“ዓለም ይስማ” አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ፣ ” ዓለም ይስማ ኢትዮጵያ በቀይ ባህር ላይ የማይናወጥ አቋም አላት” ሲሉ ፓርላማው አደነቀ። አስከትለውም ” በዚህ ጉዳይ ላይ የምንደባበቀው ነገር የለም” በማለት የኢትዮጵያን አቋም ይፋ አደረጉ። ይህ ሲሉ በፓርላማው የተገኙ የውጭ አገር ታዛቢዎች አንገታቸውን ያወዛውዙ ነበር።
“በሳንቲም አንሸጥም፣ በሳንቲም ተሽተን የማንንም ዓላማ አናስፈጽምም” ሲሉ ስሜት ቀስቃሽ ንግግር ያሰሙት አብይ አህመድ፣ ኢትዮጵያ ቀይ ባህር ላይ ያላትን አቋም ምክንያታዊና ፍትሃዊ ጥያቄ በመሆኑ በየትኛውም ጊዜ ልጆቻችን እንደሚያሳኩት ገልጸዋል። ህዳሴ ግድብን በምሳሌ አንስተዋል።
የህዳሴው ግድብ እውን የሆነው በገንዘብ መዋጮ ብቻ ሳይሆን ህይወት ተገብሮበት እንደሆነ ሲገልጹ ” ያላሰማሩበን፣ ያላስታጠቁት፣ ያልረጩት ገንዘብ አልነበረም። ግን አልተሳካም። ግድቡ አልቋል” ብለዋል። በተመሳሳይም ኢትዮጵያ ወደ ቀይ ባህር መመለሷን ማንም ሊያስቆመው የሚችል ጉዳይ እንደሆነ ከጥያቄውና ፍላጎቱ ፍትሃዊነት፣ እንዲሁም 120 ሚሊዮን ህዝብ ቆልፎ ማኖር ካለመቻሉ ጋር አስታከው አስረድተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ አንዳን ኢትዮጵያዊ ያልሆኑ ወገኖች 120 ሚሊዮን ሕዝብ ላይ መቆለፍ ነወር መሆኑንን እንደሚናገሩ አስታውቀው፣ በተቃራኒው ኢትዮጵያዊ ሆነው የተሸጡ ለጠላት መረጃ የሚሰጡ፣ ከተላት ጋር የሚሰሩ፣ የኢትዮጵያን ብሄራዊ ጥቅም ለሌሎች አሳልፈው ለመስተት የሚተጉ መኖራቸውን አመልክተዋል። ሁሉም ቢሆን ግን እንደማይሳካ አመልክተዋል።
ኢትዮጵያ ልትወረር እንደምትችል የሚወራ ወሬ ስለምኖሩ አንስተው፣ ዛሬ ላይ ኢትዮጵያን ማንም መውረር እንደማይችል አስረግጠው ተናግረዋል። ቀደም ሲል ኢትዮጵያ ስትገዛቸው የነበሩ መሳሪያዎችን ማምረት መጀመሯን አስታውሰው ” ጦርነት አንፈልግም፣ ነገር ግን ከነኩን ለማንም አንመለስም” ሲሉ ቁርጡን አስታውቀዋል።
“ማንም ኢትዮጵያን እንዲዳፈር አንፈቅድም፣ ማንም ቢመጣ አሳፍረን ከመመለስ ወደሁዋላ አንልም” ያሉት አብይ አህመድ፣ ኢትዮጵያ በባህር በር ጉዳይ ላይ ወደ ኋላ የማይል ይፋዊ አቋም እንዳላት ባማስረገጥ ነው። “ነገር ግን ይህን ለማሳካት ጦርነትም ሆነ የኃይል አማራጭ አንፈልግም፣ ፍላጎታችንን ማሳካት የምንሻው በሰላማዊ አማራጭ ነው” ሲሉ ኢትዮጵያ ለሰላም ተገዢ እንደሆነች ገልጸዋል።
“ጠቅላይ ሚኒስትሩ አክለውም፥ ኢትዮጵያ የትኛውንም ሀገር ላይ ወረራም ሆነ ጥቃት አትፈጽምም” በማለት ተናግረዋል። ከኤርትራ በኩል አንዳንድ ወሬ እንደሚሰማ ጠቅሰው ከዛ ካልመጣ በስተቀር ኤርትራውያን በሰላም እንዲኖሩ ማስተማመኛ ሰጥተዋል። ጅቡቲን እንኳን ለመውረር የሚከአቸው አካል ቢነሳ ኢትዮጵያ ቀደማ ከጎናቸው እንደምትቆም አመልክተዋል። በሺህ የሚቆተር ህይወት የተከፈለላት ሶማሊያ መሪዎቿ አደብ እንዲገዙና ሰክነው እንዲያስቡ ጊዜ መሰጠቱንም አብይ አህመድ አመልክተዋል።
የኢትዮጵያ አቋም ከሁሉም ጋር በትብብርና ሰጥቶ በመቀበል መርህ መኖር ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ጉዳዮችን በሚመለከት ከምክር ቤት አባላት ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል።
በማብራሪያቸውም የኢትዮጵያ አቋም ከሁሉም ጋር በትብብርና ሰጥቶ በመቀበል መርህ መኖር ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ የአፍሪካ የኃይል ማዕከል ናት፤ ከራሷ ባለፈ ለአፍሪካ ልማት ቁርጠኛ ናት ሲሉም አክለዋል፡፡ ከየትኛውም ጎራ ጋር ሳንሰለፍ ከሁሉም ጋር በሰጥቶ መቀበል መርህ ለብሔራዊ ጥቅማችን እንሰራለን ሲሉም ተናግረዋል፡፡
ሁሉም ኢትዮጵያዊ ይህን በመገንዘብ ሀገርን አስቀድሞ መስራት አለበት ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በውስጥ የሚኖረን አንድነትና ሰላም ለዲፕሎማሲያዊ ጥንካሬያችን ከፍተኛ ሚና አለው ሲሉም ተናግረዋል፡፡
በቴሌግራም ይከታተሉን – https://t.me/+f_kxmaPjD-9jYTdk