በማሌዥያ የአልጋ ቁራኛ የሆነውን ባለቤቷን ለስድስት ዓመታት ስታስታምም የነበረችው ግለሰብ ከበሽታው ካገገመ በኋላ ሌላ ትዳር መሰረተ
በደረሰበት የተሽከርካሪ አደጋ ለስድስት አመታት የአልጋ ቁራኛ የሆነውን ባሏን የተንከባከበችው ማሌዥያዊት ሴት ባሏ ከበሽታው ካገገመ በኃላ ሌላ ሴት ማግባቷን በቅርቡ አስታውቃለች።
ለዓመታት ኑሩል ስያዝዋኒ የዕለት ተዕለት ህይወቷ የባለቤቷ ጠባቂ በመሆን የምታሳልፈውን ጊዜ በማህበራዊ ድህረ-ገፆች ላይ በማሳየት ስራ የበዛበት ተግባሯን አጋርተች። ይህም ባለቤቷ ምግብ በእጁ ጎርሶ ስለማይወርድለት በናሶጋስቲክ ቱቦ መመገብ፣ ዳይፐር መቀየር እና እንዲታጠብ መርዳት የእርሷ የእለት ከእለት ስራ ነበር። የኑሩል ባል የመኪና አደጋ ከደረሰበት በኃላ እንደገና ለመራመድ ስድስት አመታት መጠበቅ የግድ ብሎት የነበረ ሲሆን በነዚህ ዓመታት ሁሉ ግን እሷ ከጎኑ ነበረች።
ለባሏ ያሳየችው ትጋት እና ታታሪ አገልግሎት በፌስቡክ ላይ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ትኩረት የሳበ ሲሆን ብዙዎቹ የኑሩል ሲያዝዋኒ ባል ካገገመ በኋላ ፈትቷታል፤ ይህም ብቻ ሳይሆን ሌላ ሴት ማግባቱን ሲሰሙ ደንግጠዋል። የእብደት ድርጊት ሲሉ በርካቶች የተደመጡ ሲሆን ኑሩል በፌስቡክ ገጿ የቀድሞ ባለቤቷን እና አዲሲቷን ሙሽሪት እንኳን ደስ አላችሁ ብላለች።ለባለቤቴ እንኳን ደስ አለህ ፤ በመረጥከው ህይወት ደስተኛ እንደሆንክ ተስፋ አደርጋለሁ። አዲሲቱ ሚስቱ አይፋ አይዛም እባካሽ ልክ እንደ እኔ ተንከባከቢው ፤አሁን ተራው የአንቺ ነው ስትል ኑሩል መልዕክቷን አጋርታለች። በጥቅምት 4 መጠናቀቁ የተነገረለት የኑሩል የፍቺ ዜና የማሌዢያን የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎችን ማስደንገጡን ዳጉ ጆርናል ተመልክቷል።
በርካታ ተጠቃሚዎች ደግነቷን ሊከፍላት ይችላል የሚለውን አባባል መቀበል አቅቷቸዋል። በህመሙ ወቅት ከባድ ጊዜን አሳልፌያለሁ በየቀኑ እንዲያገግም እረዳው ነበር፣ ቤተሰቦቼ በየቀኑ ሊረዱኝ ይመጡ ነበር፣ ለልጆቼና ለባለቤቴ የሚያስፈልጉትን ነገሮች ብቻዬን ሳሟላ ቆይቻለሁ ስትል ተደምጣለች።ሆኖም ኑሩል የቀድሞ ባለቤቷ “ኃላፊነቱን በሚገባ እንደተወጣ” እንደሚሰማት ጠቁማ ሰዎች እሱን እና አዲሷን ሚስቱን ማስጨነቅ እንዲያቆሙ ጠይቃለች ። ሆኖም ደጋፊዎቿ በሀሳቧ አልተስማሙም። አንድ ሰው በሰነዘረው አስተያየት “እንዴት እንዲህ ያለው ምስጋና አልባ ሰው ሊኖር ይችላል? ልብ ያለው አይመስለኝም ሲል መደመጡን ዳጉ ጆርናል ዘግቧል።
የቀድሞ ባሏን እና አዲሲቱን ሚስቱን ከብዙሃኑ ትችት ለማዳን ስትል ኑሩል ሲያዝዋኒ በፌስቡክ ላይ የደረሰባትን ያሰፈረችውን ፅሁፏን በማጥፋት ሰዎች ለተፈጠረው ነገር የቀድሞ ባሏን መወንጀል እንዲያቆሙ ደጋፊዎቿን ጠይቃለች።የቀድሞ ባለቤቴን፣ አዲሲቱን ሚስቱን እና ቤተሰቦቻቸውን በፌስ ቡክ ላይ ባጋራሁት መልዕከት ለደረሰባቸው ትችት ይቅርታ መጠየቅ እፈልጋለሁ። የሆነው ሁሉ የእኔ ስህተት ነበር ሲል ኑሩል ጽፋለች።
Vua – Addis_Reporter
TIPS
Growing relations between Israel and Ethiopia: between military deals, intelligence influence, and an eye on Egypt
The Wars We Still Can Stop
Ethiopia: Israel Foreign Minister Says His Country Wants to Be Part of Ethiopia’s Success
A Nation Silenced: How the 1993 Referendum Stripped All Ethiopians of Their Sea
The 1976 TPLF Manifesto: TPLF’s “Republic of Greater Tigray”
Away from the global spotlight, Eritreans are trapped in a garrison state
Testimonials of a Sudanese Intelligence Officer on the Proxy war between Sudan and Ethiopia from 1970s to early 1990s
Ethiopia-Eritrea Tension: A Volatile History that Never Truly Ended – Could Assab Become Africa’s Crimea?
“As an outlier among the five tplf leaders, I wasn’t part of the armed struggle tradition”
Former Tigray fighters say no to war
Don’t Risk Your Future: The United States Cracks Down on Illegal Immigration
Counter-Video by EBC Challenges EBS Broadcast, Sparks Public Outcry Over Alleged Misinformation
Ethiopia and Eritrea Slide Closer to War amid Tigray Upheaval
Sea Outlet Serious and Unabated Agenda for Ethiopia: Retired Lieutenant General Yohannes
Israel’s Peace With Egypt Is Starting to Crack
Egyptian, Eritrean FMs reject involvement of non-bordering countries[Ethiopia] in Red Sea security