መግቢያ
ሰዎች ባላቸው የእለት ተእለት መስተጋብር የሚገጥማቸውን አለመግባባት ከሚፈቱበት መንገድ አንዱ ጉዳያቸውን ለፍርድ ቤት አቅርበው ዳኝነት መጠየቅ ነው፡፡ ፍርድ ቤት ከሄዱም በኋላ በሚሰጠው ውሳኔ ቅሬታ ሲኖራቸው አቤት የሚሉበት የተዋረድ የይግባኝ ሥርአት መዘርጋቱ እጅግ አስፈላጊ በመሆኑ የይግባኝ ሥርአት ተበጅቷል፡፡ ይግባኝ ወንጀልም ሆነ በፍትሐብሔር ሥነ ሥርአት ህግጋት የተዘረጋ መብት ሲሆን በዚህ አጭር ፅሁፍ ትኩረታችንን በፍትሐብሔር የይግባኝ አቀራረብ ላይ የምናደርግ ይሆናል፡፡
የይግባኝ ምንነት
ይግባኝ ማለት በመጀመሪያ ደረጃ ስልጣን ጉዳዩን ባየው ፍርድ ቤት በተሰጠ ፍርድ/ውሳኔ/ ትዕዛዝ ቅር የተሰኘው ወገን ቅሬታውን ይግባኝ እንዲቀበል በህግ ለከተመከተው ከፍ ላለው ፍርድ ቤት በማቅረብ የተሰጠውን ፍርድ፣ ውሳኔ ወይም ትዕዛዝ እንዲሰረዝ፣ እንዲሻሻል፣ እንዲሻር የሚጠየቅበት ሥርዓት ነው። ይህም በፍትሐብሔር ሥነ ሥርአት ህግ ቁጥር 320(1) ተመልክቷል፡፡
ይግባኝ የሚባለው የመጨረሻ ፍርድ ላይ ስለመሆኑ
ይግባኝ የሚቀርበው የሥር ፍርድ ቤት የቀረበለትን ጉዳይ መርምሮ በሚሰጠው የመጨረሻ ፍርድ ላይ እንደሆነ በፍትሐብሔር ሥነ ሥርአት ህግ ቁጥር 320(1) ደንግጓል፡፡ የፍትሐብሔር ሥነ-ሥርአት ህግ ቁጥር 320(2) እና (3) መሰረት ጊዚያዊነት ባላቸው ትዕዞዞች ላይ ማለትም ቀጠሮ ሲወስን ወይም በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ላይ ውሳኔ ሲሰጥ ወይም የጠበቃን እርዳታ ስለማግኘት ወይም ከጠበቃ ጋር ስለመቅረብ ወይም ዳኝነት ሳይከፈል በነፃ ለመክሰስ በሚቀርብ ጥያቄ ላይ በሚሰጠው ትዕዛዝ ይግባኝ መቅረብ የሚችለው በጉዳዩ ላይ የመጨረሻ የፍርድ ውሳኔ ከተሰጠ በኋላ በአንድ ላይ እንጂ ነጥሎ ይግባኝ ማቅረብ አይፈቀድም፡፡ ሆኖም በልዩ ሁኔታ ማለትም ማንም ሰው እንዲታሰር ወይም በማረፊያ ቤት እንዲቆይ ወይም በእጅ ያለን ንብረት ለሌላ ወገን እንዲተላለፍ በተሰጠ ትዕዛዝ እንዲሁም ያላግባብ ታስሪያለው ይግባኝ ይታይልኝ ሲል በሚቀርብ አቤቶታ ተቀባይነትን ሲያጣ ይግባኝ ሊቀርብ ይችላል።
የፍትሐብሔር ይግባኝ ማልከቻ ይዘትና የሚቀርብበት ጊዜ
የፍትሐብሔር ሥነ ሥርአት ህግ ቁጥር 327 የይግባኝ ማመልከቻ ይዘት ምን መምሰል እንዳለበት ደንግጓል፡፡ በዚህም መሰረት የይግባኝ ማመልከቻ
ይግባኝ የቀረበበትን ፍርድ ቤት ስምና የሚያስችልበትን ቦታ
የይግባኝ ባዩና የመልስ ሰጭው ስምና አድራሻ
ይግባኝ የተባለበትን ፍርድ የሰጠው ፍርድ ቤት ስም፣ ፍርዱ የተወሰነበትን ቀንና የመዝገብ ቁጥር
መጥሪያ ለመስጠት እንዲቻል የመልስ ሰጭውን አድራሻ
ለይግባኙ ምክንያት የሆኑ ነገሮች፣ በይግባኙ እንዲታረም የሚፈለገውን የነገር ዝርዝርና የሚጠይቀውን ዳኝነት ዓይነት ማካተት አለበት፡፡
በፍትሐብሔር ሥነ ሥርአት ህግ አንቀጽ 323(2) መሠረት ይግባኝ የሚቀርበው ይግባኝ የሚባልበት ጉዳይ ላይ ውሳኔ በተሰጠ በ60 (ስልሳ) ቀናት ውስጥ ነው፡፡ ይግባኝ በ60 ቀን ውስጥ ያልቀረበ ከሆነ ይግባኝ ባይ ይግባኝ የማቅረብ መብቱን ያጣል፡፡ በአንፃሩ የይግባኝ ማቅረቢያ ጊዜው ያፈለበት አሳማኝ ምክንያት ያለው ሰው ይግባኙን በጊዜው ለማቅረብ ያልቻለበትን በቂ ምክንያት ከማስረጃዎች ጋር አያይዞ የፈቃድ ጥያቄ ማመልከቻ ማቅረብ እንደሚችል በሥነ ሥርአት ህጉ ቁጥር 325 ተደንግጓል። ይህ የፈቃድ ጥያቄ ማመልከቻ የይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት መዝገብ ቤት ሹም ይግባኙን በመለሰው በ10 ቀናት ውስጥ መቅረብ አለበት፡፡ በቂ ምክንያት ለሚለው በህጉ የተሰጠ ዝርዝር ነገር የሌለ በመሆኑ የምክንያቱ በቂነት እንደየሁኔታው በፍርድ ቤቱ የሚመዘን ይሆናል፡፡ ሆኖም አመልካቹ ይግባኙን በጊዜ ያላቀረበው በአመልካቹ ጠበቃ ወይም ነገረ ፈጅ ወይም ወኪሉ አለመቅረብ ምክንያት የሆነ እንደሆነ ይህ በቂ ምክንያት ተብሎ እንደማይወሰድና የይግባኝ መዝገብ እንዲከፈት የማይፈቀድ መሆኑን የፍትሐብሔር ሥነ ሥርአት ህግ ቁጥር 326(2) ደንግጓል፡፡
የይግባኝ አቤቱታ ተቀባይነት የሚያገኝበት ወይም የማያገኝበት ሁኔታ
ይግባኝ ከቀረበ በኋላ ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ነገሩ የሚሰማበትን ቀነ ቀጠሮ ወስኖ ይግባኝ ባዩ ወይም ጠበቃው የሚያቀርቡትን ክርክር ከሰማ በኋላ የመጀመሪያው ደረጃ ፍርድ ቤት ፍርድ የሰጠበትን የመዝገብ ግልባጭ መርምሮ ፍርዱ ጉድለት የሌለበት መሆኑን ከተረዳ መልስ ሰጭውን ሳይጠራ ይግባኙን ዘግቶ አቤት ባዩን ሊያሰናብት ይችላል፡፡
በአንፃሩ ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ይግባኙን የተቀበለ እንደሆነ ይግባኙ የሚሰማበትን ቀነ ቀጠሮ ወስኖ መልስ ሰጭው እንዲቀርብ መጥሪያውንና የይግባኝ ማመልከቻውን ግልባጭ ይልክለታል፡፡ በቀነ ቀጠሮው ሳይቀርብ ቢቀር ይግባኙ በሌለበት የሚሰማ መሆኑን በመጥሪያው ላይ ያስታውቀዋል፡፡
በተጨማሪም ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ለጉዳዩ እልባት እስከሚሰጥ ድረስ የሥር ፍርድ ቤት ፍርድ አፈፃፀም ታግዶ እንዲቆይ ሊያዝ እንደሚችል ከሥነ ሥርአት ህጉ ቁጥር 332 መረዳት ይቻላል፡፡ ይህ የሚሆነውም
ይግባኝ ከመታየቱ በፊት ፍርድ ቢፈፀም ከፍ ያለ ጉዳት የሚደርስ መሆኑ ሲታመን
ፍርድ እንዲታገድ የቀረበው ማመልከቻ ሳይዘገይ የቀረበ ሲሆን እና
አልመካቹ ስለ ፍርድ አፈፃፀም በቂ ገንዘብ ወይም በቂ መያዣ ያስቀመጠ መሆኑን ሲረጋገጥ እንደሆነ በሥነ ሥርአት ህጉ ቁጥር 335 ተደንግጓል፡፡
የይግባኝ ክርክር ሂደት
በመጀመሪያ ደረጃ ጉዳዩን ባየው ፍርድ ቤት ያልተነሳ አዲስ ክርክር በይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት አንስቶ ለመከራከር እንደማይቻልም በፍትሐብሔር ሥነ ሥርአት ህግ ቁጥር 329(1) ስር ተደንግጓል፡፡ እንዲሁም ተጨማሪ ማስረጃ በሚመለከት ለይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት አዲስ ማስረጃ ማቅረብ አይፈቀድም፡፡ በልዩ ሁኔታ በፍትሐብሔር ሥነ ሥርአት ህግ ቁጥር 345 መሰረት ይግባኝ የቀረበበትን ክርክር የፈረደው ፍርድ ቤት መቀበል የነበረበት ማስረጃ ያለበቂ ምክንያት ሳይቀበል ከቀረ ወይም ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ትክክለኛ ፍርድ ለመስጠት ወይም ተገቢ መስሎ በታየው በማናቸዉም ምክንያት ተጨማሪ ማስረጃ እንዲቀርብና እንዲሰማ መፍቀድ ይችላል። ፍርድ ቤቱ መሰል ትዕዛዝ በሚሰጥበት ጊዜ ማስረጃው እንዲቀርብ የተደረገበትን ምክንያት በመዝገቡ ላይ ማስፈር ጠበቅበታል፡፡
ይግባኙን ለመስማት በተወሰነው ቀነ ቀጠሮ ክርክሩ በሚሰማበት ጊዜ ይግባኝ ባዩ ያቀረበውን ይግባኝ የሚደገፍበትን ነገር ለማስረዳት አስቀድሞ ክርክሩን ይጀምራል፡፡ ይግባኝ ባዩ ላሰማው ክርክር መልስ ሰጭው የመከላከያ መልሱን ይሰጣል፡፡ ቀጥሎም መልስ ሰጭው ላቀረበው መከላከያ ይግባኝ ባዩ መልስ ለመስጠት ይችላል፡፡ ከዚህ በላይ ባለው ንዑስ ቁጥር የተነገረው ድንጋጌ ይግባኝ ባዩ በጽሑፍ ላቀረበው የይግባኝ ማመልከቻ መልስ ሰጭው የመከላከያ መልሱን በጽሑፍ እንዲያቀርብ ከማዘዝ ፍርድ ቤቱን አያግደውም፡፡ በስተመጨረሻም ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን ክርክርና እንደአስፈላጊነቱም ይግባኝ የተባለበትን ፍርድ የወሰነውን ፍርድ ቤት መዝገብ ከመረመረ በኋላ ውሳኔ ይሰጣል፡፡ በውሳኔውም የሥር ፍርድ ቤት ውሳኔን ሊያፀና፣ ሊያሻስል፣ ሊሽር ወይም የበታች ፍርድ ቤት መያዝ ያለበት ጭብጥ ሳይዝ ወይም ፍሬ ነገሩን ሳይመረምር ቀርቶ ከሆነ የይግባኝ ሰሚው ፍርድ ጭብጥ ይዞ ወይም መመርመር ያለበት ፍሬ ነገር ለይቶ እንዲመረምር በፍትሐብሔር ሥነ ሥርአት ህግ አንቀጽ 343 መሰረት ጉዳዩን ላየው ፍርድ ቤት መልሶ ሊልክ ይችላል፡፡
ማጠቃለያ
በአጠቃላይ በታችኛው ፍርድ ቤት ውሳኔ ቅር የተሰኘ ተከራካሪ ወገን ይግባኝ የማለት መብቱ የተከበረ ሲሆን ይግባኙን የፍትሐብሔር ሥነ ሥርአት ህጉ ባስቀመጠው ግዜ እና ሥነ ሥርአት ማቅረብ ይጠበቅበታል፡፡
በንቃተ ህግ ትምህርትና ስልጠና ዳይሬክቶሬት የተዘጋጀ
TIPS
The Wars We Still Can Stop
Ethiopia: Israel Foreign Minister Says His Country Wants to Be Part of Ethiopia’s Success
A Nation Silenced: How the 1993 Referendum Stripped All Ethiopians of Their Sea
The 1976 TPLF Manifesto: TPLF’s “Republic of Greater Tigray”
Away from the global spotlight, Eritreans are trapped in a garrison state
Testimonials of a Sudanese Intelligence Officer on the Proxy war between Sudan and Ethiopia from 1970s to early 1990s
Ethiopia-Eritrea Tension: A Volatile History that Never Truly Ended – Could Assab Become Africa’s Crimea?
“As an outlier among the five tplf leaders, I wasn’t part of the armed struggle tradition”
Former Tigray fighters say no to war
Don’t Risk Your Future: The United States Cracks Down on Illegal Immigration
Counter-Video by EBC Challenges EBS Broadcast, Sparks Public Outcry Over Alleged Misinformation
Ethiopia and Eritrea Slide Closer to War amid Tigray Upheaval
Sea Outlet Serious and Unabated Agenda for Ethiopia: Retired Lieutenant General Yohannes
Israel’s Peace With Egypt Is Starting to Crack
Egyptian, Eritrean FMs reject involvement of non-bordering countries[Ethiopia] in Red Sea security
Ethiopia, Creditors Agree on $8.4 Billion Debt Restructuring