በኢትዮጵያ ታሪክ የክብር ኒሻን ተሸልመው በሰላም ከስልጠን የወረዱ ኢታማዡር ጀነራል ሳሞራ የኑስ በትግርኛ ባደረጉት ቃለ ምልልስ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይን እንዲያስሩ ከደህንነት ኃላፊው አቶ ጌታቸው አሰፋ ለቀርበላቸው ጥያቄ የሰጡት ምላሽ አነጋጋሪ ሆኗል። ጉዳኡ አነጋጋሪ የሆነው ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ወደ ስልጣን ከመምጣታቸውም ሆነ ጠቅላይ ሚኒስትር ከሆኑ በሁዋላ በዚህ ደረጃ ትህነግ ሊያጠፋቸው የወሰኑበት ምክንያት ነው። በተለይም የቀድሞው የኢንሳ ዳሬክተር ዶ/ር ተክለብርሃን ወልደአረጋይ የጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ ጠላት ስለሆኑ “ልንታገላቸው ይገባል ሲሉ ኮነኑ የቀድሞው የኢንሳ ዳሬክተር “አስወግዱት” ተብለን ነበር ካሉትና ዲጂታል ወያኔ “እረኛውን ምታ መንጎቹ ይበተናል” በሚል ይፋ ያደረገው ዘመቻ ዋና አጀንዳ ሆነዋል።
የቀድሞው የኢንሳ ዳሬክተር የነበሩት ዶ/ር ተክለብርሃን ወልደአረጋይ የጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድን ጠላት ስለሆኑ ልንታገላቸው ይገባል” ሲሉ ወደ ትግራይ ካፈገፈጉ በሁዋላ በይፋ ሲናገሩ እንዳስታወቁት ” ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ አስወግዱት” ብለዋቸው እንደነበር ማስታወቃቸው በወቅቱ ከፈተኛ መነጋገሪያ ጉዳይ እንደነበር የሚታወስ ነው። በውቅቱ ግን አብይን የማስወገዱ ውሳኔ ቸል የተባለው ምንም አያመጣም የሚልና ኦርሞ ይቆጣል ከሚል ፍርሃቻ እንደነበር የቀድሞ የኢንሳ ኃላፊ አመልክተዋ ነበር። በቃለ ምልልሳቸው ከጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ጋር የተነጋገሩት እንደወረደ
- እኔ ግን ” ወደ ኦሮሞዎቹ ሄዶ ወደ ላይኛው እርከን ከወጣ ችግር ይፈጥርብናል።ሳናባረው እዚሁ ከኛ ጋር እንዳይላወስ አድርገን ኩርምት ብሎ እንዲቀመጥ በማድረግ contain እናደርገዋለን ” አልኩት።
- መለስ ዜናዊ ግን ” ኖ ኖ ምክንያት ካገኘህለት ዝም ብለህ ብቻ አስወግደው” አለኝ ።
- እኔም ” ምክንያት እማ ሞልቷል ብዬ 4 እና 5 ምክንያቶችን ጠቅሼ አቢይን አባረርኩት “
-አቢይ በዚህ ተበሳጭቶ አልቃቅሶ ወጣ። ጀነራሉ ይህን አስከትለው ሌለም ሌላም እያሉ ይቀጥላሉ
ለውጡን ተከትሎ “ዲጂታል ወያኔ” በሚል የተቋቋመው ሰራዊት በዋናነት በማህበራዊ ሚዲያ፣ በመገናኛ አውታሮችና በተገኘው አጋጣሚ ሆኑ “እረኛውን ምታ መንጋው ይበተናል” መሪ አጀንዳ ይዘው መነሳታቸው፣ በሚያስገርም ሁኔታ ሰባት ቀን ሃያ አራት ሰዓት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ላይ የተተከለ ዘመቻ ሲያካሂዱ እንደነበር፣ አሁን በሽንፈትና በበጀት ምክንያት ቢፋዘዝም እንዳልቆመ መረጃ ያላቸው በተደጋጋሚ ይፋ ማድረጋቸው እየተነሳ ዛሬ መነጋገሪያ ሆኗል። መነጋገሪያ የሆነውም “ለምን በዚህ ደረጃ ትህነግ አብይን ፈራ ወይም ጠላ ወይም ሊያጠለቸው በጀት በጀተ” የሚለው ነው።
ከዚህ ሁሉ ወጥመድና ዕቅድ ተርፈው ግዙፍ ኃይል የገነቡት፣ ተጽዕኖ ፈጣሪ የሆኑት አብይ አህመድ ” ያደረገልኝን ስለማውቅ እግዚአብሄርን አመስግናለሁ” ያሉበት ምክንያት እያደር ይፋ እየሆነ ነው። አብይ አህመድ ወደ ጠቅላይ ሚኒስትርነት ሲያኮበኩቡ ጀምሮ ሲሽከረከሯቸው የነበሩት አስደንጋጭ መረቦች እንዴት እንደመከኑ በራሱ ትንግርት ነው። ማንንም ለማሰርና ለማስወገድ ፍርሃቻ ያልነበረው ትህነግ እሳቸው ጋር ሲደርስ በዚህ ደረጃ ምን አብረከረከው?
የጄነራል ሳሞራ ዩኑስ ቃለ ምልልስ ይፋ ያደረገውን የእስር ጥያቄ ተከትሎ፣ የተሰማው ትህነግ ጦርነት ከመጀመሩ በፊት ” አብይን ከህዝብ የመነጠሉ ስራ ስኬታማ ነው” በሚል መገምገሙ ነው። ይህ ግምገማ የተደረገው ጦርነቱ ቢጀመር አብይ አሕመድ ደጋፊ ስላጡ በአጭር ቀን ውስጥ ማስወገድ ይቻላል የሚል ድምዳሜ ለመያዝ እንደነበር ግምገማውን የተከታተሉን በመጥቀስ በወቅቱ ዘግበን ነበር።
ከሰኔ 16 የግድያ ሙከራ፣ ወታደሮች በመላክ በቤተመንግስት አብይን ለማፈን ከተደረገው ሙከራና እነ ጃዋር ኦህዴድን በይፋ ማፍረሳቸውን በሚዲያ ለማወጅ ደቂቃዎች ሲቀሩ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ደርሰው እንዳከሸፉ ለተከታተሉ በርካታ ጥያቄ ያጫረውና ያለፈውን ያስታወሰው የጄነራል ሳሞራ ቃለ ምልልስ ነው።
” መዋጋት ርስት አይደለም። ለ42 ዓመታት በውግያ ቆይቻለሁ። እኔ እጣ ፈንታዬ መዋጋት ነው ብዬ አላምን ፤ አቋሜ ውግያ አያስፈልግም ይቁም የሚል ነበር ፤ አሁንም አቋሜ ያው ነው የተለወጠ የለም !! ” ጄነራል ሳሞራ የኑስ
ከሰሞኑን የቀድሞው የኢትዮጵያ ሀገር መከላከያ ሰራዊት ኢታማዦር ሹም ጄነራል ሳሞራ የኑስ አነጋጋሪ ቃለ ምልልስ ሰጥተው ነበር። ከረጅም ጊዜ በኃላ ወደ ሚዲያ ቀርበው ቃላቸውን የሰጡት ብራኸ (ከፍታ) ለተሰኘ በዩትዩብ ላይ ለሚተላለፍ ፕሮግራም ነበር።
በዚሁ ቃለ ምልልስ የቀድሞ የኢፌዴሪ ጠ/ሚ አቶ ኃለማርያም ደሳለኝ በጠ/ሚ ዶ/ር ዐብይ አህመድ ከመተካታቸው በፊት በእሳቸው (ጄነራል ሳሞራ) እና በአገር ድህንነት ሃላፊ በነበሩት አቶ ጌታቸው አሰፋ መካከል አለመጣጣም እንደነበር አስታውቀዋል። በዚህም ጠቅላይ ሚንስተር ዶ/ር ዐብይ አህመድ የኦህዴድ ምክትል ሊቀመንበር እያሉ እንዲያስሯቸው ሲጠይቋቸው በአቶ ጌታቸው አሰፋ ሲጠየቁ ” አላስርም ! ” ማለታቸውን አንሰተዋል።
” ያኔ ዐብይን እሰረው ተብዬ አይሆንም ካልኩኝ ዛሬም ልክ ነኝ። ምክንያቱ እኔ የሰራዊት መሪ እንጂ የሲቪል ፓለቲከኛ አሳሪና መሃሪ አይደለሁም። መከላከያ ሲቪል ፓለቲከኛ የማሰር ስልጣንና መብት የለውም” ሲሉ ይፋ እንዳደረጉት የአቶ ዴታቸው አሰፋን ጥያቄ ውድቅ ማድረጋቸውን በዝርዝር አስረድተዋል።
“በውቀቱ አብይ የአንድ ታላቅ ክልልና ህዝብ አመራር ነበር። ታላቁ ህዝብ ማለት ኦሮሞ ነው። ያኔ የኦሮሞ ህዝብ መሪ የፓለቲካ ድርጅት የነበረው ኦህዴድ ነው። የድርጅቱ ምክትል ሊቀመንበር አብይ ነበር። በተጨማሪም የፓርላማ የህዝብ ተመራጭ አባል ነበር” ሲሉ ማሰር ያልቻሉበትን ፖለቲካዊና ስነልቦናዊ ምክንያታቸውን ይፋ አድርገዋል። “አብይ ያኔ መታሰር ከነበረበት ጥንካሬና ድክመቱ ወደ ሳራሞራ ሳይሆን ወደ ፓርለማ ነው የሚወሰደው። ከፓርላማ ካለፈ ወደ ያኔው የኢህአዴግ ሊቀመንበርና ጠቅላይ ሚንስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ ይቀርባል” በማለትም ሂደቱ እንዴት ሊስተናገድ እንደሚገባ አስረድተዋል።
የኢህአዴግ ሊቀመንበሩና ጠ/ ሚንስትሩ የዐብይ ድክመት ልክ ነው ብሎ ካመነበት ከፓርላማ ሃላፊነቱ ማንሳት እንደሚኖርበት ሳሞራ አመልክተዋል። ካልሆነም ሃይለማርያም ደሳለኝ ራሳቸው ጠቅላይ ሚኒስትር አብይን የማሰር ስልጣን ስለሌላቸው ጉዳዩን ወደ ኦህዴድ ሊመሩት እንደሚገባም ሳሞራ ዩኑስ መናገራቸውን ቲክቫህ ወደ አማርኛ መርልሶ ካቀረበርው ሪፖርት ለመረዳት ተችሏል።
“ኦህዴድ ካመነበት ደግሞ ይታሰር ብሎ ከወሰነ የሚመለከተው የህግ አካል እንጂ ሳሞራ ዐብይን የማሰር ስልጣን የለውም ” ሲሉ አቋማቸውን ይፋ ያደረጉት ሳሞራ ዩኑስ ጦርነትን አጥብቀው እንደሚቃወሙ፣ አስቀድመውም ጦርነት እንዳይካሄድ ምክር ሲሰጡ እንደነበር ተናግረዋል።
ጀነራሉ በዚሁ ጦርነትን በሚቃወመው አቋማቸው ሳቢያ በርካታ ሃሜቶችና ትችቶች ሲሰነዘርባቸው እንደነበር ይታወሳል። ለዚሁ ያለፈ ትችት መልስ ይሆን ዘነድ በሰጡት ቃለ ምልልስ ላይ በርካታ ጉዳዮች አንስተዋል። በተለይም ” ጄነራል ሳሞራ ከፌዴራል መንግሥት ጋር ወግነው በድብቅ ጦርነት መርተዋል ተሳትፈዋል ” ለሚለው ወሬ “ጦርነቱ የከበዳቸው የትግራይ ፓለቲከኞች ለድክመታቸው መሸፈኛ የፈጠሩት ምክንያት ነው ፤ ጦርነቱ ሲጀመርም ሆነ ሲፋፋም ከቤተሰቦቼ ጋር አዲስ አበባ ነበርኩ” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።
መዋጋት ርስት እንዳልሆነ ፤ ለ42 ዓመታት በውግያ እንደቆዩ፣ እጣ ፈንታቸው ውግያ ነው ብለው እንደማያምኑ፤ አቋማቸው ውግያ አያስፈልግም የሚል እንደሆነ ፤ ይህ አቋማቸው አሁን ድረስ የጸና እንደሆነ ተናግረዋል።
ጦርነቱ በተጀመረ ማግስት መንግስትንና ጀነራሎቹን ጦርነቱ እንዲቆም እንደጠየቁ፣ እስከ መጨረሻ ድረስም ግጭቱ በሰላም እንዲፈታ ጥረት እንዳደረጉ ያወሱት ጀነራል ሳሞራ፣ “የትግራይ ህዝብ ሃያ ዓመት እየቆጠረ መዋጋትየለበትም” ብለዋል። የትግራይ ህዝብ ጦርነት እንደሰለቸው፣ የሰላም አርአያ መሆን እንደሚፈልግ፣ ፓለቲከኞችም የህዝበ ሰላም መጠበቅ እንዳለባቸው በቃለ ምልልሳቸው አመልክተዋል።
“እምነታቸው የትግራይ ህዝብ መዋጋት የለበትም” የሚል እንደሆነ ያመለከቱት ጀነራሉ፣ እንደ አመራር ህዝቡ ወደ ውግያ መግፋት አግባብ እንዳልሆነ አውግዘው ተናግረዋል። ውግያ ሲጀመር አከባቢ ጠ/ሚ አብይን እና አቶ ግርማ ብሩን አግኝተው ውግያ እንዳይጀመር እንደጠየቁ ፤ እነሱም እንደ አመራር የሰጧቸው መልስ እንዳለ አምልክተዋል። መልሳቸውን በትርጉሙ መረጃ ውስጥ ምን እንደነበር ግን አልተብራራም።
በትግራዩ ጦርነት በትግራይ ህዝብ ላይ እልቂት መፈጸሙን እንደሚያምኑ፤ የትግራዩ ጦርነት መንስኤ የፓለቲካ ብልሽት ፤ የአመራሮች መበስበስና ከህዝብ አገልጋላይነት መውጣት ውጤት እነደሆነ፤ የአማራ ኤሊቶች የትግራዩ ጦርነት አንዲጋጋል ከፍተኛ ሚና እንደተጫወቱ በርካታ እላፊ ነገሮች እንደተናገሩ፤ የትግራዩ ጦርነት ከሁሉም የኢትዮጵያ ክልሎች የተወጣጡ ወታደሮች የተሳተፉበት ቢሆንም የሁሉም ክልሎች ህዝብ ደግፎታል ተሳትፎበታል ማለት እንዳልሆነ አመልክተዋል።
በትግራይ ጦርነት የሻዕብያ ሃይል አጋጣሚው በመጠቀም የትግራይን ህዝብ ያለ ስሙ ስም በመስጠት አንገቱ ለማስደፋትና ለማጥፋት እንደዘመተ ሳሞራ በቁጭት ስሜት ተናግረዋል።
ከጦርነቱ በፊት ከምርጫው ጋር ተያይዞ የነበሩት የእልህ አገላለጾችና አካሄድ እንዲቆሙ በሁለቱም በኩል ሲገስጹ እንደነበር፤ ጦርነቱ እንዳይነሳ ፤ ከዛም እንዲቆም ብዙ ጥረት እንዳደረጉ፤ ያልተዘጋጁበትን፣ ያላመኑበትን ወግያ እንደማይሳተፉ፣ እንደማይዋጉ በይፋ አቋም መያዝቸውን አስታውቀዋል።
የጄነራሉ አቋም ዛሬ በሰጡት ቃለ ምልልስ የተሰማ ወይስ ቀደም ሲል የነበረ? ለሚለው ቲክቫኽ ከ5 ዓመታት በፊት በ2012 ዓ.ም ህዳርና ታህሳስ ወር ላይ እንዲሁም ጦርነቱ ተጀምሮ የፌደራል መንግስት መቐለ በተቆጣጠረበት ወቅት የካቲት 2013 ዓ.ም በአካልና በስልክ ባደረገው ግንኙነት የሰጡትን ምላሽ አስታውሷል።
ጀነራል ሳሞራ ሀገራዊ ኒሻን ተሸልመው በጡረታ ከተሰናበቱ በኋላ በመቐለ ከተማ ፕላኔት ሆቴል አግኝቶ ቲክቫኽ ሲያናግራቸው በዚህም በዚያም በወጣቶች የሚታይ የነበረው የጦረኝነት ስሜት ፓለቲከኞቹ በማርገብ ሃላፊነታቸው እንዲወጡ ወታደራዊ ምክር ሰጥተው እንደነበር በማስታወስ አቋማቸው አውዳሚው ጦርነት ከመቀስቀሱ በፊት የተያዘ መሆኑን ማረጋገጥ ተችሏል።
ጥር 2012 ዓ/ም ደጀና ላይ 45ኛው የህወሓት የምስረታ በዓል ለማክበር ለተሰባሰቡት ወጣቶች ባሰሙት ንግግር፣ ወጣቶች ከዚህም ከዚያም ያሉ ፓለቲከኞች በሚለኩሱት ጦርነት ገብተው እንዳይቃጠሉ የሚያስገነዝብ አባታዊና ወታደራዊ ምክር አስተላልፈው ነበር። ጦርነቱ ከተጀመረ እና ከተባባሰ በኃላ በሰጡትም አስተያየት ጦርነትን ከበፊቱ የባሰ እንደተጠየፉት ገልፀውለት ነበር።