ኢ-ፓስፖርት ማምረት ተጀምሯል፣
ፓስፓርት የሚያገለግልበት ጊዜ ገደብ ከነበረበት አምስት ዓመት ወደ አስር አመት ከፍ ሊደረግ መሆኑን የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ገለጸ።
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ሰላማዊት ዳዊት ለጋዜጤኞች በሰጡት መግለጫ እንደገለጹት፣ ፓስፓርት የሚያገለግልበት ጊዜ ገደብ ከነበረበት አምስት ዓመት ወደ አስር አመት ከፍ ይደረጋል።
ፓስፖርት የሚያገለግልበት የጊዜ ገደብ አምስት ዓመት እንደነበር የገለጹት ወይዘሮ ሰላማዊት ፓስፖርት የሚያገለግልበት ጊዜ ገደብ ወደ አስር ዓመት ከፍ ይደረጋል ብለዋል።
የጊዜ ገደቡ ከዚህ በፊት የታተሙትን እንደማይመለከት በመግለጽ ከዚህ በኋላ የሚታተሙ ፓስፖርቶች የጊዜ ገደብ አስር ዓመት እንደሚሆን ተናግረዋል።
የጊዜ ገደቡን ወደ 10 ዓመት የማሻሻል ስራዎችም ከሚቀጥሉት ሩብ አመት ይጀምራል ብለዋል።
አሁን ያለዉን የፓስፖርት ቡክሌት ወደ ኢ-ፓስፖርት ለመቀየር ምርት መጀመሩን ጠቅሰው በመጪው የፈረንጆቹ አዲስ አመት የመጀመሪያ ወር መስጠት እንደሚጀመር ገልጸዋል።
በሩብ ዓመቱ ውስጥ 478 ሺህ ቡክሌት ወደ ሀገር ውስጥ ማስገባት ተችሏል ያሉት ወይዘሮ ሰላማዊት ከ367 ሽህ በላይ ፖስፖርቶች ታትሞ ማሰራጨት ተችሏል ብለዋል፡፡
ከታተመው ፓስፖርት ውስጥ 357 ሺህ 036 ተገልጋዮች ፓስፖርታቸውን መውሰዳቸውን ጠቅሰው
በሩብ አመቱ 559 ሺህ 848 በአየር ኬላ ወደሀገር መግባታቸውን በመግለጽ 581 ሺህ 704 መንገደኞች ከሀገር የወጡ መሆናቸውን ተናግረዋል።
በየብስ ኬላ 106 ሺህ ,003 ደንበኞች ወደሀገር መግባታቸውን ጠቅሰው 131 ሺህ 869 ከአገር መውጣታቸውን ገልጸዋል።
በማርቆስ በላይ
ጥቅምት 1 ቀን 2017 ዓም
TIPS
Growing relations between Israel and Ethiopia: between military deals, intelligence influence, and an eye on Egypt
The Wars We Still Can Stop
Ethiopia: Israel Foreign Minister Says His Country Wants to Be Part of Ethiopia’s Success
A Nation Silenced: How the 1993 Referendum Stripped All Ethiopians of Their Sea
The 1976 TPLF Manifesto: TPLF’s “Republic of Greater Tigray”
Away from the global spotlight, Eritreans are trapped in a garrison state
Testimonials of a Sudanese Intelligence Officer on the Proxy war between Sudan and Ethiopia from 1970s to early 1990s
Ethiopia-Eritrea Tension: A Volatile History that Never Truly Ended – Could Assab Become Africa’s Crimea?
“As an outlier among the five tplf leaders, I wasn’t part of the armed struggle tradition”
Former Tigray fighters say no to war
Don’t Risk Your Future: The United States Cracks Down on Illegal Immigration
Counter-Video by EBC Challenges EBS Broadcast, Sparks Public Outcry Over Alleged Misinformation
Ethiopia and Eritrea Slide Closer to War amid Tigray Upheaval
Sea Outlet Serious and Unabated Agenda for Ethiopia: Retired Lieutenant General Yohannes
Israel’s Peace With Egypt Is Starting to Crack
Egyptian, Eritrean FMs reject involvement of non-bordering countries[Ethiopia] in Red Sea security