ልጆችን የምታስቦርቀው፣ እናቶችን የምታስቀው፣ ሞት እና መከራን የምታርቀው፣ መውደቅ እና መውደምን የምታስቀረው ሰላም ስለ ምን ዋጋዋ ቀለለ? ገበሬው አርሶ የሚያጎርስባት፣ አርብቶ አደሩ አልቦ የሚያቀርብባት፣ ነጋዴው ነግዶ የሚያተርፍባት፣ መምህሩ ዕውቀትን በትውልድ ልቡና ላይ የሚዘራባት፣ ተማሪዎች ዕውቀትን የሚገበዩባት፣ ወገን ከወገኑ በፍቅር የሚገናኝባት፣ ሐኪሞች ያለ ስጋት ሕሙማንን ለመርዳት የሚጣደፉባት ሰላም ስለ ምን ችላ ተባለች?
ሠርግ የሚሠረግባት፣ ገበያው የሚጠግብባት፣ አረጋውያን የሚጦሩባት፣ እስከ ዘመነ ፍጻሜያቸው በኩራት ታሪክ የሚነግሩባት፣ ሕጻናት በተድላ እና በደስታ የሚያድጉባት፣ ወላጆች የድካማቸውን ፍሬ የሚያዩባት ሰላም ስለ ምን ተጠላች?
እልህ የያዛቸው ልቦች የሚራሩት፣ ለሰላም የታጠፉ እጆች የሚዘረጉት፣ ለወላጆች እንባ የሚያዝኑ አንጀቶች የሚገኙት፣ ወደ ሰው የዞሩ አፈሙዞች የሚመለሱት፣ በሰው ደም የሚሳለቁት እንደ ሰው የሚያዝኑት፣ የተዘጉ የውይይት በሮች የሚከፈቱት፣ ትግሎች ሁሉ በጠረጴዛ ላይ በእስክብሪቶ ብቻ የሚኾኑት፣ ጎዳናዎች ሰላም የሚያገኙት፣ ወገኖች በሰላም የሚንቀሳቀሱት፣ የግጭት ነጋሪቶች የማይጎሰሙት፣ የፍቅር እንቢልታዎች የሚነፉት መቼ ነው? ሽማግሌዎች የሚሰሙት፣ የሃይማኖት አባቶች የሚከበሩት፣ የሰላም ስብከቶች ማረፊያ ልብ የሚያገኙት፣ የሚፈስሱ ደሞች የሚቆሙትስ መቼ ነው?
ስቀለው፣ ውሰደው፣ በለው የሚሉ ድምጾች፣ ሰላም ሁኑ፣ እርቅን ውደዱ፣ ሰላምን አስቀድሙ፣ ፍቅርን አስበልጡ፣ ተዋደዱ፣ ወንድም በወንድሙ ላይ አይነሳ እያሉ የሚሰብኩት መቸ ነው?
በግጭት ምክንያት ሥራ ያጡ ወገኖች፣ ድህነት እና የሰላም እጦት ሕይዎታቸውን ያጎበጠባቸው አቅመ ደካሞች አኗኗር ለሰላም እጅ እንዲዘረጉ አያስገድድምን? ይሄን ያክል ሰላምን መጥላት፣ ግጭት እና ጦርነትን መናፈቅስ ጤንነት ነውን? ታናናሾች እንዳይማሩ መከልከልስ ሕዝብን የመውደድ ምልክት ነውን?
በየቀኑ መገዳደሉ አይበቃምን? ሰላም ሁኑ ብለው የሚለምኑ አባቶችን እና እናቶችን መስማት አይጠቅምምን? ለወገን ሰላም ሲባል አንተም ተው ማለት አያስፈልግምን ? በሚሊዮን የሚቆጠሩ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ መራቅ አያሳዝንምን? ሕጻናት ያለበደላቸው ከእኩዮቻቸው ሲያንሱ፣ በጥይት ድምጽ ወስጥ ኾነው ሲጨነቁ አያስለቅሱምን? የአባቶች እና የእናቶችን የሽምግልና ጥሪ መግፋትስ ግፍ አይኾንም?
ሌሎች በሰላም እየሠሩ በዕድገት ጥለውን ሲሄዱ አያስቆጭምን? አረጋውያን እና ሕጻናትን ማገት እና ማፈንስ ለሕዝብ መጥቀም ነውን? መድረሻው የት ነው? ዓላማውስ ምንድን ነው? ሚሊዮኖችን ዕውቀት አልባ ማድረግ፣ ፋብሪካዎችን ማዘጋት፣ ማሳውን ጦም ማሳደር፣ የልማት ሥራዎችን ማደናቀፍ ለምን?
በአማራ ክልል የተፈጠረው የጸጥታ ችግር እልፍ ጉዳይ አሳጥቷል፡፡ ከአንድ ዓመት የተሻገረው ግጭት በሰላም ይፈታ ይኾን የሚለው ተስፋ እውን ሳይኾን ጊዜዎች ነጉደዋል፡፡ ተስፋ የተጣለባቸው የሰላም ጥሪዎችም እውን ሳይኾኑ ቀናት ሳምንታትን፣ ሳምንታት ወራትን እየተኩ ቀጥለዋል፡፡ በዚህ ሁሉ ሂደት ታዲያ በየቀኑ የመከራ ገፈት የሚቀምሱ ንጹሐን ሞልተዋል፡፡
መንግሥት የሰላም ጥሪዎቼ ዋጋ ሳይኖራቸው ቀርቷል፤ ለሰላም የዘረጋኋቸው እጆቼም የሚቀበላቸው አጥተዋል፤ ለሰላም የከፈትኳቸው በሮችም የሚገባባቸው አልተገኘም፤ በአማራ ክልል የተፈጠረውን ችግር እፈታ ዘንድ ኀይል መጠቀም ግዴታ ኾኖብኛል ብሏል፡፡ የአማራ ክልል መንግሥት እና የሀገር መከላከያ ሠራዊትም በቅንጅት የሕግ ማስከበር ሥራ እየሠራን ነው ብለዋል፡፡
የአማራ ክልል ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ኀላፊ መንገሻ ፈንታው (ዶ.ር) በክልሉ እና በሀገሪቱ አስተማማኝ እና ዘላቂ ሰላም እንዲመጣ ለማድረግ የሕግ ማስከበር ሥራ እየተሠራ ነው፣ ሰላሙን ቀድሞ ወደነበረበት ለመመለስ እየተሠራ ነው ይላሉ፡፡ ሥልጣን በሰላማዊ መንገድ የሚገኝ ኾኖ ሳለ በኀይል ሥልጣን ለመውሰድ የተነሱ ቡድኖች ሕዝባችንን ለመከራ እየዳረጉት ነው ብለዋል፡፡ ሥልጣን በሥርዓት እና በሕግ ብቻ ይያዛል እንጅ በኀይል አይያዝም ነው የሚሉት፡፡
እንደ ኀላፊው ገለጻ ሰላማችን እንዲናጋ በሀገር ውስጥ እና በውጭ ያሉ ጠላቶቻችን እጅ እና ጓንት ኾነው በሕዝባችን ላይ ሰፊ ችግር ሲያደርሱበት ቆይተዋል፤ ችግሮችን ለመፍታት ከሕዝብ ጋር ተወያይተናል፣ የሰላም እጆች ተዘርግተው፣ ወደ ሰላም እንዲመጡ ጥረት ተደርጓል ጥረታችን ግን ውጤት አላመጣም ነው የሚሉት፡፡
የሰላም ጥሪዎች ቀርበዋል፣ ድርድር እንዲካሄድም ጥሪ ቀርቧል፣ በየትኛውም ቦታ፣ በየትኛውም ሰው እና በየትኛውም ጊዜ ለመደራደር መንግሥት ዝግጁ መኾኑን በተደጋጋሚ ለምኗል፤ ጥሪው ግን ከምንም አልተቆጠረም ይላሉ፡፡ በባሕሪው ጽንፈኛ በተግባሩ ደግሞ ዘራፊ የኾነው ኀይል የሰላም ጥረታችንን ከምንም አልቆጠረውም፣ ይባስ ብሎ የሰላም አምባሳደሮች የኾኑ የሀገር ሽማግሌዎችን፣ የሃይማኖት አባቶችን እና እናቶችን እያንገላታ ብዙ ግፍ አድርሶባቸዋል ነው ያሉት፡፡
ጽንፈኛው ኀይል የሰላም ጥሪ የያዙ ሰዎች እንዳይመጡበት አውጇል፣ ሰላምን ጠልቷልም ይላሉ ዶክተር መንገሻ፡፡ በክልሉ ሕጻናት ተገድለዋል፣ ነጋዴዎች እንዳይነግዱ ተደርገዋል፣ አርሶ አደሮች ምርታቸውን ወደገበያ እንዳያቀርቡ፣ የኑሮ ውድነት እንዲባባስ፣ ማዳበሪያ ወደ አርሶ አደሮች እንዳይቀርብ ሠርተዋል፤ በክልሉ ግፍ እና በደል ተፈጽሟል ነው ያሉት፡፡
ታዲያ ይሄን ግፍ እና በደል ታግሰን የምንቆዬው እስከ መቼ ነው? በግልጽ ከሀገራችን ውስጣዊ እና ውጫዊ ጠላቶቻችን ጋር እየሠሩ ነው፣ ታዲያ ይሄን እንዴት እንታገሰው? ነው የሚሉት፡፡ ለሰላም እጃችን ዘረጋን ግን ሰላም የወደደ ኀይል የለም፤ ይሄን የተረዳው መንግሥት ሕግ ማስከበር ጀምሯል፣ ሰላምን አማራጭ አድርጎ ያልወሰደውን የመጨረሻ እርምጃ ይወስዳል ነው ያሉት፡፡
በአጭር ጊዜ ችግሩን በመቀልበስ ሰላምን ማምጣት ይኖርብናል፤ ዓላማችንም ሰላምን ማምጣት ነው፣ አሁንም የሰላም አማራጭ ዝግ አይደለም፣ ሕዝቡ ለሰላም የሚደረገውን የሕግ ማስከበር እርምጃ መደገፍ አለበት ነው ያሉት፡፡ የሀገር መከላከያ ሠራዊት የቆመበት ዋነኛ ዓላማ ሕዝብን ከጥቃት ለመከላከል መኾኑንም አንስተዋል፡፡
ሕዝብ ሰላሙን መጠበቅ አለበት፣ ክልሉን የልማት ማዕከል ማድረግ አለብን፣ ትምህርት ቤቶች መከፈት አለባቸው ይላሉ፡፡ የምጣኔ ሃብት ምሁራን ክልሉ እየደረሰበት ያለውን ውድመት ማሳወቅ አለባቸው፣ መስዋዕት እየከፈልንም ቢኾን ለሰላም መሥራት አለብን ነው ያሉት፡፡ ሁሉም ለሰላም የየራሱን ድርሻ ማዋጣት እንዳለበትም አሳስበዋል፡፡
የሀገር መከላከያ ሠራዊት የሕዝብ ግንኙነት ኀላፊ ኮሎኔል ጌትነት አዳነ የሀገር መከላከያ ሠራዊት ሀገርን ከውጭ እና ከውስጥ ጠላቶች የመከላከል ግዳጅ እንደተሰጠው ይገልጻሉ፡፡ ከውጭም ከውስጥም የሚመጣን ጠላት መከላከል፣ የሀገር ሉዓላዊነትን የሚያፈርስ ጉዳይ ሲገጥም መጠበቅ፣ ማስቆም ተልዕኳችን ነው፣ በአማራ ክልል እያደረግነው ያለውም ይሄንኑ ነው ይላሉ፡፡
ጽንፈኛ ኀይሉ ፀረ ሕዝብ የኾነ፣ ዓላማው የተዘበራረቀ እና መጨበጫ የሌለው፣ የያዘው ስም ልኩ ያልኾነ፣ የሚያደርገው ተግባር የረከሰ እና የወረደ፣ የአማራን ሕዝብ የማይመጥን፣ በታሪካችን አጋጥሞን የማያውቅ ነው ይሉታል ኮሌኔሉ፡፡ አትማሩም፣ አትነግዱም የሚለውን ሁከት እና ግርግር ማስቆም እና መልክ ማስያዝ አለብን፣ ዓላማችን በክልሉ ሰላምን መፍጠር ነውም ይላሉ፡፡
ጽንፈኛ ቡድኑ የሽምግልና ባሕል እና ወግ እንዲጠፋ፣ ሽማግሌዎች ተንበርክከው እንዲሄዱ ያደረገ ነው፤ ለሰላም እጃችን ስንዘረጋ እንቢ ያለ ኀይል መመታት ያስፈልገዋል፤ ሰላም የሚመጣውም ሲመታ ነው፤ ሴሉን ከሕዝብ የለየ፣ መሪውን ከጀሌው የነጠለ ኦፕሬሽን መውሰድ ጀምረናል ነው ያሉት፡፡
ታግሰን እየለመን ተወያይተናል፣ ይሄ ግን አልኾነም፣ አስተማማኝ ሰላም እስኪመጣ ድረስ እርምጃ ይወሰዳል፤ እስካሁን ተለምኗል፤ ከዚህ በኋላ መከላከያ የሚወስደው እርምጃ ነው ይላሉ፡፡
መንግሥት አሁንም የሰላም በር ዝግ አይደለም ብሏል፤ ታዲያ ሰላምን መምረጥ ለምን አቃተን? አሁንም፣ ነገም ከዚያ ወዲያም ሰላምን መጠቀም ከብዙ ኪሣራ ያድናል፤ ሕዝብንም ይጠቅማል፡፡ ሰላምን መምረጥ ሕዝብን መውደድ፣ ወገንን ማክበር ነው፡፡
አሚኮ
TIPS
Growing relations between Israel and Ethiopia: between military deals, intelligence influence, and an eye on Egypt
The Wars We Still Can Stop
Ethiopia: Israel Foreign Minister Says His Country Wants to Be Part of Ethiopia’s Success
A Nation Silenced: How the 1993 Referendum Stripped All Ethiopians of Their Sea
The 1976 TPLF Manifesto: TPLF’s “Republic of Greater Tigray”
Away from the global spotlight, Eritreans are trapped in a garrison state
Testimonials of a Sudanese Intelligence Officer on the Proxy war between Sudan and Ethiopia from 1970s to early 1990s
Ethiopia-Eritrea Tension: A Volatile History that Never Truly Ended – Could Assab Become Africa’s Crimea?
“As an outlier among the five tplf leaders, I wasn’t part of the armed struggle tradition”
Former Tigray fighters say no to war
Don’t Risk Your Future: The United States Cracks Down on Illegal Immigration
Counter-Video by EBC Challenges EBS Broadcast, Sparks Public Outcry Over Alleged Misinformation
Ethiopia and Eritrea Slide Closer to War amid Tigray Upheaval
Sea Outlet Serious and Unabated Agenda for Ethiopia: Retired Lieutenant General Yohannes
Israel’s Peace With Egypt Is Starting to Crack
Egyptian, Eritrean FMs reject involvement of non-bordering countries[Ethiopia] in Red Sea security