በሶማሌ ክልል ሰርጎ በመግባት ጥቃት ለመፈፀም በተንቀሳቀሱ 60 የአልሻባብ የሽብር ቡድን አባላት ላይ እስከ ዕድሜ ልክ የፍርድ ውሳኔ መተላለፉን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አስታወቀ
በሀገራችን ሶማሌ ክልል አፍዴር እና ሸበሌ ዞኖች በኩል ሰርጎ በመግባት ጥቃት ለመፈፀም ሲንቀሳቀሱ የነበሩ 60 የቡድኑ አባላት በቁጥጥር ሥር ውለው በ10 የምርመራ መዝገብ ተከሰው እስከ ዕድሜ ልክ እስራት የፍርድ ቤት ውሳኔ የተላለፈባቸው መሆኑን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አስታውቋል፡፡
ፖሊስ በ60 የሽብር ቡድኑ አባላት ላይ በቂ የቴክኒክና የታክቲክ ማስረጃ በማቅረብ በሽብር ወንጀል ምርመራ አጣርቶ ለፍትህ ሚኒስቴር በመላክ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ድሬዳዋ ምድብ ተዘዋዋሪ ችሎት ሁለት የሽብር ቡድኑ ከፍተኛ አመራሮች በዕድሜ ልክ እስራት፣ 56 ተከሳሾች እንደወንጀል ተሳትፎአቸው ከ6 ዓመት እስከ 18 ዓመት ፅኑ እስራት እና በአልሸባብ የሽብር ቡድን አባልነት የተከሰሱ ሁለት ተከሳሾች እያንዳንዳቸው 2 ዓመት ከ6 ወር እስራት እንዲፈረድባቸው ማድረጉን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ገልጿል፡፡
በዚያን ወቅት በሀገራችን አንዳንድ አካባቢዎች የተፈጠሩ የፀጥታ ችግሮችን እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም የአልሸባብ የሽብር ቡድን ኢትዮጵያ ውስጥ ወታደራዊ ቤዝ ለመመስረት፤ ከአንዳንድ የሀገራችን አካባቢዎች ወጣቶችን በመመልመል፤ በሶማሊያ ሀገር ወታደራዊ ስልጠና ወስደው የጦር መሣሪያ ሳይታጠቁ ሰላማዊ ሰው መስለው ወደ ሀገራችን እንዲገቡ በማድረግ፣ ለሽብር ቡድኑ በመሰለል፣ ፈንጂ በማፈንዳት ድንገተኛ ጥቃት በመፈፀም አካባቢዎችን የሚቆጣጠር ኃይል ለማዘጋጀት ሲንቀሳቀስ እንደነበር የምርመራ ቡድኑ ባካሄደው ማጣራት ደርሶበታል፡፡
የሽብር ቡድኑ ሐምሌ 11 ቀን 2014 ዓ.ም ከሶማሊያ ሀገር በሰባት ተሸከርካሪና በአራት ሞተር ሳይክል በሌሊት ወደ ሀገራችን ሶማሌ ክልል አፍዴር ዞን ሁሉል አካባቢ ሲደርስ የሶማሌ ክልል ፖሊስ ከአካባቢው ነዋሪዎች ጋር በመተባበር ከአራት ቀን እልህ አስጨራሽ ውጊያ በኋላ በርካታ የሽብር ቡድኑን አባላት በመደምሰስ ሁለት ከፍተኛ አመራርን ጨምሮ 92 የሽብር ቡድኑ ታጣቂዎችን በመማረክ 406 ክላሽንኮቭ ጠመንጃ ከ67 ሳጥን መሰል ጥይቶች፣ 43 ላውንቸር እና 27 ብሬን ከአንድ ሳጥን መሰል ጥይት ጋር እንዲሁም በርካታ ተቀጣጣይ ፈንጂዎችን በኤግዚቢትነት መያዛቸውን የምርመራ መዝገቡ ያስረዳል፡፡
ከዚሁ ጋር በተያያዘ በስድስት የምርመራ መዝገብ 95 ተጠርጣሪዎች በሽብር ወንጀል ጉዳያቸው በፍርድ ቤት ክርክር ላይ እንደሚገኝ ከፌደራል ፖሊስ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
TIPS
Growing relations between Israel and Ethiopia: between military deals, intelligence influence, and an eye on Egypt
The Wars We Still Can Stop
Ethiopia: Israel Foreign Minister Says His Country Wants to Be Part of Ethiopia’s Success
A Nation Silenced: How the 1993 Referendum Stripped All Ethiopians of Their Sea
The 1976 TPLF Manifesto: TPLF’s “Republic of Greater Tigray”
Away from the global spotlight, Eritreans are trapped in a garrison state
Testimonials of a Sudanese Intelligence Officer on the Proxy war between Sudan and Ethiopia from 1970s to early 1990s
Ethiopia-Eritrea Tension: A Volatile History that Never Truly Ended – Could Assab Become Africa’s Crimea?
“As an outlier among the five tplf leaders, I wasn’t part of the armed struggle tradition”
Former Tigray fighters say no to war
Don’t Risk Your Future: The United States Cracks Down on Illegal Immigration
Counter-Video by EBC Challenges EBS Broadcast, Sparks Public Outcry Over Alleged Misinformation
Ethiopia and Eritrea Slide Closer to War amid Tigray Upheaval
Sea Outlet Serious and Unabated Agenda for Ethiopia: Retired Lieutenant General Yohannes
Israel’s Peace With Egypt Is Starting to Crack
Egyptian, Eritrean FMs reject involvement of non-bordering countries[Ethiopia] in Red Sea security