ከዳንግላ ወህኒ አስፈትተህ ፣ የጎንደርን ፎርጅድ መታወቂያ አሰርተህ ፣ እስከ ትግራይ ወሰን ድረስ ሸኝተህ ከለቀቅከው የወያኔ ሻለቃና ኮሎኔል ጋር ያደረከውን ውል እኛ ስለማናውቅ ስለ ውሉ ሹክ የሚለንን ፍለጋ ላይ ነን …
“እመነኝ” ይላል ሻዕቢያን ከድቶ ዛሬ ህይወቱን በዱባይ እየመራ ያለው ሙሴ ሰናይ (ስም የተቀየረ) ” ብታምንም ባታምንም ሻዕቢያ ከወያኔ በላይ ወልቃይት ጠገዴን ይፈልጋል”። ሙሴ መረጃው የቅርብ እንደሆነ ከተረዳ በሁዋላ በስፋት አነጋግሮት መረጃውን ለኢትዮ ሪቪውን የላከው ተባባሪ እንዳለው አሁን ላይ በአማራ ክልል ላይ ያሉ ኃይሎች የጀርባ ውል ማሰራቸውን ያውቃል።
ለመነሻ እንዲሆን ትህነግ በወልቃይት ጠገዴ ላይ ያለውን አቋም ማስታወስ እንደሚበጅ የሚገልጸው ሙሴ በጦርነቱ ወቅት ከኤርትራ አዲስ አበባ ተልኮ የከፍተኛ መኮንነት ስራ ሲሰራ ቆይቶ መንግስት ” አሁን በመኮንነት ደረጃና በድህንነት ረገድ የሚደረገው ድጋፍ በቃኝ” ማለቱን ተከትሎ ወደ ኤርትራ ከመመለስ ይልቅ ወደ ዱባይ አቅንቶ እየኖረው ነው።
“በደንብ እየተዋወቅን መምጣታችን ጥሩ ነው” ጋሻው መርሻ
ጎንደር ውስጥ የሰሊጥ እርሻ የብልፅግና ኢንቨስሮች ነው እንዳይሰበሰብ ማለት ጎጃም ውስጥ ጤፍ እና በቆሎ፣ አርሲ እና ባሌ ስንዴ፣ ወሎ ማሽላ፣ ሸዋ ጤፍ የብልፅግና ኢንቨስተሮች ምርት ስለሆነ እንዳይሰባሰብ እንደማለት ነው።
ከቋራ እስከ ሁመራ ከ500 ኪ.ሜ በላይ በተዘረጋው የቆላ ማሳ ውስጥ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ድሃ ገበሬዎች የሰሊጥ ምርት ሳይሰበሰብ እንዲቀር ይህን ያክል መጨከን ግን ምንኛ ወያኔያዊ ምቀኝነት ነው። የኢንቨስተሮቹስ ቢሆን ስለምን ሜዳ ይብላው? እንደ ጎንደር ተወላጅነቴ ይኸ ጉዳይ እጅጉን ይገደኛል።
አንባቢ ሆይ በዚህ ጉዳይ ላይ ረጅም መጣጥፍ ከፈለክ ከሁለት ዓመት በፊት ሰሊጥ ለመሰብሰብ ወደ ጎንደር እንዳትሄዱ ብልፅግና ለውትድርና ያፍሳቹሃል በተባለ ጊዜ የጻፍኩትን ማንበብ ትችላለህ።
በእርግጥ በደንብ እየተዋወቅን መምጣታችን ጥሩ ነው። አንድ የሚገርመኝ ነገር ግን ወያኔዎች እንዴት እንደተሳካላቸው ብቻ ነው። መቀሌ ብቻ ነው አልሆንላችሁ ያላቸው።
ሙሴ ተቀማጭነታቸው አዲስ አበባ ከሆነ የኤርትራ ዲፕሎማቶች ጋር አብሮ ወደ ባህር ዳር በተደጋጋሚ መጓዙንና በዛ ያለውን ኃይል በማደራጀት ረገድ ሲሰራ የነበረውን ስራ ያውቃል። ስም ጠርቶ ግንኙነቱን ይፋ አያደርግም እንጂ የኤርትራ ዲፕሎማት ባህር ዳር እየተመላለሱ መዋቅር ሲዘረጋ ይሳተፉ ነበር። መንግስት አካሄዱን ተረድቶ ከሻዕቢያ የበላይ አመራሮች ጋር መነጋገር፣ ዲፕሎማቱንም በግልጽ ማወያየት በጀመረ ሰሞን ግጭቱ እንደገነፈለ ሙሴ ይተርካል።
የሙሴ መረጃ አማራ ክልል ላይ መፍንቅለ መንግስት ለማካሄድ ዕቅድ እንደነበር መንግስት አሰቅድሞ ማወቁን ጠቅሶ ለሰጠው መረጃ ማረጋገጫ ሆኗል። ኢትዮጵያና ኤርትራ መካከል የነበረው ጸብ በተወገደ ማግስት ሻእቢያ አማራ ክልል ላይ ትኩረት አድርጎ እንደነበር የሚገልጸው ሙሴ፣ መንግስት የኢኮኖሚ ግንኙነቱ በውል ይታሰር የሚል አቋሙን በፍጥነት እንዲቋጭ ግፊት ማድረጉ ሻዕቢያን እንዳላስደሰተ ይናገራል።
የኢትዮጵያን እጅ ለመጠምዘዝ ተቃዋሚ ማደረጃት የሻዕቢያ ዋና ተገባር እንደሆነ ሙሴ የሚገልጸው ኤርትራ ውስጥ ተቀምጠው የትጥቅ ትግል እዲያደርጉ ሲሰለጥኑ፣ ሲታጠቁና ሲሰማሩ የነበሩትን ነጻ አውጪ ድርጅቶች በመዘርዘር ነው።
አንዳንዴ ጥንቃቄ የሚመርጠው የሙሴ መረጃ በግልጽ በማይታወቅ ኩርፊያ ሻዕቢያ ላይ ጥላቻ እንዳለው ያሳብቅበታል። ወደ ዋናው ጉዳይ ሲመለስ ሻዕቢያ በመጀመሪያ ያደራጀው ጎጃም ውስጥ የሚገኙትን ኃይሎች እንደሆነ ይገልጻል። ምክንያቱም በጎንደር በኩል ያሉት ወልቃይት ጠገዴን አስመልክቶ አቋማቸው ግልጽ ስለሆነና ሻዕቢያ በይፋ በዚህ መልኩ ካወያያቸው ነገሩ በጥሬው እንዳይበላሽ ሰግቶ ነው።
በጎጃም አካባቢ የተሰራውን መዋቅር በዘመድ አዝማድና ቤተሰብ ተዋረድ እንዲሆን ሻዕቢያ የራሱን የድሮ የአዲስ አበባ ውስጥና የተለያዩ ከተሞች አደረጃጀት ተግባራዊ በማድረጉ እንቅስቃሴው በአጭር ጊዜ እስከ ገበሬ ማህበር ሊደርስ እንደቻለ የሙሴ ማብራሪያ ያስረዳል።
ሻዕቢያ ትህነግ ከወልቃይት ጠገዴ እንዲለቅ ሲደረግ ተባባሪ እንደነበር ሙሴ ያውቃል። ትህነግ ወደ ወልቃይት ለመመለስ ሲያስብም ከሁዋላ ሆኖ ያጠቃው እንደነበር ይመስክራል። በተለይም በከፍተኛ ደረጃ የተገነባውን ምሽግ ከጀርባ ሆኖ በመድፍ በመነረት ያፈርሰውና ከፊት የአማራ ኃይሎችና መከላከያ እንዲያጠቁ ድጋፍ ማደረጉን ያስታውስና ይህ የሆነበትን ምክንያት ያስረዳል።
በጦርነቱ ወቅት ቤተሰቧቿ ጋር የነበረች አንድ ጋዜጠኛ የትህነግ ከባድ ይዞታና ምሽግ አለበት ከሚባለው ኤርፖርት ጀርባ ከፍተኛ የሆነ የመድፍ ድምጽ ይሰማ እንደነበር ምስክርነት መስጠቷ የሚታወስ ነው።
በስም የሚታወቁ ጀነራል መኮንኖችን ጠርቶ አስመራ ድረስ በመሄድ መምከራቸውን በመግለጽ ሻዕቢያ በየትኛውም ሂሳብ ትህነግ ዳግም ወልቃይት ጠገዴ እንዲገባ ፍላጎት እንደሌለው ሙሴ ያስረዳል። በወልቃይት ጠገዴ በኩል የኤክስፖርት ሰብሎችን ለማጓጓዝና ገቢ ለማግኘት ዕቅድ ስላለው፣ ትህነግ ዳግም ወደ ወልቃይት ጠገዴ ከተመለሰ የመውጫ ኮሪዶር በማግኘት አቅሙን አጎልብቶ ዳግም ሊፈትን እንደሚችል ፍርሃቻ ስላለው፣ ኢትዮጵያ መስመሩን ተቆጣጥራ ከሱዳን ጋር ሰላም ከሆነች ሻዕቢያን ለማጥቃት መንደርደሪያ ስለሚሆናትና በመስለ ፖለቲካዊ ጉዳዮች ሻዕቢያ ወልቃይት ጠገዴን ከወያኔ በላይ ይፈልጋታል።
ስማቸውን ከጠራቸው ጀነራል መኮንኖች ጋር ምን ተወያዩ ለሚለው፣ ውይይቱን ቃል በቃል እንዳልሰማ ሙሴ ይጠቅሳል። ውይይቱን ዝርዝር ባይሰማውም ወደ ባህር ዳር በተደጋጋሚ ሲጓዙ አካሄዱ አማራ ክልል ላይ ጠንካራ ሻዕቢያ የሚመራው ኃይል ማደራጀት እንደነበረ እውቀቱ ስላለው የሚነጋገሩት ስለምን እንደሆነ ጥርጥር የለውም። ከተመደበበት ስራ ውጭ ባህር ዳር ሲመላለስ በነበረበት ወቅት ከብልስግና መዋቅር ሰዎች ጋር ስሙን መጥቀስ በማይፈልገው አንድ ሆቴል ይመክሩ እንደነበርም አልሸሸገም።
አሁን ላይ መጠላለፍ እንዳለ የሚናገረው ሙሴ ወያኔዎቹ የጎጃሙን ቡድን እንደቀረቡት ስምቷል። በሚኖርበት ዱባይና በሌሎች አገራት ንግግር አድርገዋል። የጎንደር አካባቢዎቹ ተፋላሚዎች በወልቃት ጠገዴ ጉዳይ ከትህነግም የቀረበላቸውን ጥያቄ “ህዝብ ምን ይለናል” በሚል ውድቅ ማድረጋቸውን በስልክ የሚገናኘው አንድ ወዳጁ አጫውቶታል።
ወያኔ ከጎንደር ይልቅ የጎጃም ሰዎችን ይቀርብ እንደነበር፣ አብሯቸውን በሽርክና ይነገድ እንደነበርና በድርጅትም ከፍተና መዋቅር ስላለው በጎጃም ግንኙነቱን ለመመጠግን የቀደምውን ይህንኑ መዋቅሩን ውጭ አገር ባሉ ባለሃብቶችና መስለ አካላት መጠቀሙን ሻዕቢያ እንደሚያውቅ ሙሴ ዱባይ ከገባ በሁዋላ መስማቱን ይገልጻል።
“ማንም አካል በአማራ ክልል ውስጥ ሆኖ ከትህነግ ጋር አብሮ የጠብ መንጃ ትግል ለማድረግ ከወሰነ መጀመሪያ የሚያደርገው አንድ ነገር ነው። እሱም ወልቃይት ጠገዴ ሴቲት ውይም መእራብ ትግራይ የሚሉት የአማራ ክፍል ላይ የትህነግን ፍላጎት ለማሳካት ቅድሚያ መስማማት ነው” በሚል ስጋት የገባቸው በተደጋጋሚ ሲያነሱ ይደመጣል። አሁን “ጥምረት ፈጥረዋል” የሚባሉት ጎጃም ውስጥና ጎንደር ኩታ ገጠም ብቅ ጥልቅ የሚሉት የፋኖ ሃይል አመራሮች ምን ዓይነት ቅድመ ስምምነት እንዳደረጉ ለማወቅ ነብይ መሆን እንደማያስፈልግ የሚጠቀሰውም ለዚህ ነው። ሙሴም ይህን ይቀበላል።
ስለ ወልቃይት አበክሮ መረጃ የሚያነፈንፈው አስፋው አብርሃ በቴሌግራም ገጹ የጎጃም ፋኖ ምክትል ሰብሳቢ አስረስ ዳምጤ ከመሳይ መኮንን ጋር ያደረገውን ቃለ ምልልስ ድምጽ ለጥፎ በሰጠው አስተያየት ላይ እንደታየው ከላይ ያለውን መረጃ የሚያጠናክር ሆኗል።
“አስረስ ማረ ዳምጤ ሆይ” ይላል የወልቃይት ተሟጋች አስፋ። ይቀጥልና “….ዝምታችን ለሌላ አልነበረም እኮ። አያያዛችሁን አይተን ይኼንን እንደምታሰሙን ስንጠብቅ ስለነበር ብቻ ነው።እውነት ለመናገር አላሰፈራችሁንም – እንደጠበቅነው ይኼው አሰማችሁን” ሲል ወልቃት ላይ ከጀርባ ንግግር እንዳለ ይፋ አድርጓል።
“ድሮዉንም ወልቃይት ጠገዴ ለጎንደር እንጂ ለኛ ምናችን ነው ? ስትሉ ነበር እኮ፣ ጥሞና ውስጥ እንድንገባ ያደረጋችሁን። 500 ሺህሲደመር የወልቃይት ህዝብ የሚተዳደረው በእርሻ መሆኑ ጠፍቶህ ነው አይባልም መቼም ።እሺ ሌላ ምን አለውና ነው ?” ሲል የሚጠይቀው አስፋው ይህን ያነሳው አስረስ ” የደረሰው ሰሊጥ ነው” በማለት ውጊያ መካሄዱ በምርት መሰብሰብ ላይ ችግር እንደማይፈጥር፣ እንዲያውም የሰሊጥ እርሻው ባለቤቶች የብልጽግና ካድሬዎች እንደሆኑ ጠቅሶ በመናገሩ ነው።
“የአርሶ አደር ልጅ ስለሆንክ ከምታውቀው ሁሉ ጨልፈህ ስላጋራኸን እያመሰገንን፣ እንደው ግን አንተን የመሰለ የአርሶ አደር ልጅ ከ450 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት እንዲሁ “መና ይቅር” እንድትል ያስጨከነህ ምን የሚሉት ጥላቻና “ኮምሌክስ” ቢጣባህ ነው?” በሚል የደረሰው ሰሊጥ ላይ የጎጃም ፋኖ የያዘውን አቋም አውግዞ አመልክቷል። አያይዞም “ዝግጁ ነን” ብሏል።
አስረስ የአርሶ አደር ልጅ መሆኑንን ገልጾ መስከረም ሃያዎቹ ላይ እንደሚገኙ ያስታውቃል። መሳይ ለጠየቀው ሲመልስ አሁን የሚሰበሰበው ሰሊጥ ብቻ እንደሆነ ይናገራል። አብዛኞቹ ጠቃሚ ምርቶች የሚሰበሰቡት አሁን እንዳልሆነ ከገለጸ በሁዋላ ግለሰቦች አጀንዳ ያደረጉት የሰሊጥ ምርትን መሆኑንን ደግሞ ይናገራል። እሱም ቢሆን የሰሊጡ እርሻው የብልጽግና ካድሬዎች፣ የኢንቨስተሮችና ውጭ አገር ያሉ ይህን ጉዳይ የሚያራግቡ ያላቸው አክቲቪስቶች መሆኑን አክሎ ትግሉ አርሶ አደሩን እንዳላስተጓጎለ የሚያመለልክትበት ቃለ ምልልስ ነው ለአስፋውና ወልቃይት ጠገዴ ነዋሪዎች ቁጣ መነሻ የሆነው።
አስፋው “የእኛና የእነሱ” አይነት ውሰጠ ወይራ ተውኔት መጫወትክንም ልብ ብለናል” ሲል አስተያየቱ አስፍሯል። ይህን ተከትሎ በውልቃይት ጠገዴ ሴቲት ሁሉም ራሱን አንቅቶ እየጠበቀ እንደሆነ ተሰምቷል።
“ከዳንግላ ወህኒ አስፈትተህ ፣ የጎንደርን ፎርጅድ መታወቂያ አሰርተህ ፣ እስከ ትግራይ ወሰን ድረስ ሸኝተህ ከለቀቅከው የወያኔ ሻለቃና ኮሎኔል ጋር ያደረከውን ውል እኛ ስለማናውቅ ስለ ውሉ ሹክ የሚለንን ፍለጋ ላይ ነን” ሲል አስፋው አከታሎ ምላሽ ሰጥቷል። አስፋው ብቻ ሳይሆሆን ቃለ ምልልሱ ወልቃይትን ገጸበረከት ለማድረግ እየተማማሉ ያሉ ኃይሎ ስለመኖራቸው ሲነገር የነበረውን እንዳጸናላቸው የሚመለከታቸው በስፋት እየተናገሩ ነው። ነገሩ “እኛም አውቀናል ጉድጓድ ምሰናል” ይሆን?
ተጨማሪ ይህን ያንብቡ