የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ባለቤታቸውን አስከትለው ሩሲያ ገብተዋል። እሳቸውን ጨምሮ በርካታ መሪዎች የሚገኙበትና ካዛን በሚካሄደው የብሪክስ 2024 ጉባኤ በርካታ የሚጠበቁ ውሳኔዎችን ያሳልፋል ተብሎ ይጠበቃል።
16ኛው የብሪክስ ጉባኤ ከጥቅምት 12-14 በሩሲያ ካዛን የሚካሄድ ሲሆን ስብሰባ ህብረቱ እግሩን በጥልቅ መተከል ከጀመረ በሁዋላ የሚካሄድ እንደሆነ ተነጓል።
ይህ ለግብፅ፣ ኢትዮጵያ፣ ኢራን፣ ሳዑዲ አረቢያ እና አርብ ኤምሬትስ የመጀመሪያ የሆነው ጉባኤ ህያ አራት የአገር መሪዎች፣ 24 የሀገር መሪዎችን ጨምሮ ከ32 በላይ ሀገራት እንደሚሳተፉበት ማረጋገጫ ሰጥተዋል። ሁሉም የብሪክስ አባላት የሚሳተፉ ሲሆን ዘጠኝ ሀገራት መሪዎቻቸውን ይልካሉ። ሳዑዲ አረቢያ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ ትወከላለች።
ጉባኤው በሁለት አጀንዳዎች ተከፋፍሎ ይካሄዳል። የመጀመሪያው (ከጥቅምት12-213) “የባለብዙ ወገን ግኑኝነትን ፍትሃዊ የዓለም ልማትና ደህንነትን ለማጠናከር” በሚል መሪ ሃሳብ ላይ ያተኩራል። ሁለተኛው (ከጥቅምት 13-14) “የብሪክስ እና ደቡባዊ ዓለም ሀገራት: የተሻለ ዓለም ግንባታ” በሚል ሃሳብ ዙሪያ ያጠነጥናል፡፡
በቀጥየም ጉባኤው አዳዲስ አባላት ሊሆኑ የሚችሉ ሃገራት ጉዳይ ላይ ይወያያል። 34 ሀገራት የብሪክስ አባል ወይም አጋር ሀገር ለመሆን ፍላጎት እንዳላቸው ገልጸዋል።
የሩሲያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ከቻይናው አቻቸው ሺ ጂንፒንግ፣ የህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ እና የቱርክ ፕሬዝዳንት ሬቼፕ ጣይብ ኤርዶጋንን ጨምሮ ከ20 በላይ የሁለትዮሽ ስብሰባዎችን ያደርጋሉ፡፡ ሲያበቃም በጉባኤው ማጠቃለያ ተሳታፊ ሀገራት የጋራ መግለጫ ያወጣሉ።