መድፈርም ኾነ መግደል ከሰብዓዊነት መውጣት ብቻ ሳይኾን የአውሬነት ባህሪንም መላበስ ነው፡፡
እናቶች በሆስፒታሎች እና በጤና ጣቢያዎች እንዳይወልዱ በማድረግ ተተኪ ትውልድ ማፍራት ላይ እንቅፋቶች አትሁኑ፡፡ በሚዘጉት መንገዶች ስለሚዘጉት ብዙ ጉሮሮዎች አስቡ፡፡
ሺህ ውበታቸው (ሽበታቸው) የሚያስከብራቸውን አባቶች እና እናቶች በመጦር ፈንታ፣ ጧሪዎቻቸውን እየነጠቃችሁ ወደ መኻንነት አትስደዷቸው፡፡
ሁሉን ነገር በተፈጥሮ በታደለችው ሀገራችን እና በክልላችን ውስጥ እንዳንኖር የምትወስኑት ገዳዮች፣ አፋኞች፣ ደፋሪዎች፣ አጋቾች እና ሌሎችም ክፉ እጆቻችሁን ከጫንቃችን ላይ አንሱልን፡፡ በቃችሁ ስንባል መጠራታችን ከፈጣሪያችን እንጂ ከናንተ እንዲኾን አንፈልግም፡፡
ከሀገራችንም ኾነ ከክልላችን ተሰድደን ወዴት እንሂድ? ከሌሎች ክልሎች ስለተሰደዱ ወገኖቻችን ቁጭታችን ሳይወጣ ስለምን እኛም ተሳዳጆች እንኾናለን?
በኑሮ ውድነት ከምናየው ስቃይ ሳንወጣ ስለምን በሕይዎት የመኖር እና ያለመኖር ስቃይ ውስጥ ታስገቡናላችሁ?
ገዳይ እጆች ይሰብሰቡልን! መሞትም፣ መራብም፣ መሰደድም፣ መፈናቀልም፣ መደፈርም፣ መታገትም፣ መሳቀቅም… በቃን!”
የሕዝባችን ድምጽ ይሄ ነው፡፡ የኅብረተሰቡ ድምጽ እንዲሰማ፣ ከችግሩም እፎይ እንዲል የድርሻችን ለመወጣት ምን ያህል ዝግጁ ነን?
“ገዳይ እጆቻችሁ ይሰብሰቡ፤ ወደ አዲስ ዓመት ለመሻገር አሮጌ አስተሳሰባችሁን በአሮጌ አቁማዳችሁ ውስጥ አስቀምጡልን፡፡ ማናችሁም ሁኑ፣ ገዳይ እጆቻችሁ ይሰብሰቡ፡፡ ሰላምን እና ጦርነትን ሚዛን ላይ አስቀምጣችሁ የትኛው ይሻላል? አትበሉን፡፡
የአማራ ክልል ወደ ቀደመ አንጻራዊ ሰላሙ ይመለስ ዘንድ የክፋት አሮጌ ሐሳቦች ወደ አዲሱ ዓመት አብረውን አይሻገሩ”
ለዚህ የኅብረተሰብ ድምጽ መልስ መስጠት የሁላችንም ግዴታ አለብን! አሁንኑ ግዴታችን እንወጣ!
(አሚኮ)”
TIPS
Growing relations between Israel and Ethiopia: between military deals, intelligence influence, and an eye on Egypt
The Wars We Still Can Stop
Ethiopia: Israel Foreign Minister Says His Country Wants to Be Part of Ethiopia’s Success
A Nation Silenced: How the 1993 Referendum Stripped All Ethiopians of Their Sea
The 1976 TPLF Manifesto: TPLF’s “Republic of Greater Tigray”
Away from the global spotlight, Eritreans are trapped in a garrison state
Testimonials of a Sudanese Intelligence Officer on the Proxy war between Sudan and Ethiopia from 1970s to early 1990s
Ethiopia-Eritrea Tension: A Volatile History that Never Truly Ended – Could Assab Become Africa’s Crimea?
“As an outlier among the five tplf leaders, I wasn’t part of the armed struggle tradition”
Former Tigray fighters say no to war
Don’t Risk Your Future: The United States Cracks Down on Illegal Immigration
Counter-Video by EBC Challenges EBS Broadcast, Sparks Public Outcry Over Alleged Misinformation
Ethiopia and Eritrea Slide Closer to War amid Tigray Upheaval
Sea Outlet Serious and Unabated Agenda for Ethiopia: Retired Lieutenant General Yohannes
Israel’s Peace With Egypt Is Starting to Crack
Egyptian, Eritrean FMs reject involvement of non-bordering countries[Ethiopia] in Red Sea security