ታላቁ የፊልም ባለሙያ ፕሮፌሰር ሐይሌ ገሪማ በአንድ ወቅት የዚህች ሀገር ችግር ተማርን ታወቅን በሚሉ እውቀት አልባዎች አንደሚባባሰ ሲናገሩ ” እነ ሚዋጉሸ ” የሚል ሰያሜ ሰጥተዋቸው ደሀውን ህዝብ ማጫረሰ እንጂ ለኢትዮጵያ ጥቅም አያሰቡም”ብለው ነበር።
ሰዎቹ ህዝብን ማነሣሣት ፣ የተሣሣተ መረጃ መሰጠት ፣ ጥላቻን መዝራት እና ለውጥን መቃወም ነው የሚችሉት ።
እነዚህ ሰዎች በሀገራቸው የሚካሄድ የለውጥ ሂደትን ለምን እንደሚቃወሙ ባይነግሩንም ከጀርባቸው አንዳች የተደበቀ ነገር እንዳለ ለመገመት አያዳግትም
ልማት እንዴት የሰው ልጅን አንደሚያፈርሰ
ባላውቅም በአንዳንድ የመድረክ ፅሁፎቿ
የማውቃት አዜብ ወርቁ እንደ ሌሎች ልብ
ወለድ ሥራዎቿ በምናብ በፈጠረቻቸው አዛውንት ሰም የፃፈችው ተውኔት ድፍን አዲሰ አበቤን አሰገርሟል
ከ60 አመት በፊት 250 ኪ/ሜ አሰጉዛ
ወደ ፈረንሳይ ባሰመጣቻቸውና ወልደው ከብደው በ93 አመታቸው የአልጋ ቁራኛ ባደረገቻቸው አዛውንት ታክካ የውሸት ታሪክ ፈጥራ በልማት ላይ ያላትን ጥላቻ ነግራናለች
የአዜብ ወርቁ ተውኔት ልማት እንዴት ሰው
እንደሚያፈርሰ ባያሰረዳላትም ተውኔታዊ
ትርክቷን በመጎተት ወደ ጫካ ፕሮጀክት መውሰዷ ተውኔቱን ካሰበችው መንገድ አሰወጥቶባታል።
እውነት ለመናገር በቆሻሻ ክምርና ለኑሮ
በማይመቹ ሠፈርነታቸው የሚጠቀሱት
እነ አትክልት ተራ ፣የአድዋ ሙዚየም የተገነባበት ሰፍራ ፣ ዶሮማነቂያ ፣ እሪበከንቱ
እና የመሳሰሉት አካባቢዎች ፈርሰው ሲገነቡና ለነዋሪዎች የተሻለ መኖሪያ ተመቻችቶላቸው ሲረከቡ አንድነገር ትንፍሸ ያላለችው የድል አጥቢያ አርበኛዋ አዜብ ወርቁ ከብት ባልዋለበት ኩበት ለቀማ እንዲሉ የጫካ ፕሮጀክት ላይ ለምን ጣቷን መቀሰር እንደፈለገች የአደባባይ ሚሰጥር ነው
በነገራችን ላይ በ2ኛው የኮሪደር ልማትና
የወንዝ ተፋሰሰ ካልሆነ በሰተቀር በጫካ
ፕሮጀክት ጉዳይ ህዝብ ያልተሰበሰበ መሆኑ እየታወቀ የ2017 የጥላቻ መርዟን በደከሙ አዛውንት አክተርነት የተጀመረውን ልማት ለማደናቀፍና ህዝብን የማተራመሰ ከንቱ ፍላጎቷን አሳይታናለች
ዛሬ በአዲሰ አበባ የኮሪደር ልማቱ መጥቶ እኛም እንደ ፒያሳና አዋሬ ሰዎች የተሻለ ቤት ባገኘን የሚሉ ብዙ ነዋሪዎች ባሉባት ከተማ ሰው ፈረሰ በማለት የጥላቻ ፕሮፓጋንዳ መንዛት ፕሮፌሰሩ እንዳሉት
“እነሚዋጉሸ” ከማለት ውጪ ምን ይባላል
አሁን በመተግበር ላይ ያለው በመቶ
ቢሊየኖች የሚገመት ብር የተመደበለት በጀትም የልማቱ ተነሺዎች ወደ ተሻለ ህይወትና ጤናማ የአኗኗር ዘይቤ የሚቀየሩበት መንገድ እየተመቻቸ ሰዎች ከኑሮአቸውና ከሰራቸው ሳይፈናቀሉ ልማቱ ከዳር እንዲደርሰ በትኩረት ይቀጥላል።
አዲሰ አበባን እንደ ሰሟ የደመቀችና ውብ እናደርጋታለን ብለን በለውጡ ማግሰት ለህዝባችን ቃል ገብተናል ያሉት ከንቲባዋ ለእነ አዜብ ወርቁ አልታይ ያላቸውን በአምሰቱ የኮሪደር ልማቶች ስታንዳርዱን የጠበቀ ገፅታ ፣ ውበት፣ አገልግሎትና ፅዳት ከተማዋ እንዲኖራት አድርገዋል
መንግሰት አዲሱን የኮሪደር ልማት በይፋ
ከመጀመሩ በፊት ባለፉት አምሰት አመታት
እነ አዜብ ወርቁ ሰው ማፍረሰ ያሉትን በርካታ የከተማ ማሰዋብና የመናፈሻዎች ፕሮጀክቶችን ሲተገብር መቆየቱ ይታወቃል
ከእንጦጦ መናፈሻ ጀምሮ የቤተመንግሰቱ
አንድነት ፓርክ ፣ ወዳጅነት ፓርክ ፣ የአራት ኪሎና የመሰቀል አደባባይ ፣የቦሌ መንገድ
ከአዲሰ አበባ ውጪም ሐላላ ኬላ፣ወንጪ
ኮይሻ ፣ ጨበራ ጩርጩራና ሌሎችም
በፍጥነት ተሰርተው ሲጠናቀቁ መሰል
የጥላቻ እንቅፋቶች እየታለፉ ነበር
ልክ እንደ እነ አዜብ ወርቁ ትርክት ነብሰጡሮች፣ ህፃናት፣ጧሪ ደጋፊ የሌላቸው አቅመ ደካሞች ሜዳ ላይ ወደቁ አይነት ድራማ ሞክረው የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት ቢጋጋጡም አልተሳካላቸውም ህዝብ አሁን የተጀመረውን የልማት ውጤት አይቷልና ለድብቅ የፖለቲካ አላማ መሣሪያ የሚሆን አይደለም ።
ባለፉት አምሰት አመታት ከግጭትና ከሁከት እንዲሁም አዜብ ወርቁን ከመሰሉ
የሐሰት የጥላቻ ትርክት ፈጣሪዎች ተላቃ በማታውቀው ኢትዮጵያ በለውጡ ሀይላት
የተከናወኑት ሰራዎች ለሀገሬ አሰባለሁ
ለሚል ዜጋ ተነሳሸነት ሀይል ከመሆኑም ባሻገር አዲሰ አበባን ይበልጥ ለኑሮ ተሰማሚና ውብ ለማድረግ በኮሪደር ልማት ፕሮጀክት አፍርሶ የመገንባት ሰራ ተጠናክሮ መሄዱን መቃወም በማይመች ሁኔታና በድህነት ህዝቡ መኖር አለበት ብሎ እንደመሰለፍ ይቆጠራል ።
የለውጡ ሀይል የልማት ተነሺዎችን ዴሞክራሲያዊ መብቶች እያከበረ በተጀመረው መንገድ የህዝቡን ተሳትፎ እያረጋገጠ በተቻለ መጠን የሀብት ብክነትና ውንብድናን አደብ እያሰያዘ ብሎም አፍራሹን ፖለቲካ በተግባር በመመከት ወደፊት መሄዱን ይቀጥላል።
ሕዝባዊ ተሳትፎን በነቃና በተደራጀ ሁኔታ
አንቀሳቅሶ የነዋሪዎችን ሁኔታ ለመለወጥ
በከርሞ ጥጃዎች ሣይወዛገብ ግቡን ይመታል::
በኑፊ ከበደ
TIPS
The Wars We Still Can Stop
Ethiopia: Israel Foreign Minister Says His Country Wants to Be Part of Ethiopia’s Success
A Nation Silenced: How the 1993 Referendum Stripped All Ethiopians of Their Sea
The 1976 TPLF Manifesto: TPLF’s “Republic of Greater Tigray”
Away from the global spotlight, Eritreans are trapped in a garrison state
Testimonials of a Sudanese Intelligence Officer on the Proxy war between Sudan and Ethiopia from 1970s to early 1990s
Ethiopia-Eritrea Tension: A Volatile History that Never Truly Ended – Could Assab Become Africa’s Crimea?
“As an outlier among the five tplf leaders, I wasn’t part of the armed struggle tradition”
Former Tigray fighters say no to war
Don’t Risk Your Future: The United States Cracks Down on Illegal Immigration
Counter-Video by EBC Challenges EBS Broadcast, Sparks Public Outcry Over Alleged Misinformation
Ethiopia and Eritrea Slide Closer to War amid Tigray Upheaval
Sea Outlet Serious and Unabated Agenda for Ethiopia: Retired Lieutenant General Yohannes
Israel’s Peace With Egypt Is Starting to Crack
Egyptian, Eritrean FMs reject involvement of non-bordering countries[Ethiopia] in Red Sea security
Ethiopia, Creditors Agree on $8.4 Billion Debt Restructuring