የታላቁ የህዳሴ ግድብ በርካታ ፈተናዎችን ተሻግሮ አሁን ያለበት ደረጃ ደርሷል። ግድቡ አሁን ላይ ወደ ኋላ ከ205 እስከ 10 ኪሎ ሜትር ተኝቷል። ጥልቀቱ 133 ሜትር ደርሷል። ይህም የጣናን ኃይቅ እጥፍ ሆኗል። 62 ቢሊዮን ሜትር ኪዩቢክ ውሃ ይዟል። አራት ተርባይኖች ኃይል እያመነጩ ሲሆን በቀጣይ አራት ወራት ውስጥም ወደ ሰባት ከፍ ይላል።
የግድቡ ግንባታም በቀጣይ አንድ ዓመት ውስጥ ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል። የህዳሴ ግድብ አሁን የደረሰበት ደረጃ ለመድረስ ከምሥረታው ጀምሮ በርካታ ጫናዎችንና ውጣ ውረዶችን አልፏል። ይሁን እንጂ ፈተዎችንና ውጣ ውረዶችን አልፎ ለስኬት በቅቷል፤ ፍሬውንም መቅመስ ጀምረናል።
ከሰሞኑን ጠቅላይ ሚኒስር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የታላቁን ህዳሴ ግድብ አስመልክቶ እንደገለጹት፤ ባለፉት አምስት ዓመታት ኢትዮጵያ በተለያየ ግንባር በተለያዩ ችግሮች ተይዛ ሳለች 15 ሺህ የሚጠጉ የውጭ ኃይሎች በህዳሴ ግድብ ጉዳይ ብቻ አሰማርተውብናል። ሲሚንቶ አምርቶ አጓጉዞ እስከ ህዳሴ ለማድረስ 15 ሺህ የሚጠጋ የተለያየ ስም ያላቸው ለውጭ የተገዙ ሰዎች ህዳሴን ለማስተጓጎል ሞክረዋል። ብዙ ጊዜና ሕይወት አጥፍተዋል።
የኢትዮጵያውያን ሊገነዘቡ የሚገባቸው ለህዳሴን ሃሳብ፣ ገንዘብና ጊዜ ብቻ አልገነባውም፤ የገነባው ደም ጭምር ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ብዙ ዋጋ ከፍለንበታል፤ ህዳሴ ብዙ ሀብት በአቅማቸው ልክ አዋጥተዋል ሲሉ ገልጸዋል።
ህዳሴን ሲሠሩ በሌላ በኩል ደግሞ ጊዜን፣ ሀብትንና ገንዘባቸውን አውጥተው ዓለም አቀፍ ጫና ለመፍጠርና በሀገር ውስጥ የተለያዩ ኃይሎችን በማስታጠቅ የሚሠሩ አሉ። በአንድ ሀገር ውስጥ አንዱ ለልማት ሌላኛው ለጥፋት ይሠራሉ። በዚህ አስቸጋሪ ሂደት ውስጥ ግድቡ አስደናቂ በሆነ መንገድ ውሃ ይዟል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አብራርተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እንዳብራሩት፤ ለማደግና ለመለወጥ ወደ ሥራ ስንገባ ዓለም ሁሉ አጨብጭቦ የሚቀበለን ባለመሆኑ ከወትሮው መንገድ በተለየ መደማመጥና ለጋራ ዓላማ መቆም አስፈላጊ ነው። ባለን ጉልበትና ገንዘብ መተባበር አስፈላጊ ነው፤ ካልሆነ ስንዴው፣ የአረንጓዴ ዐሻራው፣ የኮሪደል ልማቱና የህዳሴው ግንባታ በዋዛ ፈዛዛ ሊሳካ አይችልም ነው ያሉት።
ለህዳሴ ግድብ የከፈልነው ዋጋ አብዛኛው ኢትዮጵያዊ ስትራቴጅክ እሳቤውን ተገንዝቦ ቢሆን ብዙ ዋጋ ባልከፈልን ነበር። ከዚህ መማር ያስፈልጋል። ሱዳንና ግብጽ መደገፍ ያለባቸው ግድብ ነው፤ በቀን እስከ ዘጠኝ መቶ ሚሊዮን ሜትር ኪዩቢ ውሃ ይይዛል። አጠቃላይ የመያዝ አቅሙ 74 ቢሊዮን ሜትር ኪዩቢ በመሆኑ በ74 ቀን ውስጥ ሙሉ ውሃውን መያዝ እንችላለን። ሌላው ቢቀር በ100 ቀን ውስጥ ግድቡ ሙሉ ማድረግ እንደሚቻል ያብራራሉ።
ይህ ደግሞ ታችኛው ተፋሰስ ሀገራት በማንኛውም ጊዜ ተጨማሪ ውሃ ቢስፈልጋቸው በቀላሉ መጠቀም ይችላሉ፤ ይህ የሚሆነው ግን ውሃውን መያዝ ሲቻል መሆኑን ገልጸዋል። አሁን ላይ አራት ተርባይኖች ኃይል እያመረቱ ነው። በቀጣይ አራት ወራት ውስጥ ተጨማሪ ሶስት ተርባይኖች ሥራ ይጀምራሉ። ታህሳስ ላይ ሰባት ተርባይኞች ኃይል ያመርታል። አጠቃላይ ሥራው ከአንድ ዓመት በኋላ ይጠናቀቃል ሲሉም ገልጸዋል።
ህዳሴን ከሞላ ጎደል ጨርሰነዋል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ከዚህ በኋላ በህዳሴ ጉዳትና ስጋት የለንም፤ ለማደናቀፍ የሞከሩ ኃይሎች ጉዳት አድርሰው ሊሆን ይችላል፤ ነገር ግን አላቆሙንም። ሥራውን ጨርሰነዋል። ያወጡት ገንዘብ፣ ጉልበትና ድካም ከንቱ ሆኖ ቀርቷል። ነገር ግን ህዳሴን ለመደገፍ ቢያውሉት በተሻለ ትብብር ጥቅም ላይ ሊውል ይችል ነበር። በርካታ ኢትዮጵያውያን ከህዳሴ ግድብ ግንባታ ለአፍሪካ የሚተርፍ ልምድና እውቀት ማግኘታቸውን ነው የተናገሩት።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስርት አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ ከሰሞኑን በአፍሪካ ቀንድ ዙሪያ በሰጡት ማብራሪያ እንደገለጹት፤ የህዳሴን ግድብ በተመለከተ ኢትዮጵያ ከግብጽ ጋር በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ዝግጁ ናት። ብዙ የሚያለያየን ጉዳይ የለም፤ ችግር የሆነው በግብጽ በኩል ፖለቲካ እየተቀላቀለበት ነው። የናይል ስምምነት ማዕቀፍ በተፋሰሱ ሀገራት እየተፈረመ ነው። የፈረሙ ሀገራም ሰነዱን ለአፍሪካ ህብረት እያስገቡ ነው፤ ያልፈረሙም ፈርመው በአንድ ማዕቀፍ ውስጥ እንሥራ የሚል ፍላጎት ኢትዮጵያ እንዳላት አብራርተዋል።
የናይል ስምምነት ማዕቀፍ ከላኛው የተፋስሱ ሀገራት ይልቅ ለታችኞች የተፋሰስ ሀገራት በጣም ጠቃሚ ነው። ህዳሴ በርካታ ፈተናዎችን አልፎ ወደ መጠናቀቁ መድረሱን አንስተዋል።
የህዳሴው ግድብ ተሟጋችና የኪንግስ ኦፍ ዓባይ ሚዲያ ምክትል ኃላፊ ዛሂድ ዘይዳን በበኩላቸው እንደገለጹት፤ የህዳሴ ግብድ በ2020 ብዙ ውሃ አልያዘም ነበር። ነገር ግን የሥራ እንቅስቃሴው አስደሳች ነበር። ስለ ህዳሴው ብዙ አሉታዊ ነገሮች በሚወሩበት ጊዜ የነበረው የሥራ እንቅስቃሴ አስደሳች ነው።
በአሁኑ ጊዜ ህዳሴ ግድቡ የሚገኝበት አካባቢ አየር ንብረቱ ሙሉ ለሙሉ ተቀይሯል፤ ከፍተኛ ሙቀት ነበር፤ አሁን ላይ ሙሉ ለሙሉ አረንጓዴ ስለመሆኑ ገልጸዋል። አሁን ላይ ህዳሴ በርካታ ችግሮችን አልፎ 62 ቢሊዮን ሜትር ኩዩቢ ውሃ መያዙ ትልቅ ስኬት ነው። ለህዳሴው ግድብ የለፉ ሁሉ የሚደሰቱበትና ልፋታቸው ፍሬ እያፈራ ስለመሆኑ የሚያስገነዘብ ነው ይላሉ።
አሁን የታየው የህዳሴ ግድብ ስኬት የሁሉም ኢትዮጵያዊ ርብርብ ነው ያሉት ምክትል ኃላፊው፤ 62 ቢሊዮን ሜትር ኪዩቢ ማለት ትርጉሙ ብዙ ነው። ግድቡ ቆሟል፣ ለግብጽ ተሽጧልና መሰል አውንታዊ ለሆኑ መረጃዎች ምላሽ የሰጠ ነው። የፖለቲካ ተቋውሞ ያላቸው ዜጎች ግድቡንና ፖለቲካን መለየት አለባቸው ነው ያሉት።
አሁን ብዙ ለውጥ አለ፤ ለማለቅ ወደ ጫፍ ደርሷል። አሁን ላይ የውሃ ፍሰት እንደሚያሳየው የግድቡ ርዝመት 628 ሜትር መድረሱን ነው። ይህ ማለት ደግሞ ግንባታው ወደ መጠናቀቁ እየደረሰ ነው። እንዲሁም ከ60 ቢሊዮን ሜትር ኪዩቢ በላይ ውሃ እንዲይዘ ያስችለዋል። ግድቡ 74 ነጥብ 2 ቢሊዮን ሜትር ኪዩቢ ውሃ ይይዛል፤ አሁን ላይ ከ98 በመቶ በላይ ውሃ ይዘናል። ይህ ደግሞ የሁሉም ኢትዮጵያዊያን ህልም እውን ስለመሆኑ ማሳያ መሆኑን ገልጸዋል።
እንደ አቶ ዛሂድ ገለጻ፤ ግድቡ ከተጀመረበት ጊዘ ጀምሮ የነበሩ ዛቻዎችንና ዓለም አቀፍ ጫናዎችን ተቋቁሞ 62 ነጥብ 1 ቢሊዮን ሜትር ኪዩቢ ውሃ መያዝ መቻሉ የኢትዮጵያን ጽናት ያሳያል። ግድቡ ውሃ እንዳልያዘ ተደርጎ ሲነዙ የነበሩ የተሳሳቱ መረጃዎችን በገሀድ ያጋለጠ ነው። ያመጣው የአየር ንብረት ለውጥ ከፍተኛ በመሆኑ ጠቀሜታው ለሁሉም ነው። ኃይል የሚያመነጩ ተርባይኖችም እየበዙ ነው፤ ይህ ደግሞ ለሁሉም ኢትዮጵያዊ ትልቅ ኩራት ነው ሲሉ 2016 ዓ.ም ስኬትን ነው ያብራሩት።
በአዲሱ ዓመትንም ሌላ ስኬት የሚመዘገብበት፣ ኢትዮጵያ ሁለተናዊ ዕድገት የሚረጋገጥበት እንደሚሆን ተስፋቸውን ገልጸዋል።
ሞገስ ጸጋዬ አዲስ ዘመን መስከረም 2 ቀን 2017 ዓ.ም
TIPS
The Wars We Still Can Stop
Ethiopia: Israel Foreign Minister Says His Country Wants to Be Part of Ethiopia’s Success
A Nation Silenced: How the 1993 Referendum Stripped All Ethiopians of Their Sea
The 1976 TPLF Manifesto: TPLF’s “Republic of Greater Tigray”
Away from the global spotlight, Eritreans are trapped in a garrison state
Testimonials of a Sudanese Intelligence Officer on the Proxy war between Sudan and Ethiopia from 1970s to early 1990s
Ethiopia-Eritrea Tension: A Volatile History that Never Truly Ended – Could Assab Become Africa’s Crimea?
“As an outlier among the five tplf leaders, I wasn’t part of the armed struggle tradition”
Former Tigray fighters say no to war
Don’t Risk Your Future: The United States Cracks Down on Illegal Immigration
Counter-Video by EBC Challenges EBS Broadcast, Sparks Public Outcry Over Alleged Misinformation
Ethiopia and Eritrea Slide Closer to War amid Tigray Upheaval
Sea Outlet Serious and Unabated Agenda for Ethiopia: Retired Lieutenant General Yohannes
Israel’s Peace With Egypt Is Starting to Crack
Egyptian, Eritrean FMs reject involvement of non-bordering countries[Ethiopia] in Red Sea security
Ethiopia, Creditors Agree on $8.4 Billion Debt Restructuring