ደጋፊዎቻቸው ፊት ቆመው “አመስግናለሁ የአሜሪካ ህዝብ፣ እንኳን ለወርቃማው የአሜሪካኖች ዘመን አደረሳችሁ። አሜሪካን ዳግም ታላቅ እንዳርጋለን፣ ይህ ለአሜሪካን ህዝብ አንጸባርራቂ ድል ነው …” ሲሉ በአድናቆት ምላሽ ይሰጣቸው ነበር።
ሰውየውን አስቀድመው ሲያወጉዝ የነበሩ የአውሮፓ አገራት 270 ነጥብ ከመመዝገቡ ቀድመው “እንኳን ደስ አለዎ፤ አብረን ለመስራት ዝግጁ ነን” የሚል የእንኳን አደረስዎ መልዕክት አስተላፈዋል። ከሁሉም በላይ አስገራሚው የዩክሬን ፕረዚዳንት ዛለንኪ ምርጫው ይፋ ሳይሆን አስቀድመው “አድናቂዎት ነኝ” ማለታቸው ነው።
“ጦርነትን ከጠላችሁ ምረጡኝ” በሚል በምርጫ ዘመቻ ተፎካካሪያቸውን ጦረኛና ግራ ዘመም በማለት የወረፉት ትራምፕ፣ ወደ ስልጣን በመጡ በማግስቱ የዩክሬንና ሩሲያን አውዳሚ ጦርነት ጸጥ እንደሚያደርጉ ቃል ገብተዋል። ለዚህም ነው መሰለ ከባይደን አስተዳደር ጋር ሆነው ሩሲያን እንደሚያሸንፉ ሲፎክሩ የነበሩት ዘለንስኪ፣ ፕሬዚዳንት ትራምፕ በዓለም አቀፍ ጉዳዮችና ለሰላም ያላቸውን ጽናት እንደሚያደንቁ ጠቅሰው፣ መመረጣቸው ለዩክሬን ሰላም እንደሚያመጣ እርግጠኛነታቸውን ጠቅሰዋል። “I appreciate President Trump’s commitment to the ‘peace through strength’ approach in global affairs. This is exactly the principle that can practically bring just peace in Ukraine closer. I am hopeful that we will put it into action together,” he said.
ከአውሮፓ ህብረት፣ ከኖቶ መሪዎች ጎን ለጎን የአፍሪካ አገራት ለትራምፕ እንኳን ደስ አለዎት እያሉዋቸው ነው። “በምርጫ አሸናፊነትዎና ወደ ፕሬዚዳንትነት ስልጣንዎ በመመለስዎ እንኳን ደስ አለዎት ማለት እወዳለሁ” ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይን በኤክስ ገጻቸው መልዕክት አጋርተዋል። ኢትዮጵያ ከእስራኤል ጋር ከጀመረችው ግንኙነት፣ ከአረብ ኢምሬትስ ጋር የዘረጋችውን ከብረት የጠነከረ ግንኙነት የሚያሰሉ የዶናልድ ትራምፕ ወደ ነጩ ቤተመንግስት መመለስ ለኢትዮጵያ መልካም አጋጣሚ እንደሆነ አስቀድመው ሲተነትኑ እንደነበር ይታወሳል።
ዴሞክራቶች ኢትዮጵያ ላይ በተለያዩ ወቅቶች ከፈጸሙት ታሪክ የማይረሳቸው ወንጀሎች አንጻር ኢትዮጵያን የሚወዱ የትራምፕን መመረጥ ሲጠብቁ ነበር።

ማክሰኞ በተጀመረውና ለሊቱን ሙሉ ዓለም በአንክሮ ሲከታተለው የነበረው ምርጫ፣ በሪፐብሊካኑ የቀድሞው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ አሸናፊነት ተጠናቋል። ካማላ ሃሪስ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ለመሆን ያደረጉት መፍጨርጨር አብቅቷል። ከምርቻ ጣቢያዎች በየደረጃ የሚወጡ የምርጫ ውጤቶች ዶናልድ ትራምፕ ለሁለተኛ ጊዜ መመረጣቸውን ይፋ አድርገዋል። “Live election updates: Donald Trump wins US presidency” ሲሉ ታዋቂ ሚዲያዎች በቀጥታ ስርጭታቸው ቢያውጁም ቀደም ብለው ትራምፕ ራሳቸው “አሸንፌያለሁ” በማለት ደጋፊዎቻቸውን ጮቤ አስረግጠዋል።
የአሜሪካ የምርጫ ውጤት በይፋ ባይገለጽም የሪፐብሊካኑ ዕጩ ዶናልድ ትራምፕ “ድል አድርጌያለሁ፤ ትራምፕ “አስደናቂ ድል ተቀዳጀሁ” ከማለታቸ በፊት ነገሩ የገባት የኒውዮርክ ታይም ዘጋቢ በቅጥታ ሪፖርቷ ላይ ” ዛሬ ወደ ጉዋላ ስምንት ዓመት ተመልሼ የሆነውን እንዳስብ ሆኛለሁ” በማለት ለሊት ተነስታ ባቡር ስትይዝ የገጠማትን ጽፋለች።
ክላር ማሮን እንዳለቸው ከስምንት ዓመት በፊት፣ ከእንቅልፏ ነቅታ በኒውዮርክ የምድር ውስጥ ባቡርን ተሳፍራ ስትጓዝ ግራና ቀኝ ግድግዳዎቹ በሙሉ የድህረ-ምረጫ ስሜቶች ተሞልተውባቸው አይታለች። ይህን ካስታወሰች በሁዋላ፣ “አሁን ትራምፕ ካሸነፉ ተመሳሳይ ስሜት የሚያንቀጥቀጥ ነገር ካለ ሊያስገርመኝ አይችልም” የሚል አስተያየቷን ጽፋላች።
ነገሩ ከጅምሩ የገባቸው ትራምፕ እንደሚያሸንፉ የሚጠቋቁሙ ምልክቶችን ይሰጡ ነበር። እንዳሉትም በሰባቱ ወሳኝ የምርጫ ግዛቶች ሳይቀር ትራምፕ አስፈላጊ የተባለ ድል ተቀዳጁ። ትራምፕ ብቻ ሳይሆኑ ሪፐብሊካኖች በሁለቱም ምክር ቤቶች የበላይነት መያዛቸው ጎን ለጎን ይፋ ሆነ፣ “ይህችን አገር እንዲያስተዳድር ትራምፕ በእግዚአብሔር ተልኳል” በሚል ጸሎትና ምስጋና ሲያቀርቡ የነበሩ ወንጌላዊያን ሳይቀር ፈንጠዚያ ላይ ሲሆኑ፣ በተቃራኒው ዴሞክራቶች በረዶ ሆነዋል።