ከፍተኛ ቁጥር ያለው የቁም እንስሳት በሰ/ጎንደር በደባርቅ በኩል ወደ ትግራይ ክልል እና አፋር በማድረግ ወደ ጅቡቲ የኮንትሮባንድ መስመር በህገወጥ መንገድ ቀደም ሲል ክነበረው በተለዬ ሁኔታ በአሁኑ ወቅት እየወጡ ስለሆነ በአጠቃላይ ለችግሩ መፍትሔ እስከሚሰጥበት ድረስ ከአሁን በፊት የተከለከሉት አካባቢዎች እደተጠበቁ ሆኖ በተጨማሪ መነሻቸውን ምዕ/ጎንደር‘ ማዕከላዊ ጎንደር‘ ሁመራ ዞን፣ ጎንደር ከተማ አስተዳደር እና ከሌሎች ምዕራብ አማራ ዞኖች በመነሳት መዳረሻቸውን ወደ ትግራይ ክልል ለሚጓጓዙ የቁም እንስሳት ይህ ደብዳቤ ከተፃፈበት ቀን ጀምሮ የማጓጓዝ ፈቃድ/መሸኛ መስጠት የተከለከለ ሲሆን ተገቢውን ክትትልና ቁጥጥር እንዲደረግ እናሳውቃለን።
ቀደም ሲል ታይቶ በማይታወቅ ደረጃ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የቁም ከብት በኮንትሮባንድ ወደ ጅቡቲ እየተጋዘ መሆኑንን ጠቅሶ የአማራ ክልል የንግድና ገበያ ቢሮ የዕግድ ማዘዣ ደብዳቤ አሰራጨ።
ለዞኖች አስተዳደር ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ የተሰራጨው ይህ የዕግድ ደብዳቤ በስም ጠቅሶ ክልከላውን ያደረገው ወደ ትግራይ የሚጋዙ የቁም እንስሳቶች ላይ ነው።
“ከፍተኛ ቁጥር ያለው የቁም እንስሳት በሰ/ጎንደር በደባርቅ በኩል ወደ ትግራይ ክልል እና አፋር በማድረግ ወደ ጅቡቲ የኮንትሮባንድ መስመር በህገወጥ መንገድ ቀደም ሲል ክነበረው በተለዬ ሁኔታ በአሁኑ ወቅት እየወጡ ስለሆነ በአጠቃላይ ለችግሩ መፍትሔ እስከሚሰጥበት ድረስ ከአሁን በፊት የተከለከሉት አካባቢዎች እደተጠበቁ ሆኖ…” በሚል የሚያሳስበው ደብዳቤ፣ “መነሻቸውን ምዕ/ጎንደር‘ ማዕከላዊ ጎንደር‘ ሁመራ ዞን፣ ጎንደር ከተማ አስተዳደር እና ከሌሎች ምዕራብ አማራ ዞኖች በመነሳት መዳረሻቸውን ወደ ትግራይ ክልል ለሚጓጓዙ የቁም እንስሳት ይህ ደብዳቤ ከተፃፈበት ቀን ጀምሮ የማጓጓዝ ፈቃድ/መሸኛ መስጠት የተከለከለ ሲሆን ተገቢውን ክትትልና ቁጥጥር እንዲደረግ እናሳውቃለን።” ይላል።
የቁም ከብት ብቻ ሳይሆን የቅባት ዕህልን ጨምሮ ማዕድን በኮንትሮባንድ ወደ ትግራይ፣ ኤርትራና ሱዳን የሚያግዙ መኖራቸውን ምስክሮች በተደጋጋሚ ጥቆማ ሲሰጡ እንደነበር ይታወሳል። የደብዳቤው ሙሉ ቃል ከስር ያለው ነው።
ጕዳዩ የቁም እንስሳት የማጓጓዝ ፈቃድን ይመለከታል
አማራ ብሔራዊ ክልል ክፍተኛ ቁጥር ያለው የቁም እንስሳት ሁበት እንደሚገኝ ይታወቃል፡፡ ይሁን እንጂ ክልሉ ካለው የቁም አንስሳት ሀብት አኳያ የሚያገኘው የኤክስፖርት ገቢ በጣም ዝቅተኛ ነው። ከዚሁ ጋር ተያይዞ የፌደራል የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር በቀን 24/09/2018 ዓ.ም በቁጥር 0185/40025 በፃፈው ደብዳቤ የሀገር ውስጥ የቁም እንስሳት የጉዞ መሸኛን ሽፋን በማድረግ ወደ ጎረቤት ሀገሮቹ በህገወጥ መንገድ/ በኮንትሮባንድ/ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የቁም እንስሳት እየወጣ መሆኑን በደብዳቤ አሳውቆናል፡፡
ለዚህም እንደሽፋን ከሚጠቀሱት ሁኔታዎች መካከል የሀገር ውስጥ የቁም እንስሳት የጉዞ መሸኛ ፈቃድ ይዞ መዘዋወር ሲሆን በተለይም መነሻቸውን ዳንሻ፣ መተማ ቦረና፤ ባሌ፣ አዳማና መተሐራ የሚያደርጉ የቁም እንስሳት በአፋር ክልል አዋሽ ወደ ሰመራ፤ በባቢሌ ወደ ፋፊም ዞን በማድረግ በጭነት መኪኖች ተጭነው በከፍተኛ ሁኔታ ወደ ሶማሌ ላንድና ጅቡቲ በህገወጥ መንገድ እየወጡ ስለሆነ መዳረሻቸውን ከላይ ወደ ተጠቀሱት አካባቢዎችና ወደ ሀገራቱ የመውጫ መስመሮች ላይ ወደ ሚገኙ ቦታዎች በማድረግ ለሚንቀሳቀሱ የሀገር ውስጥ የቁም እንስሳት ግብይት ተዋናዮች ምንም አይነት የቁም እንስሳት የማጓጓዝ ፈቃድ/መሸኛ መስጠት የተከለከለ መሆኑን በቁጥር 02/ም/1/11238/15 በቀን 30/00/2015 ዓ.ም በተፃፈ ደብዳቤ ለሁሉም ዞንና ከተማ አስተዳደር ንግድና /ል/መምሪያ ቢሮው ማሳወቁና ወደ ስራ ገብቶ የቆየ መሆኑ ይታወቃል፡፡

አሰላምታ ጋር