በተረፈ የሰሞኑ ድራማ እና ቡትቶው ጥምረት “የቀይ ባህር ጉዳይ”ን እንደ ሰበብ የሚጠቀም እንጂ፤ መሰረታዊ መንስኤው (the structural cause) “የቀይ ባህር ጉዳይ” እንዳልሆነ ሁሉም ሊረዳው ይገባል። ግብፅ ቀይ ባህር ላይ ያላትን ጥቅም ለማስጠበቅ የሁለት ድንክዬዎችን [የሶማሊያን እና የኤርትራን] ድጋፍ አትሻም። ሶማሊያም የህንድ ውቅያኖስ እንጂ “የቀይ ባህር ሃገር” አይደለችም። ከሁሉም በላይ ጉዳዩ የቀይ ባህር ጉዳይ ቢሆን ኖሮ የምንጋፈጠው እነዚህን ሶስት ሃገራት ብቻ አልነበረም። ነገሩን “የቀይ ባህር ጉዳይ” አድርገው ሊያጮሁት የሚፈልጉት የኤርትራ operatives፣ ተላላኪዎች እና አንዳንድ አላዋቂ ኢትዮጵያውያን ናቸው። ከላይ እንደተገለፀው የቡትቶው ጥምረት መሰረት የማይናበቡ
BBC “The Axis against Ethiopia” ብሎታል የሰሞኑን በግብፅ ደራሲነት፣ በኤርትራ መድረክነት፣ በአል ሲሲ፣ በኢሳያስ እና በሐሰን ሼኽ ተዋናይነት የተተወነ ድራማ። እኔ ደግሞ The Hodgepodge Alliance (ቡትቶው ጥምረት) እለዋለሁ። እንደሚታወቀው “በፖለቲካ በተለይም በዓለም ዓቀፍ ፖለቲካ ዘላቂ ጥቅም እንጂ ዘላቂ ወዳጅነት የለም”። የፖለቲካዊ ግንኙነት መሰረቱ ብሄራዊ ጥቅም ነው። ሃገራት ብሄራዊ ጥቅማቸውን መሰረት ያደረጉ በርካታ የተናጠል ጥረቶችን ያደርጋሉ። “ብሄራዊ ጥቅማችን ተቀራርቧል/ተመሳስሏል” ብለው ባመኑ ጊዜ ደግሞ ጥምረት (alliance) ይመሰርታሉ።
ለምሳሌ በመጀመሪያው ፎቶ ላይ የሚታዩት የአፍሪካ ቀንድ ሃገራት መሪዎች ቢጣመሩ ሊሰምር የሚችለውን ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊ እና ማህበራዊ ጥቅም ታሳቢ ያደረገ ጥምረት ለመመስረት በ2012 አንድ እንቅስቃሴ ጀምረው ነበር። የትስስራቸው እና የጥምረታቸው መልህቅ (anchor state) ደግሞ ከሁለቱም ጋር ድንበርም፣ ቋንቋም፣ ባህልም የምትጋራው ኢትዮጵያ ነበረች። እንዳለመታደል ሆኖ በውስጣዊ እና በውጫዊ መንስኤዎች ጥምረቱ ሳይሰምር ቀርቷል።
በሁለተኛው ፎቶ የምንመለከተው ቡትቶ ጥምረት የመጀመሪያው ፎቶ ላይ ያየነውን አይነት የጥምረት ሙከራ መሰረት የለውም። የግብፅ አጀንዳ የአባይ ውሃ ነው። የሶማሊያ አጀንዳ የሶማሊላንድ ጉዳይ ነው። የኢሳያስ አጀንዳ የ”small state, big ego” ውጤት የሆነው እና ጠ/ሚ አብይ ሲመጣ ጋብ ብሎ የነበረው የኢሳያስ “ባልበላውም ጭሬ ልድፋው” ፖሊሲ ተቀፅላ ነው። ስለዚህ የሰሞኑ Hodgepodge Alliance መሰረቱ የጋራ ጥቅም ሳይሆን በኢትዮጵያ ላይ ያላቸው የጋራ ጠላትነት ነው። የጥምረቱ anchor state ያለሰፈሯ የመጣቸው ባዕድ ሃገር ግብፅ ስትሆን፤ ኤርትራ የተለመደውን የድለላ ስራ እየሰራች ነው [እዚህ ላይ አንዳንድ የፖለቲካ መሃይማን እነዚህ ሀገራት “ፀባቸው ከአብይ እንጂ ከኢትዮጵያ አይደለም” ሲሉ ሰምተናል። ከእነሱ የቀደሙት እና ራሳቸውም “ፀባቸው ከመንግስቱ ኃይለ ማሪያም/መለስ ዜናዊ እንጂ ከኢትዮጵያ አይደለም” ሲሉን እንደነበረው ማለት ነው። “ጅል አይሙት እንዲያጫውት” አይደል የሚባለው 😁]
እና ምን እናድርግ?…ያው የመጀመሪያው ስራ “housekeeping” ነው። የውስጣችንን ጉዳይ በሜዳ ላይም ይሁን በጠረጴዛ ዙሪያ በቶሎ ቋጭተን አቅማችንን በቀጠናው ላይ ያሉንን ብሄራዊ ጥቅሞች በሚያስከብር መልኩ መቃኘት አለብን። ይህ ማለት ግን የውስጥ ጉዳያችን እስኪፈታ የውጪውን እንተወዋለን ማለት አይደለም። አልተውነውምም። የቅርብ ጊዜያት እንቅስቃሴዎች እንደሚያመላክቱት የውስጡንም የውጪውንም simultaneously በሚመጥነው መልኩ ማስተናገድ ተጀምሯል። ተጠናክሮ መቀጠል አለበት። እንደበፊቱ ሜጋፎን ይዞ ማቅራራት አያስፈልግም።
ከላይ ያለው እንደተጠበቀ ሆኖ ቀጣይ እርምጃዎች በሁለት ተመጋጋቢ ስትራቴጄክ አማራጮች ላይ ተመስርተው ይሄዳሉ ብዬ እጠብቃለሁ፦
1ኛው) Balancing (የሃይል ሚዛን ማንበር) ነው። ይህም አባይን በተመለከተ ከላይኛው ተፋሰስ ሃገራት ጋር አብሮ ግብፅን ተከላካይ (isolate) ማድረግ [ዛሬ አሳሪ ስምምነት ሆኖ ወደ ስራ የገባው የNBI-CFA ጥሩ ግብአት ነው]፣ በፑንትላንድ፣ ጁባላንድ፣ ሂር ሸበሌ እና ጆውሃር ያሉንን “assets” በመጠቀም በሶማሊያ ላይ ያሉንን pressure points ሁሉ ከግምት ያስገባ signalling በቋሚነት deliver ማድረግ እና በገፍ ካሰለጠነው ተዋጊ ውጪ እዚህ ግባ የሚባል የጤናማም ሆነ የዘመናዊ ሃገረ-መንግስትነት element የሌለውን የኢሳያስ መንግስት ደጋግሞ እንዲያስብ የሚያደርግ deterrent posturing ያለ ምንም ማወላወል (unequivocally) communicate ማድረግ ነው።
2ኛው) Bandwagoning (ከጠንካራ/ጠንከር ካሉ ሃገራት ጋር ማበር) ነው። ይሄ ስለ አለም ልዕለ-ሃያል ሃገራት ብቻ ሳይሆን ስለ አካባቢው [የአፍሪካ ቀንድ እና የመካከለኛው ምስራቅ ወጠምሻ ተቀናቃኞችም) ያለንን ፖለሲ መከለስ ይጠይቃል። በተለይ በመካከለኛው ምስራቅ ያሉ ሃገራትን አንድ አይነት (homogenous) አድርጎ ለማየት የሚዳዳውን ግንዛቤያችንን መግራት፤ ከብሄራዊ ጥቅም ይልቅ ተምኔታዊ መርሆዎች ላይ የተመሰረተውን ዲፕሎማሲ መከለስ ግድ ይላል። ይህም ማለት አሁን ባለው ቀጠናዊ ሁኔታ ከእያንዳንዱ ሃገር ጋር ያለን ግንኙነት ተደማምሮ “ከአስመራ እስከ ሞቃዲሾ የተዘረጋው”ን [የቀድሞውን ጠ/ሚ መለስ አባባል ልዋስና] Hodgepodge Alliance መና የሚያስቀር መሆን አለበት። ከዚህ አንፃር እንደ ሃገር በቂ ተሞክሮ ስላለን በዚህ አቅጣጫ ገፍተን መሄዳችን አይቀሬ ነው።
በተረፈ የሰሞኑ ድራማ እና ቡትቶው ጥምረት “የቀይ ባህር ጉዳይ”ን እንደ ሰበብ የሚጠቀም እንጂ፤ መሰረታዊ መንስኤው (the structural cause) “የቀይ ባህር ጉዳይ” እንዳልሆነ ሁሉም ሊረዳው ይገባል። ግብፅ ቀይ ባህር ላይ ያላትን ጥቅም ለማስጠበቅ የሁለት ድንክዬዎችን [የሶማሊያን እና የኤርትራን] ድጋፍ አትሻም። ሶማሊያም የህንድ ውቅያኖስ እንጂ “የቀይ ባህር ሃገር” አይደለችም። ከሁሉም በላይ ጉዳዩ የቀይ ባህር ጉዳይ ቢሆን ኖሮ የምንጋፈጠው እነዚህን ሶስት ሃገራት ብቻ አልነበረም። ነገሩን “የቀይ ባህር ጉዳይ” አድርገው ሊያጮሁት የሚፈልጉት የኤርትራ operatives፣ ተላላኪዎች እና አንዳንድ አላዋቂ ኢትዮጵያውያን ናቸው። ከላይ እንደተገለፀው የቡትቶው ጥምረት መሰረት የማይናበቡ ፍላጎቶች የፈጠሩት የጋራ ጠላት ነው። እንዲህ አይነት ጥምረት ደግሞ አንድ ጠንካራ “ስትራቴጂክ ምት” ካረፈበት፤ internal cohesion እና security logic ያጣል። ስለዚህ ለሰሞኑ ድራማ dramatic ሳይሆን strategic response ብቻ ነው የሚያስፈልገው።
በተረፈ በ1969ኙ የዚያድ ባሬ ቅዠት ዙሪያ converge እንዳደረገው ግብፅን እና የውስጥ ባንዳዎችን ያቀናጀ ጥምረት፣ ጫና እና ወረራ እና በ1999ኙ የUnion of Islamic Courts እና የሻዕቢያ ቅዠት ዙሪያ converge እንዳደረገው “ከአስመራ እስከ ሞቃዲሾ” የተዘረጋ ፀረ-ኢትዮጵያ nework፤ የሰሞኑ ቡትቶ ጥምረትም በኢትዮጵያውያን ጥረት ግብአተ መሬቱ ይፈፀማል። እንደ 1969ኙ ፈተናም፤ ይህንንም ታሪክ በራሱ መስፈሪያ የእያንዳንዱን ሚና እየሰፈረ ይዘክረዋል!
A luta continua, vitória é certa