የግብፅ የስለላ ተቋም ኃላፊ እና በውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ ባድር አብዱል አቲ የተመራ ልኡካን ቡድን በአስመራ መግባታቸውን ተከትሎ እንደተሰማው ኢትዮጵያ ላይ በጣምራ ከበባ የሚያደርጉበትን ዕቅድ አጽድቀዋል። በርካቶች ኤርትራ ኢትዮጵያ ላይ እየፈጸመች ያለችውን ሴራ አስመልክቶ ለኤርትራም ሆነ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ግልጽ መረጃ ሊሰጥ እንደሚገባ እየጠየቁ ነው።
የግብፅ ጠቅላላ የስለላ አገልግሎት ኃላፊ አባስ ካሜል እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ባድር አብደልላቲ በአስመራ ለፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፉወርቂ የተላከ መልዕክት ለማድረስ ወደ አስመራ መግባታቸው ቢገልጽም፣ በዋናነት ግን ኢትዮጵያ ላይ ከበባ ለማጠናከር ቀደም ብሎ በተያዘው ዕቅድ መሰረት ለመነጋገር መሆኑን መረጃዎች እየወጡ ነው።
የግብጽ ከፍተኛ ባለስልጣናት ወደ አስመራ የሄዱት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌና ሌሎች በኢትዮጵያ ውስጥ ጠብመንጃ ካነሱ ሃይሎች ጋር አብረው የሚሰሩ አስመራ ከትመው ከሻዕቢያ ጋር ከመከሩ ባሁዋላ እንደሆነ እንቅስቃሴውን በቅርብ የሚከታተሉ አመልክተዋል። ይህም ኢትዮጵያን በውስጥ በጦርነት ለማመስ ኃላፊነት የወሰዱት አካላት በተጠና ዕቅድ እንደሚንቀሳቀሱ ማረጋገጫ አቶ አንዳርጋቸው ጠብ መንጃ ካነሱት ጋር ብቻ ሳይሆን አሁን ላይ ከተሰነጠቀው የትህነግ አመራር መካከል የእነ ዶክተር ደብረጽዮን ቡድን አካል ከሆኑት ከሞንጆሪኖ ወንድም ጋርም ግንባር ፈጥረው አብረው ወደ አስመራ መሄዳቸውን መዘገባችን ይታወሳል።
ይህ ከሆነ በሁዋላ ነው የግብጽ ከፍተኛ ባለስልጣናት ወደ አስመራ ማምራታቸው የተሰማው። ምክክራቸውን አስመልክቶ ከሚወጡት መረጃዎች መካከል በቀጣናው ያለውን ወቅታዊ የደኅንነት እና የፖለቲካ ሁኔታ፣ እንዲሁም የአገራቱን ግንኙነት ማጠናከረን የሚመለከት ምክክር ማድረጋቸው ተመልክቷል
በሌሎች አገሮች መካከል በተፈጠረ አለመግባባት ሳቢያ አገራቸው የጦርነት አውድማ እንድትሆን እንደማይፈቅዱ መናገራቸውን ጋርዌይ አስነብቧል። ሚኒስትሩ በተለይም በግብፅ እና ኢትዮጵያ መካከል በአባይ ግድብ መነሻነት የተነሳውን ውዘግብ ተከትሎ ያለውን ውጥረት በማንሳት ነው አገራቸው የጦርነት አውድማ አትሆንም ያሉት።
የግብፅ ልዑካን ጉብኝትን በተመለከተ በኤክስ ገጻቸው ላይ መልዕክት ያሰፈሩት የኤርትራው የማስታወቂያ ሚኒስትር የማነ ገብረመስቀል “ግብፅ በአፍሪካ ቀንድ አለመረጋጋት የመፍጠር እና የጣልቃ ገብነት አጀንዳ ታራምዳለች የሚለው ክስ ባዶ ክስ ነው” በማለት ጉዳዩ በውይይቱ ወቅት መነሳቱን ጠቅሰዋል ጥብቅናቸውን አሳይተዋል። ግብጽ ከሶማሊያ ጋር ወታደራዊ ስምምነት ማድረጓ፣ መሳሪያ ማጋጋዟና 5ሺህ ወታደሮችን ማስገባቷን የሚያውቁት ኤርትራዊው የማነ ገብረመስቀል፣ ይህን ሲሉ ምን ማለታቸው እንደሆነ ግልጽ እንደሆነ ጥቅሰው ምላሽ የሰጡ ” ደግነቱ የአንድ ቀበሌ ሊቀውመንበር ያህል እንኳ አትሰሙም” ሲሉ አጣጥለዋቸዋል። ባንዳነትም ከደም እንደሆነ ጠቅሰው ወርፈዋቸዋል።
የሶማሊያ አጠቃላይ የግዛት አንድነት እና ሉዓላዊነት እንዲጠበቅ አብረው እንደሚሰሩ ኤርትራና ግብጽ በድጋሚ ስምምነታቸውን ሲያስታውቁ ከሶማሊያ ዘንዳ አዲስ ዜና ተሰምቷል።
የሶማሊያ ጠቅላይ ሚንስትር ሃምዛ አብዲ ባሬ መንግስታቸው ሶማሊያ በሌሎች አገሮች መካከል በተፈጠረ አለመግባባት ሳቢያ አገራቸው የጦርነት አውድማ እንድትሆን እንደማይፈቅዱ መናገራቸውን ጋርዌይ አስነብቧል። ሚኒስትሩ በተለይም በግብፅ እና ኢትዮጵያ መካከል በአባይ ግድብ መነሻነት የተነሳውን ውዘግብ ተከትሎ ያለውን ውጥረት በማንሳት ነው አገራቸው የጦርነት አውድማ አትሆንም ያሉት።
ቀጥለውም በሶማሊያ ድንበሮች ውስጥ የትኛውም የውጭ መንግስታት ወደ ጦርነት እንዲገባ እንደማይፈቀድ አስታውቀዋል። ጉዳያቸውንም ከሶማሊያ ውጭ እንዲያከናውኑ ብለዋል። ሚኒስትሩ ይህን አቋማቸውን ያስታወቁት እጅግ አፅንዖት ሰጥተው እንደሆነ በቪዲዮ የተደገፈው የጋርዌይ ዘገባ ያስረዳል።
ቀደም ሲል ትጥቅ፣ ስንቅ፣ ወታደርና አቅም እንዳላቸው ጠቅሰው ሲያስፈራሩ የነበሩት ሚኒስትሩ አቋማቸውን በዚህ ደረጃ ለማለሳለስና ግብጽን የሚጎሽም ዜና ማሰማታቸው አነጋጋሪ ሆኗል።
“ኢትዮጵያ ከሶማሊ ላንድ ጋር ያደረገችውን ቅድም ስምምነት ካልቀደደችና ህጋዊ ውል ካደረገች እንዋጋለን” በማለት በተደጋጋሚ ሲናገሩ የነበሩት ሚኒስትሩ፣ ኤርትራና ግብጽ ሲማማሉ እሳቸው በምን መነሻ አሳባቸውን ለመቀየር እንደወሰኑ በይፋ ባያስታውቁም የኢትዮጵያን በቀይ ባህር ላይ መሳተፍ በአሜሪካና እስራኤል፣ እንዲሁም እንግሊዝን የአውሮፓ ወሳኝ አገሮች ውስጥ ውስጡን ስለሚደግፉት አማራጭ ከማጣት አንጻር እንደሆነ የሚናገሩ አሉ።
ሶማሊ ላንድ የመግባቢያ ስምምነቱ በህግ ታስሮ ተግባራዊ ሊሆን መቃረቡንና እጅግ ቅርብ ጊዜ ውስጥ በውል የታሰረው ስምምነት ይፋ እንደሚሆን ባለፈው ሳምንት ማስታወቃቸው ይታወሳል። ለኢትዮጵያ አዲስ ዓመት እንኳን አደረሳችሁ ያለችው ሶማሊላንድ በዓዲስ ዓመት ያበሰረችው ዜና በሰበር መሰማቱም አይዘነጋም።
ከኢትዮጵያ በየዓመቱ 3 ቢሊዮን ዶላር የምታልበው ጅቡቲ እሪ ብትልም፣ የኢትዮጵያ ቴሌኮም የኔትዎርክ ግንባታውን እያፋጠነ ነው። ቻይና የባቡር መስመሩን በቅልጥፍና እንደምታጠናቅቅ የተገለጸ ሲሆን ወደቡን ከኢትዮጵያ ጋር የሚያገኘው የአውራ መንገድ ተጠናቆ ለስራ ክፍት ሆኗል። በይፋ አልተገለጸም እንጂ የኢትዮጵያ ባህር ኃይል ወደቡ ላይ ሰፍሯል።
አሁን በርካታ ኢትዮጵያዊያንን እያነጋገረ ያለው “ኤርትራን የሚመራው ሻዕቢያ ድሮ የፈጸመው ሳያንሰው ምን ሆኖ ነው በዚህ ደረጃ ኢትዮጵያ ላይ በዚህ ደረጃ የተነሳው” የሚለው ነው።
“ኢትዮጵያስም ሆነች ኢትዮጵያዊያን ኤርትራ እንደ አገር ራሷን ችላ ለመሄድ ስትወስን ያሉት ነገር የለም። ፍትህና ርትዕ ተዛብተው የባህር በር አላባ ሲሆኑ ችለው ዝም ብለዋል። ከለውጡ በሁዋላ በሰጥቶ መቀበል መርህ አሰብን ለመጠቀም ጥያቄ ቀርቦ ተከልክለዋል። በተቃራኒው ኢትዮጵያዊያን ለኤርትራዊያን እንደ ህዝብም ይሁን እንደ አገር አንድም ያጎደሉት ነገር የለም። ነጻነት ብለው እንዳሽቸው ኢትዮጵያ ውስጥ ሳይሸማቀቁ በሚፈልጉት ደረጃ እየኖሩ ነው። እየሰሩና እየነገዱ፣ በመንግስት ቤት እየኖሩ፣ በብር እየተገበያዩ ህይወታቸውን እያሳለፉ ነው። ይህ ሁሉ እየሆነ ስንጥር ለማይነካባቸው ህዝብ በዚህ ደረጃ ግፍ ሲፈጸም ለምን ዝም ይላሉ” በሚል ለኤርትራዊያን ጥያቄ የሚያቀርቡ ጥቂት አይደሉም።
ከምንም በላይ ኢትዮጵያ ሶማሊላንድ ሄዳ የባህር በር የጠየቀችው ተገፍታ መሆኑን እያወቁ በዚህ ደረጃ መንግስታቸው ኢትዮጵያን በማተራመስ ዘመቻ ሲሳተፍ ደጋፊ ሆነው የሚይታዩት አብዛኛ ኤርትራዊያን የኢትዮጵያዊያንን ልብ እያሳዘኑ እንደሆነም የግል ተሞክሯቸውን ጠቅሰው የጻፉ አሉ። እንደ በርካቶች እምነት ግን ኤርትራዊያን ሻዕቢያ ኢትዮጵያ ላይ እያደረገ ያለውን ሴራና ጣልቃ ገብነት ቢቻል ቢያወግዙ አለያ ግን አብረው እየኖሩ ካሉበት ህዝብ መካከል ሆነው ሻዕቢያን ከማገዝ ሊቆጠቡ ይገባል።
ሰብለወርቅ ዓለሙ የተባሉ የገርጂ ነዋሪ ” ፍቅር ይሻላል። በወያኔ ጊዜ ከሆነው እንማር። ፖለቲከኞች ባበዱ ቁጥር አብሮ ማበድ ዋጋ ያስከፍላልና” ሲሉ አስተያየት ሰጥተዋል።፡ የኢትዮጵያም ሆነ የኤርትራ ህዝብ የሚያምርበት ተከባብሮ በአብሮ መጠቅም መርህ መኖር ሊሆን እንደሚገባው. እጣ ፈንታቸውን ይህ እንደሆነ የአብዛኞች እምነት ነው።
በሌላ ተመሳሳይ ዜና አሜሪካ በሶማሊያ ምንም ዓይነት ውጊያ እንዲካሄድ እንደማትፈልግ፣ ዋና ትኩረቷ አልሸባብ እንደሆነ ጠቅሳ ለሶማሌ ባለስልጣኖች መመሪያ መስተቷን ለማይክ ሓመር የሰሞኑ ጉብኝት ቅርብ የሆኑ ነገረውናል። ይህ አቋም የኬንያም እንደሆነ ታውቋል።
አሜሪካና አጋሮቿ አቋማቸውን በዲፕሎማሲያዊ መንገድ እንዳስረዱ ነው። አገራቱ ኢትዮጵያ የባህር በር ለማግኘት እየሄደች ያለችበትን አግባብ አለሳልሰው ማየታቸው የድጋፋቸው ማሳያ እንደሆነ በርካቶች የሚስማሙበት እውነታ ነው።
በሌላ ዜና የተባበሩት መንግስታት የጸጥታ ምክር ቤት ግብጽ “ ኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ ላይ የምታደርገውን እንቅስቃሴ እንድታቆም ጫና እድርጉልኝ ” ስትል ያስገባችውን የክስ ደብዳቤ አልተቀበለውም። ምክር ቤቱ የህዳሴ ግድብን ጉዳይ ላይ ኢትዮጵያ ሰላማዊ ድርድርን ለማድረግ ፍቃደኛ ሆና ሳለች በውጥረትን መፍጠር እንደማያስፈልግ እና ጉዳዩ በአፍሪካ ህብረት በኩል ለመፍትሔው እየተሰራበት በመሆኑ እንደማይመለከተው ገልጾ ፋይሉን ዘግቷል። የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በበኩሉ የግብጽን ወታደራዊ መስፋፋት ከቀጠናው አለመረጋጋት ጋር ተጨማሪ ስጋት እንደሆነ በመጥቀስ ለጸጥታው ምክር ቤት ደብዳቤ መላኩ የሚታወስ ነው።
በቴሌግራም ይከተሉን እባክዎ https://t.me/+f_kxmaPjD-9jYTdk