አል – ሻባብ የጣሊያን መንግስት ለሞቃዲሾ መንግስት በቅርቡ ከለገሰቻቸው ሁለት ሄሊኮፕተሮች መካከል አንዱን መያዙ ነው በዛሬው ዕለት የተዘገበው።
የሶማሊያ ጋዜጠኞች እንደገለፁት ሄሊኮፕተሯ በሶማሊያ ጋልሙዱግ Galmudug ግዛት ውስጥ አልሸባብ በተቆጣጠረው ቦታ እንድታርፍ ተደርጋለች።
በተያዘው የፈረንጆቹ 2024 ውስጥ ለሶማሊያ ሰራዊት የጦር መሳሪያ የጫነ አይሮፕላን አልሸባብ በሚቆጣጠረው አካባቢ ሲያርፍ ይህ ለሶስተኛ ጊዜ ሲሆን ይህም አሸባሪው ቡድን የጦር መሳሪያዎቹን በእጁ እያስገባ የመቀጠሉ ማሳያ ነው።
አል ሸባብ አሁን ወደራሱ ያደረጋት ሄልኮፕተር ወደ ሶማሌ ብሄራዊ ሰራዊት የጦር መሳሪያዎች ጭና በጋልሙሉክ ግዛት አካባቢ በማጓጓዝ ላይ የነበረች ሲሆን በውስጧም ስምንት የበራሪዋ ሰራተኞች ነበሩ ተብሏል።
ጣልያን በቅርቡ ለሶማሊያ የለገሰቻቸው 4 ሄልኮፕተሮች ‘Bell 412 Multipurpose’ ሄልኮፕተሮች ሲሆኑ እያንዳንዳቸውም 16 ሚሊዮን ዶላር ዋጋ ያላቸው ናቸው። ይሁንና አል ሸባብ ያዛት የተባለችው ሄልኮፕተር ጣልያን ከለገሰቻቸው 2 ሄልኮፕተሮች መካከል ናት የሚሉት ከሶማሊያ የወጡ ሪፖርቶች፣ አል ሻባብ የያዛት Bell 412 ወይም ሌላ አይነት ሄልኮፕተር ስለመሆኗ የሚያስረግጡ መረጃዎች ለጊዜው አልተገኙም።
በርካታ ምንጮች እንደሚገልፁት ለሞቃዲሹ መንግስት ከተላኩት የጦር መሳሪያዎች ውውጥ 90 በመቶ የሚሆኑት በተለያዩ መንገዶች በአልሸባብ እጅ ይወድቃሉ። ይህን መሰል የጦር መሳሪያ የጫኑ አውሮፕላኖች በአልሸባብ ቁጥጥር ስር ባሉ አካባቢዎች ከማረፋቸው ባሻገር፣ የሶማሊያ ብሄራዊ ሰራዊት ወታደሮች ሳይቀር የጦር መሳሪያቸውን ብዙ ጊዜ ለአልሸባብ በመሸጥ ጫት ለመግዛት እንደሚያውሉት ይገለፃል። የአዲስ ሪፖርተር መረጃ ያስረዳል
TIPS
The Wars We Still Can Stop
Ethiopia: Israel Foreign Minister Says His Country Wants to Be Part of Ethiopia’s Success
A Nation Silenced: How the 1993 Referendum Stripped All Ethiopians of Their Sea
The 1976 TPLF Manifesto: TPLF’s “Republic of Greater Tigray”
Away from the global spotlight, Eritreans are trapped in a garrison state
Testimonials of a Sudanese Intelligence Officer on the Proxy war between Sudan and Ethiopia from 1970s to early 1990s
Ethiopia-Eritrea Tension: A Volatile History that Never Truly Ended – Could Assab Become Africa’s Crimea?
“As an outlier among the five tplf leaders, I wasn’t part of the armed struggle tradition”
Former Tigray fighters say no to war
Don’t Risk Your Future: The United States Cracks Down on Illegal Immigration
Counter-Video by EBC Challenges EBS Broadcast, Sparks Public Outcry Over Alleged Misinformation
Ethiopia and Eritrea Slide Closer to War amid Tigray Upheaval
Sea Outlet Serious and Unabated Agenda for Ethiopia: Retired Lieutenant General Yohannes
Israel’s Peace With Egypt Is Starting to Crack
Egyptian, Eritrean FMs reject involvement of non-bordering countries[Ethiopia] in Red Sea security
Ethiopia, Creditors Agree on $8.4 Billion Debt Restructuring