አልጃዚራ እንዳለው የሱዳን ፈጣን ኃሃይሎች መሪ ሞሃመድ ሃምዳን ዳጋሎ ግብጽ በሱዳን የውስጥ ጦርነት ተሳታፊ ህናለች ሲሉ ተናግረዋል። ግብጽ በተለይም በአየር ጥቃት መሳተፉን ጠቅሰው ሃምዳን ዳጋሎ ማስጠንቀቃቸውን ተከትሎ ግብጽን ያስደነገጠ መረጃ ተሰምቷል።
የሱዳን ፈጣን RSF ኃይሎች አዛዥ ሙሐመድ ሀምዳን ዳጋሎ ይህ ካሉ በሁዋላ ሄሜቲ የግብፅ ጦር በሱዳን ጦርነት ውስጥ በቀጥታ እየተሳተፈ መሆኑን ከማውገዝም በላይ ታሪክ አንስተው አውግዘዋል። ግብፅ የሱዳን ቁጥር አንድ ጠላት ሆና መቀጠሏን አመልክተው፣ ሱዳን ከእንግሊዝ ቅኝ ገዢዎች ጋር በነበራት የኦሞዱርማን – ቀራር ውጊያ ላይ ግብፆቹ ከእንግሊዝ ወግነው ባሴሩት ደባ የተነሳ ሱዳን በጦርነቱ እንድትሸነፍ ማድረጓንም ጨምረው አውስተው አውስተዋል።
“An advisor from Hemeti’s Rapid Support Forces (RSF) has openly threatened to strike Egypt’s Aswan High Dam! As tensions between #Sudan and #Egypt escalate, this bold warning highlights mounting anger over Egypt’s interference in Sudan’s internal war. Egypt is fueling the conflict”
ዳጋሎ ግብጽ አሜሪካን ሰራሽ ቦምቦችን በአየር ጥቃቱ ወቅት መጠቀሟን፣ ዒላማ ያደረገችውም በጀበል ሞያ ካባቢ የሚገኝ የእሳቸው ኃይል ላይ እንደሆነ ዘርዝረዋል። የጠቀሱትና እሳቸው በሚመሩት ኃይል እጅ እንደህነ ያመለከቱት ስፍራ በደቡብ አቅጣጫ ለሱዳን ዋና ከተማ መዳረሻ ቁልፍ የሆነ ቦታ እንደሆነ አመልክተዋል።
“አሜሪካኖች ስምምነት ባይኖራቸው ኖሮ ይህ ቦምብ ሱዳን ድረስ አይደርስም ነበር ” ማልታቸውን አልጀዚራ ዳጋሎ ካሰርጩት ቪዲዮ መስማቱን ገልጾ ዘግቧል። ይህንን የሄሜቲ ንግግር ተከትሎ የፈጣን ድጋፍ RSF ጦር አማካሪ የተሳተፉበት የዙም ውይይት በትላንትናው ዕለት ተካሂዶ ነበር።
በዚህ ወቅት ከ RSF ጋር ቅርበት አለው የተባለውና በሱዳን ታዋቂ አክቲቪስትና የሚዲያ ሰው አብደል ሞኒም አል ራቢ ግብፅ ከድርጊቷ ካልተቆጠበች “ሁሉም አማራጮች በጠረጴዛ ላይ ናቸው” ሲል ተደምጧል። በዚሁ ንግግሩ ግብጽን ከዳር እስከዳር ያንቀጠቀጠና ያስቆጣ ማስጠንቀቂያ አስተላልፏል።
“የግብፁን አስዋን ግድብ Aswan High Dam መደብደብ አንዱ አማራጫችን ይሆናል!” ሲል በይፋ ማስጠንቀቁን ተከትሎ የግብጽ ሚዲያዎች እየተቀባበሉ ጉዳዩን አጯጩኸውታል።
ይህን ተከትሎ የግብፅ ታዋቂ ሚዲያዎችና አክቲቪስቶች አስካሁንም ድረስ የዘለቀ ጩኸት እያሰሙ ሲያሰሙ ካነሱት ጉዳዮች መካከል አንዱን ፤ “የ RSF አስዋን ግድብን የመምታት ማስጠንቀቂያው የተለያዩ ሃገራት አይዟችሁ ብለዋቸው ነው” የሚል ነው። ይኸው መላምታቸው በተለይም እስራኤል ላይ አነጣጥሯል። “እስራኤል በጉዳዩ ላይ ትኖርበታለች የሚለውን ስጋት አለን” ያሉ ግብፃዊ ሚዲያዎች ደጋግመው ጉዳዩን ሲጠቅሱት ተደምጠዋል።