ከጥቂት ቀናት በፊት በአሜሪካ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ጉዳይ ኮሚቴ የስቴት ዲፓርትመንት (የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር) መሥሪያ ቤት ኃላፊን ቃል በተቀበለበት ወቅት፣ የሕዝብ ተወካዩ ብራድ ሸርማን በአሜሪካ የሚኖሩና “በተለይ የአሜሪካ ዜግነት ካላቸው ትውልደ ኤርትራውያን የኤርትራ መንግሥት የሚሰበስበውን የዳያስፖራ ታክስ ወደ ኤርትራ እንዳይሄድ እንዴት መከልከል እንችላለን” ሲሉ የፖለቲካ ንግግር አሰምተው ነበር። “ተቃዋሚዎችን በገንዘብ እንርዳ” በሚል አስተያየት በተሰጠበት በዚህ ስብሰባ ሻዕቢያ የአፍሪቃ ቀንድ አተራማሽ እንደሆነና ሊወገድ እንደሚገባው ተመልክቶ ነበር።
የቀይ ባህር አፋሮች ድፍን የኤርትራን ህዝብ አንቆ የያዘውንና በተለይም የአፋርን ህዝብ ለይቶ ማጥቃት ባህሪው እንደሆነ፣ ከዚህም በላይ ሰፊው የአፋር ህዝብ የባሕር በር ያለው በቀጣናው ሰላም እና ዕድገት መስመጣት የሚችል ሕብረተሰብ በመሆኑ ይህንኑ ለማሳካት እንዳይችል ያደረገውን የሻዕቢያ መንግስት ነቅሎ ለመጣል ወታደራዊ አማራጭ ሊያሰፋ ጫፍ መድረሱ ተገለጸ። የትግራይ ህዝብ ነጻ አውጪ ግንባር ለሻዕቢያ ከለላ ለመስጠት የሚያደርገውን እንቅስቃሴ እንዲያቆም ጠይቀዋል።
የአፋር ህዝብ መብቶች እንዲከበሩ ላለፉት ሁለት አስርት ዓመታት ሲታገሉ ቆይተዋል። አሁን ላይ ሰፊ የትጥቅ ትግል ለማድረግ ዝግጅታቸውን ያጠናቀቁት እነዚህ ወገኖች በይፋ የቀይ ባህር አካል በመሆናቸው አሰብን ለማስመለስ እንደሚሰሩ ለኢትዮሪቪው የአዲስ አበባ ተባባሪ ገልጸዋል። በቅርቡም ወደ እንቅስቃሴ እንደሚገቡ አመልክተዋል። የትህነግና የሻእቢያ አዲስ መሞዳሞድ ይህንኑ እንቅስቃሴ ለማስተጓጎል ሻዕቢያ ያቀደው እንደሆነ ገልጸው “ይህን ጉዳይ የትግራይ ህዝብና ፖለቲከኞች ከወዲሁ ይወቁት” ብለዋል።
ኤርትራ ዉስጥ ሁሉም የሐገሪቱ ዜጎች እኩል የሚሳተፉበት ፌደራዊ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት በሚመሰረትበትና ሕገ መንግስት በሚረቀቅበት ስልት ላይ የሚነጋገር ጉባኤ ከዓመት በፊት በዩናይትድ ሐሪስበርግ- ፔንስልቬንያ፣ ዩናይትድ ስቴትስ መደረጉ የሚታወስ ነው። ይህ ጉባኤዉ ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ የሚመሩት ሥርዓት ሲወገድ አገሪቱ የምትመራበትን ፖለቲካዊ ስርዓት አስቀድሞ መቅረጽ ዋናው ዓላማው ነበር። ከዚህ ጉባዔ ጀርባ ያሉ ወገኖች በይፋ ባይገለጹም ከሻዕቢያ ወገን አሜሪካንን የመውቀስ ግብረ ምላሽ ተሰጥቶ ነበር።
በዚሁ ጉቤዔ ከ200 ሺህ በላይ ግፍና መከራ ያንገፈገፋቸው የኤርትራ አፋሮች ወደ ኢትዮጵያ፣ጀቡቲና ወደ ሌሎች አካባቢዎች መሰደዳቸው ተመልክቶ ነበር። ይህንኑ ያስታወሱት የዜናው ባለቤት ጅቡቲና የመን ያሉትን ሳይጨምር በኢትዮጵያ ብቻ ከሰባ ሺህ የሚልቁ የተመዘገቡ ኤርትራዊያን ስደተኞች በኢትዮጵያ እንዳሉ አመልክተዋል።
“በሻዕቢያ ያልተማረረ ኤርትራዊ የለም” የሚሉት እኚሁ ሰው ” ይህንን ሰው በላና ኃላ ቀር አገዛዝ ለማስወገድ። ከበቂ በላይ ምክንያት አለ። የሰው ኃይል ችግር የለብንም። ዓለምም ትግላችንን ይደግፈዋል። ትግሉ ፍትሃዊ በመሆኑ የሎጂስቲክ ችግርም የለብንም። አሁን ወደ ተግባራዊ እንቅስቃሴ ለመሸጋገር ጫፍ ላይ ነን” ብለዋል።
ድርጅቱ ባለፈው ኦገስት መጨረሻ አዲስ አበባ ባካሄደው ድርጅታዊ ጉባዔ በኢትዮጵያ፣ ጅቡቲ እና የመን የሚገኙ የቀይ ባሕር አፋር ስደተኞች መብት እንዲከበርላቸው ጠይቆ ነበር። ከጉባኤው በሁዋላ ባወጣው መግለጫ የኤርትራን መንግሥት በማንኛውም ሁኔታ ከስልጣን ለማንሳት አቋም መያዙን በይፋ አስታውቆ እንደነበር ይታወሳል።
“የቀይ ባሕር አፋር ሕዝብ የባሕር በር ያለው በቀጣናው ሰላም እና ዕድገት መስመጣት የሚችል ሕብረተሰብ በመሆኑ ትኩረት ተሰጥቶ መብቶቹ እንዲከበሩ” በመግለጫው ጠይቆ ድጋፍ እንዲደረገለትም አሳስቦ ነበር።
የኤርትራን መንግስት በፖለቲካ እና ወታደራዊ አማራጮች የሚታገል መሆኑን የሚገለጸው ይህ ድርጅት፣ ዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ ለስደተኛ ኤርትራዊያን ጥገኝነት ጠያቂዎች ሕጋዊ ከለላ እንዲያገኙ እንዲያስችል፣ የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ማስተባበሪያ ቢሮም እነዚህን ስደተኞች ኑሮ መስርተው ሊኖሩ ወደሚችሉባቸው ሦስተኛ ሀገራት እንዲያዘዋውር የድርጅቱ የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል የሆኑት አቶ ያሲን መሐመድ አብደላ መጠየቃቸውን መግለጫውን የተከታተሉ ዘግበው ነበር።
ከሌሎች የኤርትራ የተቃዋሚ ኃይሎች ጋር በቅርብ መስራት መጀመሩን ያወሱት ዜናውን ያቀበሉን እንዳሉት አብሮ ለመስራትና ሻእቢያን ለማስወገድ ስምምነት ላይ ተደርሷል። ድጋፍ ስለሚያደርጉላቸው ወገኖችና አብረዋቸው ስለሚሰሩት ክፍሎች ብዙም መናገር ያልፈለጉት የቀይ ባህር አፋሮች ዴሞክራሲያዊ ድርጅት የቅርብ ሰው ” በምንም ይሁን በምን ቀኑ ደርሷል” ብለዋል። “ግን” አሉ “ግን አስገራሚው ጉዳይ የትህነግ የፖለቲካ አቋምና የሻዕቢያ አጋር ለመሆን በትግራይ ህዝብ መነገዱ ነው”
የባድመና ዛላንበሳው ወረራና ዕልቂት ቢቀር በቅርቡ አጋጣሚውን ተብቆ ሻዕቢያ ትግራይን ወሮ በትግራይ ምስኪኖች ላይ የፈጸመውን ግፍ፣ እልቂት፣ ዘረፋ፣ አስገድዶ መድፈርና የጅምላ ጭፍጨፋ የሚያስታውሱ የእነ ዶክተር ደብረጽዮን ቡድን ከሻዕቢያ ጋር አብሮ መስራት መጀመሩ የተዓምር ያህል እንደሆነባቸው በተለያዩ የማህበራዊ ገስ አውዶች እየገለጹ ነው።
የአፋር ህዝብ ንቅናቄ ሻዕቢያ ላይ ሊወስድ ያሰበውን የተባበረ ጥቃት ለማስተጓጎል ትህነግ ከሻዕቢያ የቤት ስራ መውሰዱን እንደሚያውቁ የገለጹት የዜናው ባለቤት፣ ” ይህን ጉዳይ የትግራይ ህዝብ ሊያውቀው ይገባል። ለዕውነት የቆሙ ሚዲያዎች ይህን ክህደት ለትግራይ ህዝብና ፖለቲከኞች ማስገንዘብ ይገባቸዋል። ትግሉ ጫፍ ስለደረሰ የሚቀይሩት ጉዳይ ባይኖርም ምስኪኑን ህዝብ እንዳያሰቃዩት ከወዲሁ ተው ሊባል ይገባል” ሲሉ አስገንዝበዋል።
ሻዕቢያ ለሶማሌ ወታደር ባማስለጠን የምስራቁን የኢትዮጵያ ክፍል ለማተራመስ በስፋት እየሰራ መሆኑ ያታወቃል። በኢትዮጵያ ብረት ያነሱ ሃይሎችን ማሰልተንና ማስታጠቅ መለያው የሆነው ሻዕቢያ፣ ከሽብር ቡድኖች ጋር ግንኙነት እንዳለው ተተቅሶ በአሜሪካ መንግስት ከቀድሞ የበለጠ እርምጃ እንዲወሰድበት ጥያቄ እየቀርበበት ባለበት በአሁኑ ሰዓት ይህ ዜና መሰማቱ ነገሩ መካረሩን የሚያሳይ ነው።
ከጥቂት ቀናት በፊት በአሜሪካ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ጉዳይ ኮሚቴ የስቴት ዲፓርትመንት (የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር) መሥሪያ ቤት ኃላፊን ቃል በተቀበለበት ወቅት፣ የሕዝብ ተወካዩ ብራድ ሸርማን በአሜሪካ የሚኖሩና “በተለይ የአሜሪካ ዜግነት ካላቸው ትውልደ ኤርትራውያን የኤርትራ መንግሥት የሚሰበስበውን የዳያስፖራ ታክስ ወደ ኤርትራ እንዳይሄድ እንዴት መከልከል እንችላለን” ሲሉ የፖለቲካ ንግግር አሰምተው ነበር። “ተቃዋሚዎችን በገንዘብ እንርዳ” በሚል አስተያየት በተሰጠበት በዚህ ስብሰባ ሻዕቢያ የአፍሪቃ ቀንድ አተራማሽ እንደሆነና ሊወገድ እንደሚገባው ተመልክቶ ነበር።
የኤርትራ መንግስት ተቃዋሚ የሆኑትና ራሳቸውን ብርጌድ ንሀመዱ ብለው የሚጠሩት ሀይሎች ወታደራዊ ዝግጅታቸውን እንዳጠናቀቁ በሚሰማበት ወቅት የቀይ ባህር አፋር ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት ይህን መረጃ መስጠቱ ተገጣጣሚ ጉዳይ ስለመሆኑ መረጃውን ያካፈሉን ያሉት ነገር የለም።
በሌላ ዜና አብዛኛውን የሱዳን ክፍል እየተቆጣተሩ ያሉት ጀነራል ሃምዳን ደጋሎ ግብፅን አስጠንቅቀዋል። የግብፅ መንግስት የአፍሪካ ቀንድን ወደ አስከፊ ጦርነት ለማስገባት እየሄደበት ያለው የአታራማሽነት ተግባር እንዲቆጠብ የሱዳን ፈጣኖ ደራሽ ሃይሎች ዋና አዛዣ ጀነራል መሐመድ ሃምዳን ደጋሎ ማስጠንቀቃቸው ለሻዕቢያ መርዶ ሆኗል።
ጀነራል ሃምዳን በትናንትናው በአማካሪያቸው በኩል በኩል ባስተላለፉት መልዕክት ግብፅ እዬሄደች ያለችው መንገድ የአፍሪቃ ቀንድን ይበልጥ እንደሚያቃውስ አስጠንቅቀዋል። ግብጽ በጄኔራል አብዱልፈታህ አል ቡርሃን ደጋፊ ብትሆንም በጦርነቱ አሳቧ ላተሳካላትም። ኢትዮጵያን ለማስፈራራትና ጣልቃ ለመግባት ጦሯን ሱዳን አስገብታ በነበረበት ውቅት የሃምዶም ኃይሎች እርምጃ ውስደው ክፉና ጉዳይ እንዳደረሱባት አይዘነጋም። በርካታ ምርኮኞች ይዘው በመስል ሲያሳዩም ነበር።
የአልሲሲ መንግስት በኢትዮጵያ ላይ የሚያሰማው የጦርነት ጉሰማ ተቀባይነት የለውም በማለት ሄማቲ አቋማቸውን ይፋ አድርገዋል። ጀነራል ሃምዳን ግብፅ ቀድመውኑ ደካማ የሆነውን የአፍሪካ ቀንድን የበለጠ መረጋጋት እንዲያጣና እንዳይረጋጋ እየሰራች እንደሆነ ገልጸው ተቃውመዋል። ሃምዳን ይህ ሲሉ ስለ ሻዕቢያ ያሉት ነገር የለም። ሻዕቢያም ሆነ ትህነግ እንደ ወትሮው ኢትዮጵያን ከሱዳን እንድተጠቃ ለማድረግ አሁን ላይ አመቺ ሁኔታ እንደሌለ በተደጋጋሚ መገለጹ የሚታወስ ነው።