የትግራይ ህዝብ ነጻ አውጪ ግንባር / ትህነግ ያደራጀውን ሰራዊት መቀለብ እንደተሳነው በክልሉ ከሚነቀሳቀሱ ተቃዋሚዎች መካከል በተለይ ለኢትዮ ኢንተርቪው ገለጹ። የፌደራል መንግስት በከፍተኛ ተማጽኖ የስንዴ ድጋፍ መስጠቱንም እነዚሁ ወገኖች አስታውቀዋል።
አቶ ጌታቸው ረዳ ወደ ስልታን ከመጡ በሁዋላ የክልሉን በጀት የሰራዊት ደሞዝ ለመክፈል ማዋላቸውን ማስታወቃቸው አይዘነጋም። 270 ሺህ የሚጠጋ ሰራዊት እንዳለም በወቅቱ ተናግረው ነበር።
ሰሞኑን በክልሉ ካሉት አጠቃላይ 2ሺ 492 ትምህርት ቤቶች ውስጥ የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት ከተፈጸመ በኋላ የመማር ማስተማር አገልግሎት የሚሰጡ ትምህርት ቤቶች 1ሺህ 835 ብቻ መሆናቸውን የትግራይ ክልል ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ሃላፊ አቶ ረዳይ ገ/ እግዚአብሄር ሰሞኑንን ለመናኸሪያ ሬዲዮ ተናግረዋል።
ይኸ ሰፊ ቁጥር ያለው ጦር በሚታወቁ 552 ትምህርት ቤቶቸ መስፈሩን የገለጹት አቶ ረዳኢ አመልክተዋል። ይህ ቁጭ ብሎ ደሞዝና ቀለብ የሚቀርበለት ኃይል አሁን ላይ ችግር ላይ መውደቁ እንዳሳሰባቸው ገልጸው ለኢትዮሪቬው እንዳሉት፣ ጉዳዩ ቋሚና አስቸኳይ መፍትሄ ካለገኘ በክልሉ ዘረፋና ደረቅ ወንጀል አሁን ካለው በላይ ሊስፋፋ ይችላል።
የፌደራል መንግስት በህገ መንግስቱ መሰረት የክልል ፖሊስና ሚሊሻ ካልሆነ በቀር ለሌሎች ታጣቂ ኃይሎች እውቅና ስለማይሰጥ የበጀት ድጋፍ እንደማያደርግ ያመለከቱት የዜናው ባለቤቶች፣ በፕሪቲቶሪያው ስምምነት መሰረት ትጥቅ በማስፈታትና መቋቋሚያ በመስጠት ወደ መደበና ህይወታቸው እንዲመለሱ ፍላግቱን በተደጋጋሚ እየገለጸ መሆኑ ይታወሳል። ይህንንም ለማድረግ የሃብት ማሰባሰብ ስራ እየተሰራ እንደሆነ በተደጋጋሚ እየተገለጸ ነው።
በትህነግ በኩል ከፊል ኃይሎች ከሃብት ማሰባሰቡ በተጨማሪ በዋናነት የሚነሳው፣ ትግራይ ከጦርነቱ በፊት ወደ ነበራት ቅርጽ ካልተመለሰች ሰራዊቱ አይበተነም፣ ትጥቅ አይፈታም የሚል አቋም ያላቸው አሉ። እነዚህ ወገኖች ሰፊ ቁጥር ያለውን ኃይል ማቆየት ከፈለጉ ደሞዝ፣ ሬሽንና አስፈላጊውን ሁሉ ማሟላት ይተበቅባቸዋል» ግን አልቻሉም።
“ይህ ችግር እያደር ጣጣ ያመጣል” የሚሉ ወገኖች እንደሚሉት ከሆነ ቀለብና ደሞዝ የማይከፍለው የታጠቀ ኃይል ሲብስበት ምን ሊያደርግ እንደሚችል ለመገመት ነብይ መሆን አያስፈልግም።
ተመካክሮ መፍትሄ ለማፈላለግ እንዳይቻል ድርጅቱ አሁን ላይ ለሁለት መከፈሉን ያወሱት የመረጃው ሰዎች፣ ሌላም ስጋት አላቸው። ክፍፍሉ በዚሁ ከቀጠል የአደዋ፣ አክሱምና ሽሬና መቀለና አካባቢዋ፣ እንደርታን ጨምሮ ደቡብ ትግራይ የሚል መለያየት ሊመጣ እንደሚችል ይሰጋሉ። ይህ ስጋት ባለበት ሁኔታ ደሞዝ የሌለውና ቀለብ የማይሟላላት ኃይልን ማን ሊቆታጠረው እንደሚችል ሲያስቡት የትግራይን ችግር ያወሳስብባቸዋል።