“ለውጥ የሚመጣው በአንድነት እና በኅብረት በመሥራት ነው ” አባተ ጌታሁን (ዶ.ር)
በአማራ ክልል በተከሰተው ተደጋጋሚ ጦርነት ከፍተኛ የኾነ ሰብዓዊ፣ ቁሳዊ እና ሥነ ልቦናዊ ጉዳት ደርሷል፡፡
የደረሰውን ጉዳት ለይቶ ወደ መልሶ ማቋቋም እና ግንባታ መግባት ሲጀመር ሌላ ችግር በክልሉ ተፈጥሯል፡፡
በክልሉ የተፈጠረው የጸጥታ ችግርም እስካሁን ድረስ መቋጫ ሳይበጅለት ቀጥሏል፡፡ በክልሉ የተፈጠረው ግጭትም ክልሉን በጉዳት ላይ ጉዳት ደራርቦበታል፡፡
የአማራ ክልል በጦርነት የተጎዱ አካባቢዎች መልሶ ማቋቋም እና መልሶ ግንባታ ፈንድ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ አባተ ጌታሁን (ዶ.ር) ከጥቅምት 2013 ዓ.ም ጀምሮ በአማራ ክልል የተለያዩ ችግሮች መኖራቸውን ገልጸዋል፡፡
እስካሁን ድረስ ችግሮቹ መቀጠላቸውንም አንስተዋል፤ በጦርነት ምክንያት በአማራ ክልል ሰፊ ሰብዓዊ፣ ቁሳዊ እና ሥነ ልቦናዊ ጉዳት መድረሱን ነው የተናሩት፡፡
በጦርነቱ የደረሰውን ጉዳት በማዕከል ለመፍታት ተቋም መቋቋሙንም ገልጸዋል፡፡ ከዩኒቨርሲቲዎች ጋር በመኾን ውድመቱ እና ጉዳቱ ምን ያክል እንደኾነ መጠናቱንም አመላክተዋል፡፡ የደረሰውን ጉዳት በመጽሐፍ ታትሞ እንዲወጣ መደረጉንም አስታውሰዋል፡፡
ጥናቱ ጉዳቱን በዝርዝር የሚያሳይ እና በሚገባ የለየ መኾኑንም ተናግረዋል፡፡ አሁን በክልሉ ያለው ግጭት ያደረሰውን ጉዳት ለማጥናት በሂደት ላይ መኾናቸውንም ገልጸዋል፡፡
ጥናቱን መሠረት በማድረግ የአምስት ዓመት ስትራቴጂክ እቅድ መዘጋጀቱንም አስታውቀዋል፡፡ በዕቅዳቸው መሠረት የዓለም ባንክ ሰፊ ድጋፍ እንዳደረገላቸው ነው የተናገሩት፡፡ 7 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር የሚኾን ድጋፍ እንደሰጣቸውም አስታውቀዋል፡፡
የክልሉ መንግሥት፣ ግለሰቦች እና ተቋማት እያገዟቸው መኾናቸውንም ገልጸዋል፡፡ የደረሰው ጉዳትም ከፍተኛ በመኾኑ ተጨማሪ ድጋፎች እና ርብርቦች ይጠይቃሉ ነው ያሉት፡፡
የሰብዓዊ ድጋፍ፣ ልማት እና ሰላም ላይ መሥራት እንደሚያስፈልግም ገልጸዋል፡፡ ችግሮችን ወደ ጸጋ መለወጥ አለብን ያሉት ኀላፊው ሁለተኛው የዓለም ጦርነት ላይ የወደሙ አንዳንድ ሀገራት በአጭር ጊዜ እንደተመለሱት ሁሉ እኛም ለመመለስ መሥራት ያስፈልገናል ነው ያሉት፡፡
መልሶ ማቋቋም እና ግንባታ ለአንድ ወገን ብቻ ተለይቶ የማይሰጥ እና የሁሉንም ድጋፍ እና ርብርብ የሚጠይቅ መኾኑንም አንስተዋል፡፡ ችግሩን መፍታት የግድ ይላል ያሉት ኀላፊው ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችሉ የተለያዩ ሥራዎች እየተሠሩ መኾናቸውን ነው ያስታወቁት፡፡
እየተወያዩ ሰላምን ማምጣት፣ ለችግሮች በውይይት ሰላምን መፈለግ እንደሚጠበቅም አመላክተዋል፡፡ ገንዘብ ያለው በገንዘቡ፣ እውቀት ያለው በእውቀቱ በመደጋገፍ መፍትሔ ማበጀት እንደሚገባም ተናግረዋል፡፡ አሁን ላይ በአማራ ክልል በቀጥታም ኾነ በተዘዋወሪ ችግር የሌለበት አካባቢ እንደሌለም ገልጸዋል፡፡
ለመልሶ ማቋቋም እና ግንባታ ምሁራን፣ ባለሃብቶች እና መሪዎች በአንድነት መሥራት እንደሚጠበቅባቸውም ተናግረዋል፡፡ ለውጥ የሚመጣው በአንድነት እና በኅብረት በመሥራት ነው ብለዋል፡፡
ክልሉን መልሶ ለማቋቋም እና መልሶ ለመገንባት የሚያስችል ስትራቴጂክ ሰነድ መኖሩንም ተናግረዋል፡፡ 105 የሚኾኑ ፕሮጀክቶችን ማጠናቃቃቸውንም ገልጸዋል፡፡
በጤና፣ በትምህርት፣ በሥራ ዕድል መፍጠሪያ ተቋማት እና ሌሎችን መሥራታቸውን ነው የተናገሩት፡፡ በ2017 በርካታ ፕሮጀክቶችን ለመሥራት ማቀዳቸውን የተናገሩት ኀላፊው ሥራዎችን ውጤታማ ለማድረግ ድጋፍ እንደሚፈልጉም ገልጸዋል፡፡
የአማራ ክልል በግጭት እንዲቆይ ያደረጉ ምክንያቶችን ማጥናታቸውን እና በቀጣይ ወደ ሰላም ለመመለስ የሚያስችሉ የስትራቴጂክ ዕቅድ ማዘጋጃታቸውንም ተናግረዋል፡፡ ችግሮችን ተባብረን መፍታት እና ለውጥ ማምጣት እንችላለን ብለዋል፡፡
መፈናቀል በአማራ ክልል ከፍተኛ ቁጥር መኾኑን የተናገሩት ኀላፊው ተፈናቃዮችን ማቋቋም የሚያስችል ስትራቴጂ መዘጋጀቱንም ገልጸዋል፡፡
ጉዳት ላይ መቆዘም መፍትሔ የለውም፣ ግጭቶችን ወደ ጸጋ መቀየር ይገባል ብለዋል፡፡ ሰላም ላይ በትኩረት መሥራት እንደሚገባም አመላክተዋል፡፡ ችግሮችን ሁሉ ለመፍታት ሰላምን ማምጣት እና ጸጋዎችን መጠቀም እንደሚገባ ነው የተናገሩት፡፡ ሁሉም ያገባኛል ብሎ መሥራት እንደሚጠበቅበትም ገልጸዋል፡፡
ተበታትነን ለውጥ ማምጣት አንችልም፣ ወደ አንድነት እንምጣ፣ ክፋቱን እና መለያየቱን እንተወው፣ ይሄን ካደረግን የክልሉን ችግር እንፈተዋለን ነው ያሉት፡፡ ሁሉም ከንግግር በዘለለ በጦርነት የወደሙ አካባቢዎችን ለመገንባት እና ለማቋቋም ተግባራዊ ሥራ መሥራት አለበትም ብለዋል፡፡
TIPS
Growing relations between Israel and Ethiopia: between military deals, intelligence influence, and an eye on Egypt
The Wars We Still Can Stop
Ethiopia: Israel Foreign Minister Says His Country Wants to Be Part of Ethiopia’s Success
A Nation Silenced: How the 1993 Referendum Stripped All Ethiopians of Their Sea
The 1976 TPLF Manifesto: TPLF’s “Republic of Greater Tigray”
Away from the global spotlight, Eritreans are trapped in a garrison state
Testimonials of a Sudanese Intelligence Officer on the Proxy war between Sudan and Ethiopia from 1970s to early 1990s
Ethiopia-Eritrea Tension: A Volatile History that Never Truly Ended – Could Assab Become Africa’s Crimea?
“As an outlier among the five tplf leaders, I wasn’t part of the armed struggle tradition”
Former Tigray fighters say no to war
Don’t Risk Your Future: The United States Cracks Down on Illegal Immigration
Counter-Video by EBC Challenges EBS Broadcast, Sparks Public Outcry Over Alleged Misinformation
Ethiopia and Eritrea Slide Closer to War amid Tigray Upheaval
Sea Outlet Serious and Unabated Agenda for Ethiopia: Retired Lieutenant General Yohannes
Israel’s Peace With Egypt Is Starting to Crack
Egyptian, Eritrean FMs reject involvement of non-bordering countries[Ethiopia] in Red Sea security