በታካሚዎች የጉሉኮስ መስጫ ከረጢት ውስጥ የልብ ማቆሚያ መርዝ በመርፌ በመመረዝ የተከሰሰው የቴክሳስ የሰመመን ባለሙያ ዶክተር በ190 ዓመታት እስራት ተቀጥቷል።
ሬይናልዶ ሪቪዬራ ኦርቲዝ የተባለው የ60 ዓመቱ የህክምና ባለሙያ “የህክምና አሸባሪ” የሚል ቅፅል ስም ተሰጥቶታል። ከቀረቡበት የክስ መዝገቦች መካከል በአራት ክሶች የህክምና ምርቶችን በመመረዝ ከባድ የአካል ጉዳት በማድረስ ፣ በአንድ ክስ በህክምና ምርት ላይ ጉዳት እንዲያደርስ በማድረግ እና በአምስት መዝገብ ደግሞ ሆን ብሎ ተገቢ ያልሆነ ንጥረ ነገር በመጨመር በህክምና ሂደቱ የጥራት ጉድለት እንዲፈጠር በማድረግ ጥፋተኛ ሆኖ ተገኝቷል። ባለፈው ዓመት በሚያዝያ ወር ከስምንት ቀናት የምርመራ ሂደት በኋላ ተደርሶበታል። የቅጣት ውሳኔ የተላለፈው በዩናይትድ ስቴትስ ዋና ዳኛ ዴቪድ ጎድቤይ ሲሆን የኦርቲዝን ድርጊት ከግድያ ሙከራ ጋር እኩል በመሆኑ የተነሳ ነው።
የዩናይትድ ስቴትስ አቃቤ ህግ ሊጋ ሲሞንተን በውሳኔ ሀሳቡ ተስማምቷል። ነውረኛ ድርጊትን የፈፀመው ይህው ዶክተር የጦር መሳሪያ የታጠቀ አካል በህዝብ ላይ ያለ ልዩነት ጥይት እንዲመተኩሰው ሁሉ ይህ ተግባርም ተመሳሳይ ነው ተብሏል። ዶ/ር ኦርቲዝ በዘፈቀደ የግሉኮስ ከረጢቶች ላይ ሕመምተኞች እንዲፈውሱ ለመርዳት በተዘጋጀው መድኃኒት ውስጥ መርዝ ይቀላቅል እንደነበር አቃቤ ህግ ሲሞንተን ተናግረዋል።ቢያንስ በዘጠኝ የተለያዩ አጋጣሚዎች ንቃተ ህሊና የሌላቸውን ታካሚዎች በቀዶ ህክምና አልጋ ላይ ተኝተው እንዳጠቃቸው የክሱ ዝርዝር ያሳያል። የጉዳት ሰለባዎቹ እና ቤተሰቦቻቸው በብዙ ቢጎዱም አጥፊው ለህግ በማቅረባችን በአጋሮቼ ኩራት ይሰማኛል ሲሉ አቃቤ ህግ ሊጋ ሲሞንተን ገልፀዋል።
ከቴክሳስ ሰሜናዊ አውራጃ የዩናይትድ ስቴትስ አቃቤ ህግ ጽህፈት ቤት የወጣው መረጃ እንደሚያሳየው የወንጀል ድርጊቱ በሚፈፀምበት ወቅት ዶክተሮች የታካሚዎቻቸው የደም ግፊት በድንገት ሲጨመሩ ግራ ይጋቡ እንደነበር ተናግረዋል ። የሕክምና መዝገቦችን ከገመገሙ በኋላ ከእያንዳንዱ ክስተት ጋር አንድ የሚያመሳስለው ነገር አግኝተዋል። ድንገተኛ አደጋዎች የተከሰቱት በግሉኮስ መስጫ ከረጢቶች መመረዝ እንደሆነም ደርሰውበታል። የቀረቡት መረጃዎች እንደሚያሳዩት እ.ኤ.አ. በ 2022 በተለመደው የሕክምና ሂደቶች የልብ ድንገተኛ አደጋዎች ህሙሟን አጋጥሟቸዋል ይላል።
ምክንያቱ ካልታወቀ ድንገተኛ የልብ ህመም በኋላ፣ አንድ የማደንዘዣ ባለሙያ ለራሷ እንደተመረዘ ያላወቀችውን የጉሉኮስ ከረጢት በተጠቀመችበ ዕለት ህይወቷ አልፏል። ባለቤቷ ዶ / ር ጆን ካስፓር የሚስቱን ህልፈት ሲያስታውስ “ሕይወት አልባ ዓይኖች” አሁንም እንደሚያሳዝኑት መጥፎ ትዝታ ጥለውበት እንዳለፈ ለፍርድ ቤቱ ተናግረዋል። እሷ በህይወቴ በጣም ጠንካራዋ ሴት ነበረች በማለት አክለዋል።ሌላ ተጎጂ እንዳለው የልብ ህመም ከደረሰብኝ በኋላ ከእንቅልፌ ስኑ እንደታኘክ ዓይነት ስሜት ይሰማኝ ነበር ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ደህና አይደለሁም ሲል ተደምጧል።ኦርቲዝ ፍርዱ ሲሰጥ እና የተጎጂዎችን ቃል ላለመስማት መብቱን ተጠቅሞ በችሎት ቦታው አልነበረም።
via ዳጉ_ጆርናል