በአፋር ክልል ንዝረቱ እስከ አዲስ አበባ የደረሰ የመሬት መንቀጥቀጥ በተደጋጋሚ እየተከሰተ መሆኑ ይታወቃል።
በቦታው የባለሙያ ቲም አዋቅሮ የላከው ሰመራ ዩኒቨርሲቲ፣ ትላንት እና ከትላንት በስቲያ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋው እንደተከሰተ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አረጋግጦ ለአካባቢው ማህበረሰብ ልዩ ትኩረት እንዲደረግ በአጽንኦት አሳስቧል።
ህዝቡ ላይ የከፋ ከደጋ እንዳይደርስ የሚመለከታቸው አካላት ሊያደርጉት የሚገባው ርብርብ ምንድን ነው ? ስንል የጠየቅናቸው ዩኒቨርሲቲው የጂኦሎጂ ትምህርት ክፍል ተመራማሪና መምህር ኖራ ያኒሚኦ ምላሽ ሰጥተዋል።
“ የአደጋው ምክንያት ምንነት አሁን ታውቋል። አደጋው የተፈጠረው የቀለጠ አለት በሚያደርገው እንስቃሴ ነው።
ስለዚህ የከሰም ግድብ የሚባል ስኳር ፋብሪካ አካበቢ አለ። አደጋው እዛ አካባቢ ላይ የሚከሰት ከሆነ የከፋ ጉዳት ሊያከተል ይችላል። ምክንያቱም የመሬት መንቀጥቀጡ በተከታታይ እየተፈጠረ ነው።
አደጋው ካልቆመና የግድቡ አካል የሚነካ ከሆነ ከግድቡ ቁልቁለት አካባቢ የሚኖሩ የህብረተሰብ ክፍሎች የከፋ ጉዳት ሊያደርስ ይችላል።
ስለዚህ በተለይ የአዋሽ ፈንታሌ የወረዳ ካቢኔዎች፣ የዞን አስተዳዳሪዎች ህብረተሰቡን ከቁልቁለታማው ቦታ የውሃ ፍስት ወደማይደርስበት ወደ ሌላ ቦታ ያውርዱ።
ተራራ ስር አካባቢ የሚኖሩ ሰዎችን ታዝበናልና እነዛ ሰዎች ወደ ሜዳ የሚመጡበት መንገድ ቢፈጠር ሊከሰት የሚችለውን ጉዳት ሊቀንስ ይችላል ” ሲሉ አስገንዝበዋል።
የዩኒቨርሲቲው የምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ተጠባባቂ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አደም አሊ በበኩላቸው፣ ወደ ቦታው ባለሙዎችን እንደላኩ ገልጸው፣ “ በአካባቢው የግድብ ስራዎች አሉ። አደጋው ከጨመረ ቀፈን ቀበና ያለው ግድብ ትልቅ ፋክተር ተደርጎ ተፈርቷል ” ብለዋል።
“ ከፍተኛ የሆነ ጥንቃቄ ሊደረግለት ይገባል ግድቡ። አንዴ ጉዳት ከደረሰበት ህዝቡን ጠራርጎ ነው የሚወስደው። ከፍተኛ ቦታ ላይ ነው ያለው። በጣም ብዙ መሬትን ሊያካልል የሚችልም ነው ” ሲሉ አስጠንቅቀዋል።
አደጋው የሚጨምር ነው የሚቀንስ ? ምን እየተሰራ ነው ? አደጋው ሊያስከትለው የሚችለው ጉዳትስ በምን ደረጃ ነው ? ስንል የጠየቅናቸው ተመራማሪና መምህር ኖራ በበኩላቸው ተከታዩ ማብራሪያ ችረዋል።
“ የመሬት መንቀጥቀጡ እየተፈጠረ ያለው በአፋር ክልል አዋሽ ፈንታሌ ነው። ከሦስት ሳምንታት ወዲህ የትላንት ስድስት ሰዓቱን ጨምሮ አደጋው ሦስት ጊዜ ተከስቷል።
መነሻው በክልሉ ሳቡሪ ቀበሌ ነው። ከዛ ተነስቶ ነው እስከ አዲስ አበባ፣ አዳማ፣ አዋሽ አካባቢዎች ላይ ንዝረቱ የሚሰማው።
በዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት አማካኝነት አንድ ቲም ተዋቅሮ ለሁለት ሳምንታት በቦታው ተገኝተን ምልከታዎችን እያደረግን ነው። ሙያዊ ሥራዎችን እየሰራን ነው። ለህዝቡ የግንዛቤ ማስጨበጫ እየሰጠንም ነው።
የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ የሚከሰትበትን ቦታ መለየት ይቻላል። በዚህ ሰዓት ሊከሰት ይችላል ተብሎ የሚገመት ግን አይደለም። አሁን ባለን ቴክኖሎጂና እውቀት ቦታዎቹን መለየት ብቻ ነው የሚቻለው።
የመሬት መንቀጥቀጥ ዋናው ምክንያቱ ከሥር የቀለጠው አለት ከፍተኛ እንቅስቃሴ ነው። ስለዚህ ማግማው ወደላይ ሰንጥቆ መውጣት እስከሚያቆም ድረስ አደጋው ቀጣይነት ሊኖረው ይችላል።
እስካሁን ድረስ እየተመዘገበ ያለው ከ4.5 እስከ 4.9 ሬክተር ስኬል አካባቢ ነው፤ ይሄም ያን ያክል ጉዳት የሚያደርስ አይደለም መካከለኛ ስኬል ነው። 7 እና ከዚያ በላይ ከሆነ ነው አደጋው ከፍተኛ ሊሆን የሚችለው ” ብለዋል።
በመጀመሪያ የመሬት መንቀጥቀጥ በተከሰተበት ቦታ ፍል ውሃ መፍለቁ፤ ነዋሪውም ውሃውን ከመጠቀም እንዲቆጠብ ማሳሰቢያ መሰጠቱ ይታወሳል፤ የተገኘ የምርምር ውጤት አለ እንዴ ? ለሚለው ጥያቄ ምላሻቸው፣ “ አሰስመንት ላይ ነን። ካጠናቀቅን በኋላ ሙሉ መረጃ እናጋራለን ” የሚል ነው።
Via tikvahethiopia
TIPS
The Wars We Still Can Stop
Ethiopia: Israel Foreign Minister Says His Country Wants to Be Part of Ethiopia’s Success
A Nation Silenced: How the 1993 Referendum Stripped All Ethiopians of Their Sea
The 1976 TPLF Manifesto: TPLF’s “Republic of Greater Tigray”
Away from the global spotlight, Eritreans are trapped in a garrison state
Testimonials of a Sudanese Intelligence Officer on the Proxy war between Sudan and Ethiopia from 1970s to early 1990s
Ethiopia-Eritrea Tension: A Volatile History that Never Truly Ended – Could Assab Become Africa’s Crimea?
“As an outlier among the five tplf leaders, I wasn’t part of the armed struggle tradition”
Former Tigray fighters say no to war
Don’t Risk Your Future: The United States Cracks Down on Illegal Immigration
Counter-Video by EBC Challenges EBS Broadcast, Sparks Public Outcry Over Alleged Misinformation
Ethiopia and Eritrea Slide Closer to War amid Tigray Upheaval
Sea Outlet Serious and Unabated Agenda for Ethiopia: Retired Lieutenant General Yohannes
Israel’s Peace With Egypt Is Starting to Crack
Egyptian, Eritrean FMs reject involvement of non-bordering countries[Ethiopia] in Red Sea security
Ethiopia, Creditors Agree on $8.4 Billion Debt Restructuring