ኢትዮጵያ የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂን ቀርፃና አፅድቃ ወደ ሥራ ከገባች ሰነባብታለች። ዲጂታል ኢትዮጵያ የዲጂታል ቴክኖሎጂ ዕድሎችን በመጠቀም ፈጠራ የታከለበትና በእውቀት ላይ የተመሰረተ ኢኮኖሚ ለመገንባት የሚያስችል በኢትዮጵያ መንግሥት የሚመራ ተነሳሽነት ነው።
የዲጂታል ቴክኖሎጂ ሽግግር በአካል ከሚደረጉ ግንኙነቶች ወጥቶ የዲጂታል አሠራሮችን በመተግበር ወደ ዲጂታል ኢኮኖሚ ለመድረስ የሚደረግ ጥረት ነው። የዲጂታል የሽግግር መንግሥት፣ በንግድ ድርጅቶች እና በማህበረሰቡ መካከል በአካል የሚያደርጉትን ግንኙነት በበይነ መረብ የመቀየር ሥራ ነው።
የኢትዮጵያ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽንን በግንባር ቀደምትነት ለመምራት የሚችሉና አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን ሊጠቀሙ የሚችሉ አራት ስትራቴጂያዊ ቅድሚያ የሚሰጣቸው ዘርፎችን ለይቷል። የተለዩት ዘርፎችም ግብርና፣ የማምረቻ ዘርፍ፣ የመረጃ ቴክኖሎጂና ቱሪዝም ናቸው።
የዲጂታል ቴክኖሎጂ አቅምና አጠቃቀምን በሚፈለገው ደረጃ ማሳደግ ለሀገር ሁለንተናዊ ዕድገት የሚያበረክተውን አስተዋጽኦ በተመለከተ የዘርፉ ምሁራን ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ማብራሪያ ሰጥተዋል።
በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የሚኒስትሩ ከፍተኛ አማካሪ ዶክተር አብዮት ባዩ እንደሚሉት፤ በአሁኑ ወቅት የዲጂታል ክህሎትና እውቀት ለሀገር ኢኮኖሚያዊ እድገት ወሳኝ ነው። በጤና፣ በትምህርት፣ በግብርና እና በማንኛውም መስክ የሚሰሩ ሥራዎች የዲጂታል ክህሎትን ይፈልጋሉ። የመግባቢያ፣ የመገልገያ እና የማምረቻ መሳሪያዎችም በዲጂታል ቴክኖሎጂ ላይ የተመሰረቱ ናቸው።
በዚህም ማንኛውም ሰው ሥራውን ለማከናወን የዲጂታል ክህሎት ያስፈልገዋል። የዲጂታል እውቀትና ክህሎት በሌለበት ሁኔታ የሀገርን ኢኮኖሚ ሊደግፍ የሚችል የሰው ኃይል ማፍራት ከባድ ነው ሲሉ ይናገራሉ።
ኢትዮጵያ በዲጂታል ክህሎት ወደኋላ ቀርታለች የሚሉት ዶክተር አብዮት፤የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ ኢትዮጵያ በዓለም ደረጃ ብቻ ሳይሆን ከጎረቤት ሀገራትም አንጻር ወደኋላ ቀርታለች ብሎ ያስቀምጣል። ኢትዮጵያን በዲጂታል ክህሎት ከሌሎች ሀገራት ጋር ተወዳዳሪ ለማድረግ በርከት ያሉ ዜጎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ ክህሎት ስልጠና ቀርጾ መተግበር እንደሚገባ ስትራቴጂውን ዋቢ አድርገው ይገልጻሉ።
አሁን ላይ የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂን ቀርጻ ወደ ተግባር መግባቷና አምስት ሚሊዮን ወጣቶችን በዲጂታል ማሰልጠን መጀመሯ ለሀገሪቱ ኢኮኖሚ ግንባታ ወሳኝ ነው። ከኢኮኖሚ ግንባታ ባለፈም በርከት ያሉ ወጣቶችን በዲጂታል ቴክኖሎጂ በማሰልጠን በቴክኖሎጂ ካደጉ ሀገራት ተርታ እንድትሰለፍ እድል ይፈጥራል ይላሉ።
በቀጣይም የዲጂታል ክህሎት ያላቸው ዜጎችን ለማፍራትና የቴክኖሎጂ መሰረተ ልማትን ለማስፋፋት ትኩረት ማድረግ እንደሚገባ በአጽንኦት ያስረዳሉ።
የዲጂታል ክህሎት በዋናነት መሠረታዊ የኮምፒውተር እውቀት፣ዲጂታል ቴክኖሎጂዎችን ተጠቅሞ ሥራ መሥራት መቻልንና መተግበሪያዎችን ማልማትን ያጠቃልላል የሚሉት ዶክተር አብዮት፤ መሠረታዊ የኮምፒውተርን ክህሎት ሁሉም ሰው ሊያውቀው ይገባል። በዚህም አብዛኛው ሀገራት ዜጎቻቸው መሠረታዊ የኮምፒውተር ክህሎት እንዲኖራቸው እያደረጉ መሆኑን ያመላክታሉ።
ወደሥራ የሚሰማራው የሰው ኃይል ውጤታማ ሥራን ማከናወን የሚችለው ዲጂታል ቴክኖሎጂዎችን ሲጠቀም በመሆኑ፤ የዓለም ሀገራት የትምህርት ሥርዓት የዲጂታል ክህሎትን ያካተቱ ናቸው። በዚህም ማንኛውም ሰው በሚያልፍበት የትምህርት ተቋማት በቂ የዲጂታል ክህሎት አግኝቶ እንዲወጣ እያደረጉ ስለመሆኑ ይናገራሉ።
ሀገራት ራሳቸውን ለመጠበቅ፣ ጥቃት ለማድረስ እና ኢኮኖሚያዊ እድገታቸውን ለማፋጠን አዳዲስ መተግበሪያዎችን የሚያለሙ እና በቂ የዲጂታል ክህሎት ያላቸው ዜጎችን ማፍራት ላይ ትኩረት ማድረጋቸውን ያስረዳሉ።
ኢትዮጵያ ለዘመናት ስትከተለው የቆየችው የዲጂታል ፖሊሲ ውድድርን የማያበረታታ መሆኑ፤ መሠረተ ልማት አለመስፋፋቱ እና ኢትዮ ቴሌኮም በገበያ የሚመራ ባለመሆኑ ወደኋላ እንድትቀር ምክንያት መሆኑን ያብራራሉ።
ኢትዮጵያ ወደኋላ የቀረችበትን የቴክኖሎጂ ዘርፍ ችግሮች በመፍታት ከአደጉ ሀገራት ጋር ተወዳዳሪ ለማድረግ የቴሌኮም ሴክተሩን ለገበያ ክፍት የማድረግ፣ አዳዲስ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎችን ወደገበያ የማስገባት፣ የትምህርት ካሪኩለሙን የመቀየር፣ በመንግሥት አሠራር ዲጂታል አሠራርን አስገዳጅ ማድረግ፣ የዲጂታል ክፍያዎችን በዲጂታል የማድረግ እና ሌሎች በርካታ ሥራዎች እየተሠሩ መሆኑን ያስረዳሉ።
በቀጣይም እነዚህን እና ሌሎች ሥራዎችን ትኩረት በመስጠት መተግበር ከተቻለ ኢትዮጵያ በቴክኖሎጂ ካደጉ ሀገራት ተርታ መሰለፍ ትችላለች ሲሉ ያብራራሉ።
ሌላኛው የቴክኖሎጂ ባለሙያ ካሳሁን ጉተማ በበኩላቸው፤ አሁን ያለንበት ዘመን የቴክኖሎጂ እንደመሆኑ መጠን ኢንዱስትሪዎች፣ የወጪና ገቢ ንግዱ፣ ማህበራዊ ጉዳዮች እና ሌሎች ዘርፎች በቴክኖሎጂ እየተሳሰሩ ነው ይላሉ።
የተለያዩ ዘርፎች ከቴክኖሎጂ ጋር መተሳሰራቸው መረጃዎችን በቀላሉ ለማግኘት፣ ጊዜን ለመቆጠብ፣ የአገልግሎት አሰጣጥን ለማዘመንና ሌሎች ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታዎችን ያስገኛል።
የዓለም ሀገራት የቴክኖሎጂ ዘርፍን የመወዳደሪያ መስፈርት አድርገው በትኩረት እየሠሩበት መሆኑን በመግለጽ፤ የግብርና፣ የጤና፣ የፋይናንስ፣ የትምህርት እና ሌሎች አገልግሎት ሰጪ ኩባንያዎች ከቴክኖሎጂ ጋር ተሳስረው አገልግሎት አሰጣጣቸውንና መረጃ አያያዛቸውን በማዘመንና በማቀላጠፍ ምርትና አገልግሎታቸውን በማሳደግ ተወዳዳሪ ሊሆኑ እንደሚገባ ያስረዳሉ።
ባለሙያው እንደሚሉት፣ የኢትዮጵያ የቴክኖሎጂ አቅምና አጠቃቀም ካለፉት ጊዜያት እየተሻሻለ ቢመጣም፤ አሁንም ሰፊ ሥራን ይጠይቃል። መንግሥት ዘርፉን ለማሳደግ የጀመራቸው ሥራዎች መበረታታት እንዳለባቸው እና ከሕፃናት ጀምሮ በሁሉም የእድሜ ደረጃ ለሚገኙ ሰዎች ቴክኖሎጂን በማስረዳት የእውቀት ሽግግር ማድረግ እንደሚገባ ይናገራሉ።
የቴክኖሎጂውን ዘርፍ ለማሳደግ መንግሥት የልማት አጋሮች፣ የግል ድርጅቶች ትምህርት ቤቶች እና እያንዳንዱ ማህበረሰቡ ኃላፊነት ወስደው ሊሠሩ ይገባል። ኢትዮጵያን በቴክኖሎጂ ተወዳዳሪ ማድረግ ከተቻለ የሀገሪቱን ሁለንተናዊ እድገት ማሳለጥ፣ በሁሉም ዘርፎች ብቁ የሆነ ትውልድን ማፍራት እና ኢንቨስተሮችን መሳብ ያስችላል ይላሉ።
ዲጂታል ኢትዮጵያ የመንግሥትን፣ የግሉን ዘርፍና የልማት ድርጅት ተዋንያንን በአንድ ላይ በማሰባሰብ፣ መሠረታዊ የዘርፍ ተነሳሽነትን በመለየት የሀገሪቱን የዲጂታል ኢኮኖሚ ጉዞ የሚያሳልጥ በመሆኑ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በኃላፊነት ሊሠሩ ይገባል።
ሄለን ወንድምነው
Via አዲስ ዘመን መስከረም 3 ቀን 2017 ዓ.ም
TIPS
The Wars We Still Can Stop
Ethiopia: Israel Foreign Minister Says His Country Wants to Be Part of Ethiopia’s Success
A Nation Silenced: How the 1993 Referendum Stripped All Ethiopians of Their Sea
The 1976 TPLF Manifesto: TPLF’s “Republic of Greater Tigray”
Away from the global spotlight, Eritreans are trapped in a garrison state
Testimonials of a Sudanese Intelligence Officer on the Proxy war between Sudan and Ethiopia from 1970s to early 1990s
Ethiopia-Eritrea Tension: A Volatile History that Never Truly Ended – Could Assab Become Africa’s Crimea?
“As an outlier among the five tplf leaders, I wasn’t part of the armed struggle tradition”
Former Tigray fighters say no to war
Don’t Risk Your Future: The United States Cracks Down on Illegal Immigration
Counter-Video by EBC Challenges EBS Broadcast, Sparks Public Outcry Over Alleged Misinformation
Ethiopia and Eritrea Slide Closer to War amid Tigray Upheaval
Sea Outlet Serious and Unabated Agenda for Ethiopia: Retired Lieutenant General Yohannes
Israel’s Peace With Egypt Is Starting to Crack
Egyptian, Eritrean FMs reject involvement of non-bordering countries[Ethiopia] in Red Sea security
Ethiopia, Creditors Agree on $8.4 Billion Debt Restructuring