በተለያዩ ጊዜያት አሽከርካሪዎችን ራቅ ወዳለ ስፍራ እየወሰዱ በመግደል ተሽከርካሪዎችን ሲሰርቁ የነበሩ አራት ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለው በሞት እንዲቀጡ ውሳኔ ተላልፎባቸዋል።
በአዲስ አበባ ገላን ክፍለ ከተማ፣ በሳሪስ እንዲሁም በቢሾፍቱ መኖሪያቸውን ያደረጉት ቴዎድሮስ ብርሃኔ እና እዩኤል ቴዎድሮስ እንዲሁም በሌላ በኩል ተፈሪ ተስፋዬ እና ዩሃንስ አረፋ የተባሉት ግለሰቦች ከአዲስ አበባ ቢሾፍቱ በመመላለስ ድርጊቱን ሲፈጽሙ እንደነበር ነው የተገለጸው።
የሸገር ከተማ አስተዳደር ዓቃቢ ህግ ጽ/ቤት የተለያዩ ወንጀሎች ምርመራ ዓቃቢ ህግ አቶ ሚዴቅሳ አጋሩ ስለወንጀሎቹ ተከታዩን ለብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ተናግረዋል።
#ወንጀል_1
ቴዎድሮስ እና እዮኤል የተባሉት ተከሳሾች ሰለሞን አሊ የተባለ የጭነት ተሽከርካሪ አይሱዚ አሽከርካሪን ከዱከም ከተማ እንጨት ትጭንልናለህ በማለት በኮንትራት ዋጋ ተስማምተው ወደ ቢሾፍቱ ከተማ ያቀናሉ።
በመቀጠል ወደ ሰንዳፋ መስመር እንዲሄድ በጦር መሳሪያ በማስገደድ ጨፌዶሳ የተባለ ቦታ ሲደርስ በሽጉጥ በመምታት ጥለውት ተሽከርካሪውን ይዘው ተሰውረው ቆይተው እንደሸጡት ተገልጿል።
#ወንጀል_2
ተፈሪ ተስፋዬ እና ዩሃንስ አረፋ የተባሉት የወንጀል ቡድን አባላት ደግሞ አቶ ከበደ በለው የተባሉ ነዋሪነታቸው አዲስ አበባ አቃቂ አካባቢ የሆኑ እና ሃይሩፍ የህዝብ ማመላለሻ ሚኒባስ ከአዲስ አበባ አሰላ በማሽከርከር የሚተዳደሩ ግለሰብ ላይ ግድያ ፈጽመዋል።
ይህም ሞችን ከቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ሰው እናመጣለን በማለት ከወሰዷቸው በኋላ በመሳሪያ በማስገደድ ወደ ገላን ከተማ በመውሰድ በገመድ አንቀው መግደላቸውንና ከዚያም ተሽከርካሪውን በጎሮ በኩል ገላን ከተማ በመውሰድ አንዶዴ የተባለው ቦታ አስከሬኑን ጥለው መሰወራቸውን ነው የገለጹት።
#ወንጀል_3
የሜትር ታክሲ አሽከርካሪው ሚኪያስ ተስፋዬ የተባለ የ28 ዓመት ወጣት እዩኤል ቴዎድሮስ የተባለው ማታ ላይ ደውሎለት ከቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ የምንቀበለው እንግዳ አለ በማለት ምሽት ላይ ቢሾፍቱ ከተማ በተከራዩበት ቤት በመውሰድ በሽጉጥ ገድለውታል።
የፖሊስ ክትትል . . .
ፖሊስ ባደረገው ክትትል ቴዎድሮስ ብርሃኔ እና እዮኤል ቴዎድሮስ በቁጥጥር ስር በማዋል የምርመራ ሂደቱ ሲያጣራ ቆይቷል።
በዚህም ሰለሞን የተባለው አሽከርሪውን ገለው ጫካ ውስጥ መጣላቸውን የጭነት ተሽከርካሪውን በ700ሺህ ብር መሸጣቸውን ለፖሊስ መርተው አሳይተዋል።
በመቀጠል ሚኪያስ ተስፋየ የተባለውን አሽከርካሪ ገድለው እንደጣሉት እና ኮሮላ ተሽከርካሪውን የደበቁበትን ቦታ ለፖሊስ ይጠቁማሉ።
ፖሊስ ምርመራውን በመቀጠል የአቶ ከበደ ገዳዮችን ለመያዝ ባደረገው ክትትል አዲስ አበባ ሳሪስ ዶሮ ተራ ከሚባል ስፍራ በመያዝ በሁለቱም ግለሰቦች ላይ ጥልቅ ምርመራ በማድረግ ሃይሩፍ ተሽከርካሪውን እንዲፈታታ በማድረግ ለመሸጥ ሲሞክሩ በቁጥጥር ስር ለማዋል ተችሏል።
ፖሊስ የምርመራ መዝገቡን በማጠናቀቅ ለዓቃቢ ህግ ይልካል። ዓቃቢ ህግ ከፖሊስ የደረሰውን የምርመራ መዝገብ በመመልከት ተከሳሾች በመደራጀት የጦር መሳሪያ በመታጠቅ በአሰቃቂ ሁኔታ የሰው መግደል ወንጀል መፈጸማቸውን በመጥቀስ በወንጀል ህግ 530 መሰረት ክስ መስርቷል።
የፍርድ ቤት ውሳኔ . . .
በዓቃቢ ህግ የተመሰረተውን ክስ የተመለከተው የሸገር ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ ፍርድ ቤት አራቱም ተከሳሾች የፈጸሙት የወንጀል ድርጊት በመመልከት ከባድ እና አደገኛ በመሆኑ የቅጣት ማክበጃ በመጥቀስ በአራቱም ተከሳሾች ላይ በሞት እንዲቀጡ ውሳኔ አስተላልፏል።
በተጨማሪም ተሽከርካሪዎች የደበቁ አራት ግለሰቦች በእስራት እና በገንዘብ እንዲቀጡ ፍርድ ቤቱ ውሳኔ ማስተላለፉ ተገልጿል።
TIPS
The Wars We Still Can Stop
Ethiopia: Israel Foreign Minister Says His Country Wants to Be Part of Ethiopia’s Success
A Nation Silenced: How the 1993 Referendum Stripped All Ethiopians of Their Sea
The 1976 TPLF Manifesto: TPLF’s “Republic of Greater Tigray”
Away from the global spotlight, Eritreans are trapped in a garrison state
Testimonials of a Sudanese Intelligence Officer on the Proxy war between Sudan and Ethiopia from 1970s to early 1990s
Ethiopia-Eritrea Tension: A Volatile History that Never Truly Ended – Could Assab Become Africa’s Crimea?
“As an outlier among the five tplf leaders, I wasn’t part of the armed struggle tradition”
Former Tigray fighters say no to war
Don’t Risk Your Future: The United States Cracks Down on Illegal Immigration
Counter-Video by EBC Challenges EBS Broadcast, Sparks Public Outcry Over Alleged Misinformation
Ethiopia and Eritrea Slide Closer to War amid Tigray Upheaval
Sea Outlet Serious and Unabated Agenda for Ethiopia: Retired Lieutenant General Yohannes
Israel’s Peace With Egypt Is Starting to Crack
Egyptian, Eritrean FMs reject involvement of non-bordering countries[Ethiopia] in Red Sea security
Ethiopia, Creditors Agree on $8.4 Billion Debt Restructuring