በበርክታ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ አጣብቂኝ ውስጥ ያለችው አሜሪካ ማክሰኞ፣ ጥቅምት 26/2017 ዓ.ም. ዓለም በአንክሮ የሚጠብቀውን ምርጫ ታካሂዳለች። የትራምፕ መመረጥ በርካታ ነገሮችን እንደሚቀይር በስጋትና በጉጉት የሚጠብቁት አሜሪካውያን ብቻ ሳይሆኑ መላው ዓለም ነው። ለኢትዮጵያ ጸር እንደሆነ በበርካታ ማስረጃዎች የሚከሰሰው አሁን ስልጣን ላይ ያለው አስተዳደር እንዲሸነፍ አገራቸውን የሚወዱ ምኞታቸው ነው።
አሜሪካ ለመጀመሪያ ጊዜ ሴት ፕሬዝደንት ትመርጣለች ወይስ ዶናልድ ትራምፕ ለሁለተኛ ጊዜ ነጩን ቤተመንግስት ይረከባሉ? ለሚለው ፍጻሜው ደርሷል። በተጭበረበረ ድምጽ ምርጫውን መሸነፋቸውን ያስታውቁት ዶናልድ ትራምፕ ምርጫውን ይወስናሉ ከሚባሉት ሰባት ግዛቶች መካከል አንዷ በሆነችው ሚሺጋን ባደረጉት የመጨረሻ ንግግር ተቀናቃኛቸው ካማላ ሃሪስን “ጤና የሌላቸው ግራ ዘመም አክራሪ”ብለዋቸዋል።
የአሜሪካ ምርጫ ማክሰኞ ጥቅምት 26/2017 ይደረጋል። ከኦፊሴላዊው የድምፅ መስጫ ቀን በፊት ባሉት ጥቂት ቀናት ብቻ ከ78 ሚሊዮን በላይ ሰዎች መምረጣቸው ተሰምቷል።
በርካታ የአሜሪካ ግዛቶች ከዚህ ቀደም አይተውት በማያውቁት ሁኔታ በርካታ ሰዎች ከድምፅ መስጫው ቀን በፊት እየመረጡ እንደሆ አሳውቀዋል።
ከሰባቱ ቁልፍ ግዛቶች አንዷ በሆነችው ኖርዝ ካሮላይና በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዜጎች ድምፃቸውን ሰጥተዋል።
አሪዞና፣ ጆርጂያ፣ ኔቫዳ፣ ኖርዝ ካሮላይና፣ ዊስኮንሲን፣ ፔንስሊቪኒያ እና ሚሸጋን የምርጫውን ውጤት ሊወስኑ የሚችሉ ቁልፍ ግዛቶች ናቸው።
ከእነዚህ መካከል በሚሺጋን፣ ዊስኮንሲን እና ፔንሲልቬኒያ ከማክሰኞ በፊት ድምፅ የሚሰጡ ሰዎች ቁጥር ከቀደመው ጊዜ እጅግ ልቋል።
ታር ሒል ስቴት ተብላ በምትታወቀው ኖርዝ ካሮላይና ከ4.4 ሚሊዮን በላይ አሜሪካዊያን ድምፃቸውን ሰጥተዋል። በዚህች ግዛት በ2020 ምርጫ በተመሳሳይ ወቅት ከምርጫው በፊት ድምፃቸውን የሰጡ ሰዎች ቁጥር 3.6 ሚሊዮን ነበር።
ምንም እንኳ በርካታ ሰዎች ከማክሰኞ በፊት ድምፃቸውን ቢሰጡም ካለፈው ምርጫ ጋር ሲነፃፀር ቁጥሩ ዝቅ ያለ ነው።
በአውሮፓውያኑ 2020 በተደረገው የአሜሪካ ምርጫ ከድምፅ መስጫው ቀን አስቀድሞ 101.5 ሚለዮን ሰዎች መርጠው ነበር። ነገር ግን ቁጥሩ እንዲህ ከፍ እንዲል ያደረገው ምርጫው የተካሄደው በኮቪድ ወረርሽኝ ወቅት በመሆኑ ሰዎች መጨናነቁን ፈርተው አስቀድመው በመምረጣቸው ነው። በ2016 የአሜሪካ ምርጫ 47 ሚሊዮን በ2012 ደግሞ 46 ሚሊዮን ሰዎች ነበሩ ከምርጫው ቀን በፊት ድምፃቸውን የሰጡት።
የካማላ ሃሪስ የህንድ ቅድመ አያቶች መንደር ጸሎት
በትንሿ ደቡባዊ ህንድ መንደር ቱላሴንድራፑራም ነዋሪዎች ለካማላ ሃሪስ ስኬት እንዲቀናት ለመጸለይ ተሰብስበዋል፣ የደቡብ እስያ የዘር ሀረግ ያላት ካማላ ሀሪስ የአሜሪካ የመጀመሪያዋ መሪ ለመሆን ተቃርባለእ፡፡የሃሪስ እናት አያት ከደቡብ ጠረፍ ከተማ ቼናይ 350 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው መንደር ውስጥ ከ100 አመታት በፊት ተወልደዋል። ጎልማሳ እያሉ ወደ ቼናይ ያቀኑ ሲሆን፣ ጡረታ እስኪወጡ ድረስ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣን ሆነዉ ሰርተርተዋልል።
ሃሪስ የአያቶቿን መንደር ቱላሴንድራፑራምን ጎበንታ አታውቅም እናም በመንደሩ ውስጥ ምንም ዘመድ የላትም፣ ነገር ግን እዚህ ያሉ ሰዎች በአሜሪካ ምርጫ ድል እንዲቀናት ጸሎት ከማድረግ አልተቆጠቡም፡፡“የእኛ መንደር ቅድመ አያቶች የልጅ ልጅ የአሜሪካ ፕሬዚዳንታዊ እጩ ሆና ቀርባለች። የእርሷ ድል ለእያንዳንዳችን አስደሳች ዜና ይሆናል” ሲሉ የቤተ መቅደሱ መሪ ኤም ናታራጃን ለአሶሼትድ ፕሬስ ተናግረዋል።
ናታራጃን የጌታ ሺቫ ቅርጽ በሆነው በሂንዱ አምላክ አያናር ምስል ፊት ጸሎቶችን መርተዋል። ” አምላካችን በጣም ኃያል አምላክ ነው። በመልካም ብንጸልይላት እንድታሸንፍ ይረዳታል” ብለዋል። ዲሞክራቷ ካማላ ሃሪስ እና ተቀናቃኛቸው ዶናልድ ትራምፕ የምርጫ ቅስቀሳቸውን አጠናቀዋል።የምርጫ ኮሮጆ ለድምፅ ሰጭዎች ክፍት ያደረገችው የመጀመሪያዋ የአሜሪካ ከተማ ኒው ሀምፕሸር ግዛት የምትገኘው ዲክስቪል ኖች ናት።በከተማዋ የምርጫ ጣቢያዎች የተከፈቱት በአካካቢው ሰዓት አቆጣጠር ሰኞ እኩለ ለሊት ነው። ከተማዋ ሁሌም የምርጫ ጣቢያዎቿን የምትከፍተው እኩለ ለሊት ነው።
የምርጫ ጣቢያው ሁሉም መራጮች ድምፃቸውን እስኪሰጡ ክፍት ሆኖ ቆይቷል።ባለፈው ጥር በከተማዋ የመጀመሪያ ዙር ምርጫ ሲካሄድ ድምፅ ለመስጠት የተመዘገቡ ሰዎች ቁጥር 6 ነበር።የአሜሪካ መገናኛ ብዙኃን ኒው ሀምፕሸር ግዛት የአሜሪካ ምርጫ ምን ሊመስል እንደሚችል ፍንጭ የምትሰጥ ግዛት ናት ይሏታል።ስድስቱም የአካባቢው ነዋሪዎች ድምፅ ከሰጡ በኋላ ቆጠራ የተደረገ ሲሆን ሃሪስ 3 ትራምፕ 3 ድምፅ አግኝተዋል።
የአሜሪካ ምርጫ ውጤት በሚወስኑት ሰባቱ የአሜሪካ ግዛቶች
የአሜሪካ ምርጫ ውጤት በሚወስኑት ሰባት የአሜሪካ ግዛቶች ውስጥ ሁለቱም እጩ ተወዳዳሪወች ያለብዙ ልዩነት ተፋጠው እንደሚገኙ ተገለጸ። የግዛቶቹ ነዋሪወች ከሁለቱም ፓርቲወች የተውጣጡ፣ በአሰፋፈራቸው፣ በጾታቸውና በዘራቸው መነሻነት የምርጫ አቅጣጫቸውን የሚወስኑ መሆኑም ተጠቅሷል። ደውቸ ወለ ያነጋገራቸው ከነዚሁ ወሳኝ ግዛቶች ውስጥ በአራቱ፣ በፔንሲልቫኒያ፣ በጆርጅያ፣ በኔቫዳ እና በሰሜን ካሮላይና የሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያውያን መራጮች የዘንድሮው ፉክክር ከወትሮው በተለየ መልኩ የተካረረና፣ ግዛቶቹን ማን እንደሚያሸንፍ ለመገመት አስቸጋሪ የሆነበት እንደሆነ ገልጸዋል።
አሜሪካውያን ቀጣዩን ፕሬዝዳንት ለመምርጥ ሰአታት ቀርተዋቸዋል። ያም ሆኖ ማነም ሰው በእርግጠኝነት ቀጣዩ ፕሬዝዳንት ማን ሊሆን እንደሚችል ለመገመት በማይችልበት እጅግ ተቀራራቢ ደረጃ ላይ ናቸው። ለዚህ ደግሞ በተለምዶ ‘ስዊንግ ስቴት’፣ በመባል የሚጠሩት፣ የኋይት ሃውስን ቁልፍ የያዙት ሰባት የአሜሪካ ግዛቶች ዋና አውደ ፉክክርናቸው። በጣም በጠበበ ልዩነት ሁለቱም እጩወች የተፋጠጡባቸው ግዛቶች ፔንሲልቫንያ፣ ሚቺጋን፣ ዊስኮንሰን፣ ኔቫዳ እና ሰሜን ካሮላይና ናቸው።
እነዚህ ግዛቶች የፉክክር ቀጠና ተብለው የሚታወቁበት ምክንያት በየትኛውም ምርጫ ወቅት ሁልጊዜ ወደ አንድ ፓርቲ ወይም ወደ አንድ እጩ የማያዘነብሉ፣ ሁሉም እጩወች ጥረው፣ ግረው፣ ቀስቅሰውና ለምነው የሚያገኟቸው መሆናቸው ነው። የተለያየ ዳራ ያለው ህዝብ የሚኖርባቸው፣ የሚቀያየር የኢኮኖሚ ስጋት እና የፖለቲካ ትኩረት የሚፈራረቅባቸው፣ ለመተንበይ የማይመቹ፣ ኋይት ሃውስን ለማሸነፍ ዋና መንገድ በመሆናቸውም ጭምር ነው። እናም እንደ ሁል ጊዜው፤ ዶናልድ ትራምፕም ሆኑ ከማላ ሃሪስ በነዚሁ ግዛቶች ላይ የምረጡኝ ቅስቀሳቸውን አጧጡፈዋል። ብዙ ገንዘብ አፍስሠው አየሩን በማስታወቅያ አጨናንቀዋል። በያንዳንዱ የምርጫ ዞን ተመላልሰው ቀስቅሰዋል። ከነዚሁ ግዛቶች ውስጥ አንዷ የሆነችውና ሁለቱም እጩወች ያለማናቸውም መሪነት የተፋጠጡባት ግዛት ፔንሲልቫንያ ናት።የግዛቷ ነዋሪ የሆኑት ትውልደ ኢትዮጵያዊው መራጭ አቶ ፈቃዱ የህዝቡ ድጋፍና የሚመረጥበት ጉዳይ ትኩረት ከቦታ ቦታ ይለያያል ባይ ናቸው።
በግዛቷ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ከዚህ ቀደም ተደራጅተው ዲሞክራቶችን ሲደግፉ መቆየታቸውን የገለጹት አቶ ፈቃዱ፣ በተለይ ከጾታና ከማህበራዊ ጉዳዮች ጋር በተያያዘ ዲሞክራቶች የያዙት አቋም ብዙወችን ወደ ሪፐብሊካን አልያም በዘንድሮው ምርጫ ወዳለመሳተፍ እየገፋቸው መሆኑን ገልጸዋል። ሌላዋ የፉክክር መድረክ የሆነችው ግዛት ኔቫዳ ናት። ደማቋን ላስቬጋስን ጨምሮ በአብዛኛው አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ላይ ያተኮረ ኢኮኖሚ ያላት ኔቫዳ፣ በዘንድሮውም ምርጫ ወሳኝ ሚና ይዛ የሁለቱም ተፎካካሪወች ማዕከል ሆናለች። አቶ እስክንድር ወርቁ በላስ ቬጋስ፣ ኔቫዳ ነዋሪ ናቸው። በኔቫዳ ግዛት ውስጥም የህዝቡ አሰፋፈር በድምጽ አሰጣጡና በውጤቱ ላይ ሚና እንዳለው አቶ እስክንድር ጠቁመዋል።
በላስ ቬጋስ ውስጥ ብዙ ትውልደ ኢትዮጵያውያን መኖራቸውን ያስታወሱት አቶ እስክንድር፣ አብዛኛወቹ ለዲሞክራቶች፣ ከግብር እና ከኢኮኖሚ አንጻር ምርጫውን የሚያዩት ደግሞ ለሪፐብሊካኖች እንደሚመርጡ ተናግረዋል። ሌላዋ ግዛት ጆርጅያ ናት። ባለፉት አራት አመታት በተለይ የአፍሪካ አሜሪካውያን የፖለቲካ ተሳትፎ ሰፍቶ ግዛቷ ከቀይ፣ ሪፐብሊካን ግዛትነት ጎራ ወጥታ እንዲህ በቀላሉ ወደማትወሰድ፣ ውድ ግዛትነት መቀየሯን የአትላንታ፣ ጆርጅያ ነዋሪ የሆኑት ዶ/ር ማሾ አብረሃ ነግረውኛል። አያይዘውም በዘንድሮው ምርጫ ማ፤ ማንን ይመርጣል የሚለው ጥያቄ የሚመለሰው በጾታ፣ በእድሜና በዘር አወቃቀር ጭምር እንደሆነ ጠቁመዋል። ዶ/ር ማሾ፤ ሃበሻ ለሃሪስ የሚል የፖለቲካ የድጋፍ ቡድን ቅስቀሳ እያደረገ እንደሆነና ኢኮኖሚና፣ የስደተኞች ህግ ዋና ርዕሰ ጉዳዮች መሆናቸውም ጠቁመዋል።
ሰሜን ካሮላይና ሌላዋ ወሳኝ ግዛት ናት።በአብዛኛው ወግ አጥባቂ ህዝብ ያለባት ግዛት እንደሆነች የግዛቷ ነዋሪ የሆኑት ማህሌት ተሾመ ገልጸዋል። መራጩ ህዝብ በአብዛኛው ወደ ሪፐብሊካን የማድላት አዝማምያ ያለው ቢሆንም በዘንድሮው ምርጫ ግን ውጤቱ ወዴት አቅጣጫ ሊሄድ እንደሚችል ለመገመት ያዳግታል ብለዋል።
እነዚህ ወሳኝ ግዛቶች ነገ በሚደረገው ምርጫ የአሜሪካንን ፕሬዝዳንት ማንነት የሚወስኑ ናቸው። የሁሉም መርጭ ህዝብ ተስፋ ከሁለቱ እጩወች አንዳቸው በማያወላዳ ሰፊ ልዩነት አሸንፈው፣ በምርጫው እለት አሸናፊው ይለይ ዘንድ ነው። ግና የዘንድሮው ምርጫ ማንም ሰው እርግጠኛ ያልሆነበት፣ እስካሁን የተደረጉ መጠይቅ ውጤቶች ሁለቱንም እጩወች ለመለየት በሚከብድ ተቀራራቢ ውጤት ላይ ያስቀመጡበት፣ ዶናልድ ትራምፕም በምርጫው ከተሸነፉ ውጤቱን አልቀበልም ሊሉ የሚችሉበትን መደላድል ከወዲሁ ያስቀመጡበት እለት ላይ ነው ያለነው። እናም ሁሉም አሜሪካዊ ነገ ምን ይዛ እንደምትመጣ ለማየት በጉጉት እየጠበቀ ነው። ውጤቱን አብረን የምናየው ይሆናል።