የተያዙ ኢግዚቢቶች በአይነት እና በመጠን በአጠቃላይ 176,881.61ግራ ምኮኬን፣ 924,450 ግራም ካናቢስ፣ 32,100.89 ግራም ሄሮይን፣ 5,089 ግራም ሄሮይን እና ሞርፊም መሆናቸው ታውቋል።
በ1996 የወጣውን የወንጀል ሕግ አንቀፅ 525 ንዑስ አንቀፅ 1(ለ)ሥር የተደነገገውን በመተላለፍ በአደገኛ ዕፅ ዝውውር ወንጀል ጥፋተኛ የተባሉ ግለሰቦች ከ2 ዓመት እስከ 12 ዓመት በሚደርስ ፅኑ እስራት መቀጣታቸው ተገለጸ።
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ጠቅላይ መምሪያ እንዳስታወቀው በ2016 በጀት አመት በዕፅ ዝውውር ከደረሱ ጥቆማዎች መካከል ጠቅላይ መምሪያው የምርመራ መዝገቦችን በሰውና በሰነድ አጣርቶ ለዓቃቤ ሕግ ከላከው መዝገቦች ውስጥ ፍርድ ቤት ጥፋተኛ ናቸው ብሎ ውሳኔ ያስተላለፈባቸው፤
1. ሚ/ር ቺቡኬ ዳንኤል፡- 12 አመት ፅኑ እስራት እና 4,000 ብር መቀጮ፣
2. ሚ/ር ኢጎር ዲማቶስ ዱትራ፡-3 አመት ከ9 ወር ፅኑ እስራት እና 3,000 ብር መቀጮ፣
3. ሚ/ር ሉዊስ ሚጎል ኮናሮጂ፡- 4 አመት ፅኑ እስራት እና 4,000 ብር መቀጮ ፣
4. ሚ/ር ኬብሮም ሙንዲሀኪ ፡- 4 አመት ፅኑ እስራት እና 2,000 ብር መቀጮ፣
5. ሚ/ር ሳንጀብ ሙክርጂ ፡-6 አመት ከ6 ወር ፅኑ እስራት እና 7,000 ብርመቀጮ፣
6. ሚ/ር ሚስ ጊርሊዬ አሚ፡- 3 አመት ፅኑ እስራት እና 3,000 ብር መቀጮ፣
7. ሚስ ሄልቪ አልቫላ ፡- 5 አመት ከ6 ወር ፅኑ እስራት እና 5,000 ብር መቀጮ፣
8. ራሄል ለገሰ ፡-3 አመት ፅኑ እስራት 3,000ብር መቀጮ፣
9. ተስፋነሽ አለንሳ፡- 3 አመት ብር ፅኑ እስራት እና 3,000 ብር መቀጮ ፣
10. ሚስስ ፑርናማ ጊታ፡- 15 አመት ብር ፅኑ እስራት እና 3,000 ብር መቀጮ፣
11. ሚስ ናፈትፓት ኑአመንሮም፡- 4 አመት ከ 5 ወር ፅኑ እስራት እና 5,000 ብር መቀጮ፣
12. ሚስ ዚቱየትነህ፡- 5 አመት ፅኑ እስራት እና በብር 3,000 ብር መቀጮ፣
13. ሚ/ር ማርክ ፖወሊኮወ፡-5 አመት ከ 6 ወር ፅኑ እስራት እና 5,000 ብር መቀጮ፣
14. ሚ/ር ኢማኑኤል ኡዙቸክው፡-6 አመት ፅኑ እስራት እና 8,000 ብር መቀጮ፣
15. ባህሩ ወልዴ፡- 12 አመት ፅኑ እስራት፣
16. ሚ/ር አስዋልደረፋይል ሄርና፡- 4 አመት ፅኑ እስራት እና 3,000 ብር መቀጮ ፣
17. ታምሩ ፍቅሬ፡- 12 ዓመት ፅኑ እስራት እና 4,0000 ብር መቀጮ፣
18. ግሬስ አዋርድር፡- 2 አመት ከ9 ወር ፅኑ እስራት እና 3,000 ብር መቀጮ፣
19. ሚስ ዜመዬ አዩን፡- 5 አመት ከ6 ወር ፅኑ እስራት እና 3,000 ብር መቀጮ፣
20. ሚ/ር ሞሀመድ ሳሉሞኪላማ፡- 6 አመት ፅኑ እስራት እና 5,000 ብር መቀጮ፣
21. ሚ/ር ሩአንደርሰደ ሰመዝ፡- 3 አመት እስራት ፅኑ እስራት እና 3,000 ብር መቀጮ፣
22. ሚ/ር አሊዬ አቡዋ፡-4 አመት ፅኑ እስራት እና 2000 ብር መቀጮ፣
23. ሚስ ቻኒካን ቡናሙኤን፡- 3 አመት ፅኑ እስራት እና 3,000 ብር መቀጮ፣
24. ሚስስ ቱርናማ ጊታ ሳሪ፡-4 ዓመት ፅኑ እስራት እና 5,000 ብር መቀጮ ናቸው።
የተያዙ ኢግዚቢቶች በአይነት እና በመጠን በአጠቃላይ 176,881.61ግራ ምኮኬን፣ 924,450 ግራም ካናቢስ፣ 32,100.89 ግራም ሄሮይን፣ 5,089 ግራም ሄሮይን እና ሞርፊም መሆናቸው ታውቋል።
ግለሰቦቹ ዕፁን ለማዘዋወር የሚጠቀሙባቸው መንገዶች በሰው አካል ውስጥን ጨምሮ በሻንጣ ውስጥ፣ በጫማ ሶል፣ ወፍራም ልብስ በማስመሰል በመልበስ፣ በተለያየ የመኪና አካል ውስጥ፣ በሻንጣ መጎተቻ ብረት ውስጥ በመበየድ እና በሌሎችም መንገዶች እንደሆነ የወንጀል ምርመራ ቡድኑ አረጋግጧል።
የዕፅ የአዘዋዋሪዎቹ ሀገራት:- ናይጀሪያ፣ ኢትዮጵ፣ ብራዚል፣ ታይላንድ፣ አንጎላ፣ ታንዛኒያ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ቪንዙዌላ፣ ቤኒን፣ ካሜሮን፣ ናሚቢያ፣ ኮንጎ፣ ኡጋንዳ፣ ኬኒያ፣ ቦሊቪያ፣ ፖላንድ፣ ጀርመን፣ ሴንትራል አፍሪካ፣ ህንድ፣ ቱኒዚያ፣ ኢንዶኒዥያ፣ ማላዊ፣ ጅቡቲ፣ ካናዳ፣ ሞዛምቢክ እና ተርክዬ መሆኑ ታውቋል።
የአደገኛ ዕፅ አዘዋወሪዎቹ መነሻ ብራዚል (ሳኦፖውሎ)፣ ደቡብ አፍሪካ (ጆሃንስበርግ)፣ አዲስ አበባ፣ አንጎላ ታንዛኒያ፣ ኬኒያ እና ሌሎች ሀገራት ሲሆን መዳረሻቸው ደግሞ ናይጀሪያ (ሌጎስ)፣ ደቡብ አፍሪካ (ጆሃንስበርግ)፣ ህንድ፣ ዱባይና ታይላንድ መሆናቸው የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ አስታውቋል።
የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ ድንበር ተሻጋሪ ወንጀል ችሎት 24 የምርመራ መዝገቦችን መርምሮ በሕግ የተከለከሉ ዕጾችን የማዘዋወር ወንጀል የፈፀሙ ተከሳሾችን ያርማል፤ ሌሎችን ያስተምራል በማለት ከ2 ዓመት እስከ 12 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲሁም ከ2 ሺህ ብር እስከ 8000 ብር የገንዘብ መቀጮ ተወስኖባቸዋል። በተመሳሳይ ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር በዋሉት ላይም ምርመራው ተጠናክሮ መቀጠሉን በመረጃው ኢ ፕ ድ ዘግቧል።